የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ዮናስ 2

2
ጸሎተ ዮናስ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዮና​ስን ይው​ጠው ዘንድ ታላቅ ዓሣ አን​በ​ሪን አዘዘ፤ ዮና​ስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣ አን​በ​ሪው ሆድ ውስጥ ነበረ። 2ዮና​ስም በዓሣ አን​በ​ሪው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አም​ላኩ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ፥
እን​ዲ​ህም አለ፦
3“በመ​ከ​ራዬ ሳለሁ ወደ አም​ላኬ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፤
በሲ​ኦ​ልም ሆድ ውስጥ የጩ​ኸ​ቴን ድምፅ ሰማኝ፤
ቃሌ​ንም አዳ​መ​ጥህ።#ግእዝ “ቃሌ​ንም አዳ​መጠ” ይላል።
4ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣል​ኸኝ፥#ግእዝ “... ጣለኝ ...” ይላል።
ፈሳ​ሾ​ችም ከበ​ቡኝ፤
ማዕ​በ​ል​ህና ሞገ​ድህ ሁሉ በላዬ ዐለፉ።
5እኔም፦ ከዐ​ይ​ንህ ፊት ተጣ​ልሁ፤
ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅ​ደ​ስህ ደግሞ እመ​ለ​ከ​ታ​ለ​ሁን? አልሁ።
6ውኃ እስከ ነፍሴ ድረስ ፈሰሰ፤
ጥልቁ ባሕር በዙ​ሪ​ያዬ ከበ​በኝ፤
7እነሆ ራሴ ወደ ታች ወደ ተራ​ሮች መሠ​ረት ወረደ፤
ከጥ​ንት ጀምሮ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችዋ ወደ ተዘጉ ምድር ወረ​ድሁ፤
አቤቱ ፈጣ​ሪዬ! ሕይ​ወቴ ጥፋት ሳያ​ገ​ኛት ወዳ​ንተ ትውጣ።
8ነፍሴ በዛ​ለ​ች​ብኝ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሰ​ብ​ሁት፤
ጸሎ​ቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅ​ደ​ስህ ትግባ።
9ከን​ቱ​ነ​ት​ንና ሐሰ​ትን የሚ​ጠ​ብቁ፤
ይቅ​ር​ታ​ቸ​ውን ትተ​ዋል።
10እኔ ግን ከም​ስ​ጋ​ናና ከኑ​ዛዜ ቃል ጋር እሠ​ዋ​ል​ሃ​ለሁ፤
የድ​ኅ​ነቴ አም​ላክ ሆይ! የተ​ሳ​ል​ሁ​ትን ለአ​ንተ እከ​ፍ​ላ​ለሁ።”
11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዓሣ አን​በ​ሪ​ውን አዘ​ዘው፤ እር​ሱም ዮና​ስን በየ​ብስ ላይ ተፋው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ