ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 16

16
ስለ ኤር​ም​ያስ ሕይ​ወት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2በዚህ ስፍራ ሚስት አታ​ግባ፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ንም አት​ው​ለድ። 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ስፍራ ስለ ተወ​ለዱ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች፥ ስለ ወለ​ዱ​አ​ቸ​ውም ስለ እና​ቶ​ቻ​ቸው፥ በዚ​ህ​ችም ምድር ስለ ወለ​ዱ​አ​ቸው ስለ አባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዲህ ይላ​ልና፦ 4“በክፉ ሞት ይሞ​ታሉ፤ አይ​ለ​ቀ​ስ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ቀ​በ​ሩ​ምም፤ ነገር ግን በመ​ሬት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ፤ በሰ​ይ​ፍም ይወ​ድ​ቃሉ፤ በራ​ብም ይጠ​ፋሉ፤ ሬሳ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለዱር አራ​ዊት መብል ይሆ​ናሉ።”
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰላ​ሜን፥ ቸር​ነ​ቴ​ንና ምሕ​ረ​ቴን፥#“ቸር​ነ​ት​ንና ምሕ​ረ​ትን” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ከዚህ ሕዝብ አስ​ወ​ግ​ጄ​አ​ለ​ሁና ልቅሶ ወዳ​ለ​በት ቤት አት​ግባ፤ ታለ​ቅ​ስና ታዝ​ንም ዘንድ አት​ሂድ። 6ታላ​ላ​ቆ​ችና ታና​ና​ሾች በዚች ምድር ይሞ​ታሉ ፥ አይ​ቀ​በ​ሩም#“ታላ​ላ​ቆ​ችና ታና​ና​ሾች በዚች ምድር ይሞ​ታሉ ፤ አይ​ቀ​በ​ሩም” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ሰዎ​ችም አያ​ለ​ቅ​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ ስለ እነ​ር​ሱም ፊት አይ​ነ​ጩ​ላ​ቸ​ውም፤ ራስ​ንም አይ​ላ​ጩ​ላ​ቸ​ውም፤ 7ሰዎ​ችም ስለ ሞቱት ለማ​ጽ​ና​ናት የእ​ዝን እን​ጀራ አይ​ቈ​ር​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ ስለ አባ​ታ​ቸ​ውና ስለ እና​ታ​ቸ​ውም የመ​ጽ​ና​ናት ጽዋ አያ​ጠ​ጡ​አ​ቸ​ውም። 8ትበ​ላና ትጠጣ ዘንድ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ለመ​ቀ​መጥ ወደ ግብዣ ቤት አት​ግባ።” 9ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት በዘ​መ​ና​ች​ሁም የእ​ል​ል​ታን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ፅና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስ​ቀ​ራ​ለሁ።
10“ለዚ​ህም ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተ​ና​ገ​ርህ ጊዜ፦ ይህን ሁሉ ትልቅ የሆነ ክፉ ነገ​ርን ስለ ምን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገ​ረ​ብን? በደ​ላ​ች​ንስ ምን​ድን ነው? በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ግ​ነው ኀጢ​አት ምን​ድን ነው? ቢሉህ፥ 11አንተ እን​ዲህ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ እኔን ስለ ተዉ ነው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ተከ​ተሉ፤ አመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውም፤ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤ እነ​ር​ሱም ትተ​ው​ኛል፤ ሕጌ​ንም አል​ጠ​በ​ቁም፤ 12እና​ን​ተም ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ይልቅ ክፉ አድ​ር​ጋ​ች​ኋል፤ እነ​ሆም ሁላ​ችሁ እንደ ክፉ ልባ​ችሁ ፍላ​ጎት ሄዳ​ች​ኋል፤ እኔ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁም። 13ስለ​ዚህ ከዚች ምድር እና​ን​ተና አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ አላ​ወ​ቃ​ች​ኋት ምድር እጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ምሕ​ረ​ትን ለማ​ያ​ደ​ር​ጉ​ላ​ችሁ ሌሎች አማ​ል​ክት ቀንና ሌሊት ታገ​ለ​ግ​ላ​ላ​ችሁ።”#ዕብ. “ምሕ​ረ​ት​ንም አላ​ደ​ር​ግ​ላ​ች​ሁ​ምና በዚያ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ቀንና ሌሊት ታመ​ል​ካ​ላ​ችሁ” ይላል።
ከም​ርኮ ስለ መመ​ለስ
14ስለ​ዚህ እነሆ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ያወጣ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዳግ​መኛ የማ​ይ​ባ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ 15ነገር ግን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሰ​ሜን ምድር፥ ከተ​ሰ​ደ​ዱ​በ​ትም ምድር ሁሉ ያወጣ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ይባ​ላል፤ እኔም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ሰጠ​ኋት ወደ ምድ​ራ​ቸው እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ።
ስለ​ሚ​መ​ጣው ቅጣት
16“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥ​ማ​ጆ​ችን እል​ካ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ያጠ​ም​ዱ​አ​ቸ​ዋል፤ ከዚ​ያም በኋላ ብዙ አድ​ዳ​ኞ​ችን እል​ካ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ከየ​ተ​ራ​ራ​ውና ከየ​ኮ​ረ​ብ​ታው ሁሉ ከየ​ድ​ን​ጋ​ዩም ስን​ጣቂ ውስጥ ያድ​ድ​ኑ​አ​ቸ​ዋል። 17ዐይ​ኖች በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ሁሉ ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ ከፊ​ቴም አል​ተ​ሰ​ወ​ሩም፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ከዐ​ይ​ኖች አል​ተ​ሸ​ሸ​ገም። 18ምድ​ሬ​ንም በተ​ጠሉ በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው#“በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ሬሳ​ዎች አር​ክ​ሰ​ዋ​ልና፥ ርስ​ቴ​ንም አስ​ጸ​ያፊ በሆኑ ነገ​ሮች ሞል​ተ​ዋ​ልና አስ​ቀ​ድሜ የበ​ደ​ላ​ቸ​ው​ንና የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።”
የኤ​ር​ም​ያስ ጸሎት
19ጌታ ሆይ! አንተ ኀይ​ሌና ረዳቴ፥ በመ​ከ​ራም ቀን መጠ​ጊ​ያዬ ነህ፤ ከም​ድር ዳርቻ አሕ​ዛብ ወደ አንተ መጥ​ተው፥ “በእ​ው​ነት አባ​ቶ​ቻ​ችን ውሸ​ት​ንና ከን​ቱን ነገር ለም​ንም የማ​ይ​ረ​ባ​ቸ​ውን ጣዖ​ትን ሠር​ተ​ዋል” ይላሉ። 20በውኑ ሰው አማ​ል​ክት ያል​ሆ​ኑ​ትን ለራሱ አማ​ል​ክ​ትን አድ​ርጎ ይሠ​ራ​ልን?
21“ስለ​ዚህ እነሆ በዚህ ወራት አስ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እጄ​ንና ኀይ​ሌ​ንም አሳ​ያ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ስሜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ ያው​ቃሉ።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ