የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 7

7
ጌዴ​ዎን ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንን ድል እንደ አደ​ረገ
1ጌዴ​ዎን የተ​ባ​ለ​ውም ይሩ​በ​ኣል ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ማል​ደው ተነሡ፤ በአ​ሮ​ኤድ ምንጭ አጠ​ገብ ሰፈሩ፤ የም​ድ​ያ​ምም ሰፈር ከእ​ነ​ርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረ​ብታ አጠ​ገብ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ነበረ።
2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ከአ​ንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝ​ቶ​አል፤ ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤል፦ እጄ አዳ​ነኝ ብሎ እን​ዳ​ይ​ታ​በ​ይ​ብኝ እኔ ምድ​ያ​ምን በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።” 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሁን እን​ግ​ዲህ፥ “የፈራ፥ የደ​ነ​ገ​ጠም ከገ​ለ​ዓድ ተራራ ተነ​ሥቶ ይመ​ለስ ብለህ በሕ​ዝቡ ጆሮ አውጅ” አለው። ከሕ​ዝ​ቡም ሃያ ሁለት ሺህ ተመ​ለሱ፤ ዐሥ​ርም ሺህ ቀሩ።
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ሕዝቡ ገና ብዙ ነው፤ ወደ ውኃ አው​ር​ዳ​ቸው፤ በዚ​ያም እፈ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔም፦ ይህ ከአ​ንተ ጋር ይሂድ የም​ለው እርሱ ከአ​ንተ ጋር ይሄ​ዳል፤ እኔም፦ ይህ ከአ​ንተ ጋር አይ​ሂድ የም​ለው እርሱ አይ​ሄ​ድም” አለው። 5ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ውኃ አወ​ረደ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ውሻ እን​ደ​ሚ​ጠጣ ውኃ በም​ላሱ የሚ​ጠ​ጣ​ውን ሁሉ፥ እር​ሱን ለብ​ቻው አድ​ር​ገው፤ እን​ዲ​ሁም ሊጠጣ በጕ​ል​በቱ የሚ​ን​በ​ረ​ከ​ከ​ውን ሁሉ ለብ​ቻው አድ​ር​ገው” አለው። 6በእ​ጃ​ቸ​ውም ውኃ ወደ አፋ​ቸው አድ​ር​ገው የጠ​ጡት ቍጥር ሦስት መቶ ሆነ፤ የቀ​ሩት ሕዝብ ግን ውኃ ሊጠጡ በጕ​ል​በ​ታ​ቸው ተን​በ​ረ​ከኩ። 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “በእ​ጃ​ቸው ውኃ በጠ​ጡት በሦ​ስት መቶ ሰዎች አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ ምድ​ያ​ም​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ የቀ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ግን ወደ ስፍ​ራ​ቸው ይመ​ለሱ” አለው። 8የሕ​ዝ​ቡ​ንም ስን​ቅና ቀንደ መለ​ከት በእ​ጃ​ቸው ወሰዱ፤ የቀ​ሩ​ት​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው ሰደ​ዳ​ቸው፤ ሦስ​ቱን መቶ ሰዎች ግን በእ​ርሱ ዘንድ ጠበ​ቃ​ቸው፤ የም​ድ​ያ​ምም ሰፈር ከእ​ርሱ በታች በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ነበረ።
9በዚ​ያ​ችም ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ተነ​ሥ​ተህ ወደ ሰፈር ውረድ። 10ብቻ​ህ​ንም ለመ​ው​ረድ ብት​ፈራ አንተ ከሎ​ሌህ ፋራን ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፤ 11የሚ​ና​ገ​ሩ​ት​ንም አድ​ም​ጣ​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ እጆ​ችህ ይበ​ረ​ታሉ፤ ወደ ሰፈ​ርም ትወ​ር​ዳ​ለህ” አለው። እር​ሱም ከሎ​ሌው ፋራን ጋር ከሰ​ፈሩ በአ​ንድ ወገን የአ​ምሳ አለቃ ጦር ወደ ሰፈ​ረ​በት ወረደ። 12ብዛ​ታ​ቸ​ውም እንደ አን​በጣ የሆነ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንና አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን የም​ሥ​ራ​ቅም ልጆች ሁሉ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ሰፍ​ረው ነበር፤ የግ​መ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ብዛት ቍጥር እን​ደ​ሌ​ለው በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ነበረ። 13ጌዴ​ዎ​ንም በደ​ረሰ ጊዜ አንድ ሰው ሕል​ምን ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ሲያ​ጫ​ውት፥ “እነሆ፥ ሕልም አለ​ምሁ፤ እነ​ሆም፥ አን​ዲት የገ​ብስ እን​ጎቻ ወደ ምድ​ያም ሰፈር ተን​ከ​ባ​ልላ ወረ​ደች፤ ወደ ድን​ኳ​ኑም ደርሳ እስ​ኪ​ወ​ድቅ ድረስ መታ​ችው፤ ገለ​በ​ጠ​ች​ውም፤ ድን​ኳ​ኑም ወደቀ” ይል ነበር። 14ባል​ን​ጀ​ራ​ውም መልሶ፥ “ይህ ነገር ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰው ከኢ​ዮ​አስ ልጅ ከጌ​ዴ​ዎን ሰይፍ በቀር ሌላ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ያ​ም​ንና ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ በእጁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አል” አለው።
15ጌዴ​ዎ​ንም ሕል​ሙ​ንና ትር​ጓ​ሜ​ዉን በሰማ ጊዜ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ሰፈር ተመ​ልሶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ያ​ምን ሠራ​ዊት በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና ተነሡ” አለ። 16ሦስ​ቱ​ንም መቶ ሰዎች በሦ​ስት ወገን ከፈ​ላ​ቸው፤ በሁ​ሉም እጅ ቀንደ መለ​ከ​ትና ባዶ ማሰሮ፥ በማ​ሰ​ሮ​ዉም ውስጥ ችቦ ሰጣ​ቸው። 17እር​ሱም፥ “እኔን ተመ​ል​ከቱ፤ እን​ዲ​ሁም አድ​ርጉ፤ እነ​ሆም፥ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ በደ​ረ​ስሁ ጊዜ እኔ እን​ደ​ማ​ደ​ርግ እን​ዲሁ እና​ንተ አድ​ርጉ፤ 18እኔ ከእ​ኔም ጋር ያሉት ሁሉ ቀንደ መለ​ከት ስን​ነፋ፥ እና​ንተ ደግሞ በሰ​ፈሩ ዙሪያ ሁሉ ቀንደ መለ​ከ​ታ​ች​ሁን ንፉ፦ ኀይል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ሰይፍ የጌ​ዴ​ዎን በሉ”#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ለጌ​ዴ​ዎን በሉ” ይላል። አላ​ቸው።
19ጌዴ​ዎ​ንም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት መቶ ሰዎች በመ​ካ​ከ​ለ​ኛው ትጋት መጀ​መ​ሪያ ዘብ ጠባ​ቂ​ዎች ሳይ​ነቁ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ች​ንም ነፉ፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም የነ​በ​ሩ​ትን ማሰ​ሮ​ዎች ሰባ​በሩ፤ 20ሦስ​ቱም ወገ​ኖች ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ችን ነፉ፤ ማሰ​ሮ​ዎ​ች​ንም ሰበሩ፤ በግራ እጃ​ቸ​ውም ችቦ​ዎ​ችን፥ በቀኝ እጃ​ቸ​ውም ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ችን ይዘው እየ​ነፉ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና የጌ​ዴ​ዎን ሰይፍ” ብለው ጮኹ። 21ሁሉም በየ​ቦ​ታው፥ በሰ​ፈሩ ዙሪያ ቆመ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ ደን​ግ​ጠው ሸሹ። 22ሦስ​ቱ​ንም መቶ ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ችን ነፉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ውን ሁሉ ሰይፍ በባ​ል​ን​ጀ​ራ​ዉና በሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ ላይ አደ​ረገ፤ ሠራ​ዊ​ቱም በጽ​ሬራ በኩል እስከ ቤት​ሲጣ ጋራ​ጋታ ድረስ በጣ​ባት አጠ​ገብ እስ​ካ​ለው እስከ አቤ​ል​ሜ​ሁላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ። 23የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምና ከአ​ሴር፥ ከም​ና​ሴም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው ምድ​ያ​ምን አሳ​ደዱ።
24ጌዴ​ዎ​ንም፥ “ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንን ለመ​ግ​ጠም ውረዱ፥ እስከ ቤት​ባ​ራም ድረስ ያለ​ውን ውኃ፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም፥ ያዙ​ባ​ቸው” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን በኤ​ፍ​ሬም ወዳ​ለው ተራ​ራማ ሀገር ሁሉ ላከ። የኤ​ፍ​ሬ​ምም ሰዎች ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው እስከ ቤት​ባራ ድረስ ውኃ​ውን፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ቀድ​መው ያዙ። 25የም​ድ​ያ​ምን ሁለ​ቱን አለ​ቆች ሔሬ​ብ​ንና ዜብን ያዙ፤ ሔሬ​ብ​ንም በሱ​ር​ኤ​ራብ#ዕብ. “በሔ​ሬብ ዐለት አጠ​ገብ” ይላል። ገደ​ሉት፥ ዜብ​ንም በኢ​ያ​ፌቅ ገደ​ሉት፤ የም​ድ​ያ​ም​ንም ሰዎች አሳ​ደዱ፤ የሔ​ሬ​ብ​ንና የዜ​ብ​ንም ራስ ይዘው ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ጌዴ​ዎን አመጡ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ