የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 18:28-38

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 18:28-38 አማ2000

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ከቀ​ያፋ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ወሰ​ዱት፤ አይ​ሁድ ግን ፈጽሞ ስለ ነጋ የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ሳይ​በሉ እን​ዳ​ይ​ረ​ክሱ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ አል​ገ​ቡም። ጲላ​ጦ​ስም ወደ እነ​ርሱ ወደ ውጭ ወጥቶ፥ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመ​ጣ​ች​ሁ​በት በደሉ ምን​ድ​ነው?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “ክፉ የሠራ ባይ​ሆ​ንስ ወደ አንተ አሳ​ል​ፈን ባል​ሰ​ጠ​ነው ነበር” ብለው መለ​ሱ​ለት። ጲላ​ጦ​ስም፥ “እና​ንተ ወስ​ዳ​ችሁ እንደ ሕጋ​ችሁ ፍረ​ዱ​በት” አላ​ቸው፤ አይ​ሁ​ድም፥ “እኛስ ማን​ንም ልን​ገ​ድል አል​ተ​ፈ​ቀ​ደ​ል​ንም” አሉት። ይህም በምን ዐይ​ነት ሞት ይሞት ዘንድ እን​ዳ​ለው ሲያ​መ​ለ​ክት የተ​ና​ገ​ረው የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው። ጲላ​ጦ​ስም እን​ደ​ገና ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ገብቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ጠራና፥ “የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?” አለው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ይህን የም​ት​ና​ገር ከራ​ስህ ነውን? ወይስ ስለ እኔ የነ​ገ​ረህ ሌላ አለን?” ብሎ መለ​ሰ​ለት። ጲላ​ጦ​ስም መልሶ፥ “እኔ አይ​ሁ​ዳዊ ነኝን? ለእኔ አሳ​ል​ፈው የሰ​ጡህ ወገ​ኖ​ች​ህና ሊቃነ ካህ​ናት አይ​ደ​ሉ​ምን? Aረ ምን አድ​ር​ገ​ሃል?” አለው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእኔ መን​ግ​ሥት ከዚህ ዓለም አይ​ደ​ለ​ችም፤ መን​ግ​ሥ​ቴስ በዚህ ዓለም ብት​ሆን ኖሮ ለአ​ይ​ሁድ እን​ዳ​ል​ሰጥ አሽ​ከ​ሮች በተ​ዋ​ጉ​ልኝ ነበር፤ አሁ​ንም መን​ግ​ሥቴ ከዚህ አይ​ደ​ለ​ችም” ብሎ መለ​ሰ​ለት። ጲላ​ጦ​ስም፥ “እን​ግ​ዲያ አንተ ንጉሥ ነህን?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ራስህ ትላ​ለህ፤ እኔ ስለ​ዚህ ተወ​ለ​ድሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ለእ​ው​ነት ልመ​ሰ​ክር ወደ ዓለም መጣሁ፤ ከእ​ው​ነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰ​ማ​ኛል” አለው። ጲላ​ጦ​ስም፥ “እው​ነት ምን​ድ​ነው?” አለው፤ ይህ​ንም ተና​ግሮ ዳግ​መኛ ወደ አይ​ሁድ ወጣና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ አን​ዲት ስን​ኳን በደል አላ​ገ​ኘ​ሁ​በ​ትም።