የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 4

4
ወደ ገሊላ ስለ መሄዱ
1ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከዮ​ሐ​ንስ ይልቅ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን እንደ አበ​ዛና እን​ደ​ሚ​ያ​ጠ​ምቅ ፈሪ​ሳ​ው​ያን መስ​ማ​ታ​ቸ​ውን ዐወቀ። 2ነገር ግን ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እንጂ እርሱ ራሱ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ አላ​ጠ​መ​ቀም። 3የይ​ሁ​ዳ​ንም ምድር ትቶ ዳግ​መኛ ወደ ገሊላ ሄደ። 4በሰ​ማ​ርያ በኩ​ልም ሲያ​ልፍ ሳለ፥ 5#ዘፍ. 33፥19፤ ኢያ. 24፥32። ያዕ​ቆብ ለልጁ ለዮ​ሴፍ በሰ​ጠው በወ​ይን ቦታ አቅ​ራ​ቢያ ወደ አለ​ችው ሲካር ወደ​ም​ት​ባ​ለው የሰ​ማ​ርያ ከተማ ደረሰ። 6በዚ​ያም የያ​ዕ​ቆብ የውኃ ጕድ​ጓድ ነበረ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መን​ገድ በመ​ሄድ ደክሞ በዚያ ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ተቀ​መጠ፤ ጊዜ​ውም ስድ​ስት ሰዓት ያህል ነበር።
ስለ ሳም​ራ​ዊት ሴት
7እነሆ፥ ከሰ​ማ​ርያ አን​ዲት ሴት ውኃ ልት​ቀዳ መጣች፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ውኃ አጠ​ጪኝ” አላት። 8ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበ​ርና። 9#ዕዝ. 4፥1-5፤ ነህ. 4፥12። ያቺ የሰ​ማ​ርያ ሴትም፥ “አንተ አይ​ሁ​ዳዊ ስት​ሆን፥ እኔም ሳም​ራ​ዊት ስሆን እን​ዴት ከእኔ ዘንድ ውኃ ልት​ጠጣ ትለ​ም​ና​ለህ?” አለ​ችው፤ አይ​ሁድ ከሳ​ም​ራ​ው​ያን ጋር በሥ​ር​ዐት#“በሥ​ር​ዐት” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። አይ​ተ​ባ​በ​ሩም ነበ​ርና። 10ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦ​ታና ውኃ አጠ​ጪኝ#በግ​ሪኩ “ውኃ ስጪኝ” ይላል። ብሎ የሚ​ለ​ም​ንሽ ማን እንደ ሆነ ብታ​ው​ቂስ አንቺ ደግሞ በለ​መ​ን​ሺው ነበር፤ እር​ሱም የሕ​ይ​ወ​ትን ውኃ በሰ​ጠሽ ነበር” ብሎ መለ​ሰ​ላት። 11ያቺ ሴትም እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ መቅጃ እንኳ የለ​ህም፤ ጕድ​ጓ​ዱም ጥልቅ ነው፤ እን​ግ​ዲህ የሕ​ይ​ወት ውኃ ከወ​ዴት ታገ​ኛ​ለህ? 12ይህን ጕድ​ጓድ ከሰ​ጠን ከአ​ባ​ታ​ችን ከያ​ዕ​ቆብ አንተ ትበ​ል​ጣ​ለ​ህን? እር​ሱም #አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ሚስ​ቶ​ቹም” የሚል ይጨ​ም​ራል። ልጆ​ቹም፥ ከብ​ቶ​ቹም ከእ​ርሱ ጠጥ​ተ​ዋል።” 13ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “ከዚህ ውኃ የሚ​ጠጣ ሁሉ ዳግ​መኛ ይጠ​ማል። 14እኔ ከም​ሰ​ጠው ውኃ የሚ​ጠጣ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም፤ እኔ የም​ሰ​ጠው ውኃ በው​ስጡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የሚ​ፈ​ልቅ የውኃ ምንጭ ይሆ​ን​ለ​ታል እንጂ።” 15ሴቲ​ቱም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እን​ዳ​ል​ጠማ፥ ዳግ​መ​ኛም ውኃ ልቀዳ ወደ​ዚህ እን​ዳ​ል​መጣ እባ​ክህ ከዚህ ውኃ ስጠኝ፤” አለ​ችው።
16ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሂደሽ ባል​ሽን ጥሪና ወደ​ዚህ ነይ” አላት። 17ሴቲ​ቱም፥ “ባል የለ​ኝም” ብላ መለ​ሰ​ች​ለት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላት፥ “ባል የለ​ኝም በማ​ለ​ትሽ መል​ካም ተና​ገ​ርሽ። 18ቀድሞ አም​ስት ባሎች ነበ​ሩሽ፤ ዛሬ አብ​ሮሽ ያለው ግን ባልሽ አይ​ደ​ለም፤ ይህ​ንስ እው​ነት አልሽ።” 19ሴቲ​ቱም እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያ​ለሁ። 20አባ​ቶ​ቻ​ችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እና​ንተ ግን ይሰ​ግ​ዱ​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባው ስፍራ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነው ትላ​ላ​ችሁ።” 21ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት በዚህ ተራራ ወይም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ብቻ ለአብ የማ​ይ​ሰ​ግ​ዱ​በት ሰዓት እን​ደ​ም​ት​መጣ እመ​ኝኝ። 22እና​ንተ ለማ​ታ​ው​ቁት ትሰ​ግ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እኛ ግን ለም​ና​ው​ቀው እን​ሰ​ግ​ዳ​ለን፤ መድ​ኀ​ኒት ከአ​ይ​ሁድ ወገን ነውና። 23ነገር ግን በእ​ው​ነት የሚ​ሰ​ግዱ በመ​ን​ፈ​ስና በእ​ው​ነት ለአብ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ባት ጊዜ ትመ​ጣ​ለች፤ እር​ስ​ዋም አሁን ናት። አብ እን​ዲህ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ለ​ትን ይሻ​ልና። 24እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነውና፤ የሚ​ሰ​ግ​ዱ​ለ​ትም በመ​ን​ፈ​ስና በእ​ው​ነት ይሰ​ግ​ዱ​ለት ዘንድ ይገ​ባል።” 25ሴቲ​ቱም፥ “ክር​ስ​ቶስ የሚ​ሉት መሲሕ እን​ደ​ሚ​መጣ እና​ው​ቃ​ለን፤ እር​ሱም በሚ​መጣ ጊዜ ሁሉን ይነ​ግ​ረ​ናል” አለ​ችው። 26ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የማ​ነ​ጋ​ግ​ርሽ እኔ እርሱ ነኝ” አላት።
27በዚ​ያም ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ መጡ፤ ከሴት ጋርም ይነ​ጋ​ገር ነበ​ርና ተደ​ነቁ፤ ነገር ግን፥ “ምን ትሻ​ለህ? ወይስ ከእ​ር​ስዋ ጋር ለምን ትነ​ጋ​ገ​ራ​ለህ?” ያለው የለም። 28ሴቲ​ቱም እን​ስ​ራ​ዋን ትታ ወደ ከተማ ገባች፤ ለሰ​ዎ​ችም ነገ​ረች። 29“የሠ​ራ​ሁ​ትን ሁሉ የነ​ገ​ረ​ኝን ሰው ታዩ ዘንድ ኑ፤ እንጃ፥ እርሱ ክር​ስ​ቶስ ይሆን?” 30ከከ​ተ​ማም ወጥ​ተው ወደ እርሱ ሄዱ።
31በዚ​ህም ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ፥ “መም​ህር ሆይ፥ እህል ብላ” ብለው ለመ​ኑት። 32ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ የም​በ​ላው እና​ንተ የማ​ታ​ው​ቁት ምግብ አለኝ” አላ​ቸው። 33ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “አን​ዳች የሚ​በ​ላው ምግብ ያመ​ጣ​ለት ሰው ይኖር ይሆን?”#አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “... ወሚመ ዛቲ ብእ​ሲት” የሚል ይጨ​ም​ራል። ተባ​ባሉ። 34ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ኔስ መብል የላ​ከ​ኝን የአ​ባ​ቴን ፈቃድ አደ​ርግ ዘንድ፥ ሥራ​ው​ንም እፈ​ጽም ዘንድ ነው። 35እና​ንተ እስከ አራት ወር ድረስ መከር ይሆ​ናል የም​ትሉ አይ​ደ​ለ​ምን? እነሆ፥ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ዐይ​ና​ች​ሁን አንሡ፤ መከ​ሩም ሊደ​ርስ እንደ ገረጣ ምድ​ሩን ተመ​ል​ከቱ። 36አጫ​ጅም ዋጋ​ውን ያገ​ኛል፤ የሚ​ዘ​ራና የሚ​ያ​ጭ​ድም በአ​ን​ድ​ነት ደስ እን​ዲ​ላ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ፍሬን ይሰ​በ​ስ​ባል። 37አንዱ ይዘ​ራል፥ ሌላ​ውም ያጭ​ዳል የሚ​ለው ቃል በዚህ እው​ነት ሆኖ​አል። 38እኔም ያል​ደ​ከ​ማ​ች​ሁ​በ​ትን እን​ድ​ታ​ጭዱ ላክ​ኋ​ችሁ፤ ሌሎች ደከሙ፤ እና​ን​ተም በድ​ካ​ማ​ቸው ገባ​ችሁ።”
ስለ ሳም​ራ​ው​ያን
39“የሠ​ራ​ሁ​ትን ሁሉ ነገ​ረኝ” ብላ የመ​ሰ​ከ​ረ​ችው ሴት ስለ ነገ​ረ​ቻ​ቸ​ውም ከዚ​ያች ከሰ​ማ​ርያ ከተማ ብዙ​ዎች አመ​ኑ​በት። 40ሳም​ራ​ው​ያ​ንም ሁሉ ወደ እርሱ መጥ​ተው በእ​ነ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ኖር ማለ​ዱት፤ ሁለት ቀንም ያህል በዚያ ተቀ​መጠ። 41ስለ ቃሉም እጅግ ብዙ​ዎች አመ​ኑ​በት። 42ሴቲ​ቱ​ንም፥ “እኛ ራሳ​ችን ይህ በእ​ው​ነት የዓ​ለም መድ​ኀ​ኒት ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ሰም​ተ​ንና ተረ​ድ​ተን ነው እንጂ በአ​ንቺ ቃል ያመ​ን​በት አይ​ደ​ለም” አሏት።
ገሊ​ላ​ው​ያን እንደ ተቀ​በ​ሉት።
43ከሁ​ለት ቀንም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከዚያ ወጥቶ ወደ ገሊላ ሄደ። 44#ማቴ. 13፥57፤ ማር. 6፥4፤ ሉቃ. 4፥24። ነቢይ በገዛ ሀገሩ እን​ደ​ማ​ይ​ከ​ብር እርሱ ራሱ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መሰ​ከረ። 45#ዮሐ. 2፥23። ወደ ገሊ​ላም ደግሞ በገባ ጊዜ ገሊ​ላ​ው​ያን ሁሉ ተቀ​በ​ሉት፤ እነ​ርሱ ለበ​ዓል ሄደው ስለ ነበር በበ​ዓሉ ቀን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ምር አይ​ተው ነበ​ርና።
46 # ዮሐ. 2፥1-11። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ውኃ​ውን የወ​ይን ጠጅ ወደ አደ​ረ​ገ​በት የገ​ሊላ ክፍል ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ቃና ዳግ​መኛ ሄደ። በቅ​ፍ​ር​ና​ሆም ልጁ የታ​መ​መ​በት የን​ጉሥ ወገን የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤ 47እር​ሱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከይ​ሁዳ ወደ ገሊላ እንደ መጣ በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ ሄደ፤ ሊሞት ቀርቦ ነበ​ርና ወርዶ ልጁን ያድ​ን​ለት ዘንድ ለመ​ነው፤ 48ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ምል​ክ​ት​ንና ድንቅ ሥራን ካላ​ያ​ችሁ አታ​ም​ኑም” አለው። 49ያም የን​ጉሥ ወገን የሆነ ሰው፥ “አቤቱ፥ ልጄ ሳይ​ሞት ፈጥ​ነህ ውረድ” አለው። 50ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሂድ፤ ልጅ​ህስ ድኖ​አል” አለው፤ ያም ሰው፦ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በነ​ገ​ረው ቃል አምኖ ሄደ። 51ሲወ​ር​ድም አገ​ል​ጋ​ዮቹ ተቀ​በ​ሉ​ትና፥ “ልጅ​ህስ ድኖ​አል” ብለው ነገ​ሩት። 52የዳ​ነ​ባ​ትን ሰዓ​ቷ​ንም ጠየ​ቃ​ቸው፤ “ትና​ን​ትና በሰ​ባት ሰዓት ንዳዱ ተወው” አሉት። 53አባ​ቱም፥ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “ልጅህ ድኖ​አል” ባለ​በት ሰዓት እንደ ሆነች ዐወቀ፤ እር​ሱም፥ ቤተ ሰቦ​ቹም ሁሉ አመኑ። 54ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከይ​ሁዳ ወደ ገሊላ መጥቶ ያደ​ረ​ገው ሁለ​ተ​ኛው ተአ​ምር ይህ ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ