ትንቢተ ዮናስ 2
2
ጸሎተ ዮናስ
1እግዚአብሔርም ዮናስን ይውጠው ዘንድ ታላቅ ዓሣ አንበሪን አዘዘ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣ አንበሪው ሆድ ውስጥ ነበረ። 2ዮናስም በዓሣ አንበሪው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥
እንዲህም አለ፦
3“በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤
በሲኦልም ሆድ ውስጥ የጩኸቴን ድምፅ ሰማኝ፤
ቃሌንም አዳመጥህ።#ግእዝ “ቃሌንም አዳመጠ” ይላል።
4ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ፥#ግእዝ “... ጣለኝ ...” ይላል።
ፈሳሾችም ከበቡኝ፤
ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ ዐለፉ።
5እኔም፦ ከዐይንህ ፊት ተጣልሁ፤
ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁን? አልሁ።
6ውኃ እስከ ነፍሴ ድረስ ፈሰሰ፤
ጥልቁ ባሕር በዙሪያዬ ከበበኝ፤
7እነሆ ራሴ ወደ ታች ወደ ተራሮች መሠረት ወረደ፤
ከጥንት ጀምሮ መወርወሪያዎችዋ ወደ ተዘጉ ምድር ወረድሁ፤
አቤቱ ፈጣሪዬ! ሕይወቴ ጥፋት ሳያገኛት ወዳንተ ትውጣ።
8ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብሁት፤
ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ትግባ።
9ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ፤
ይቅርታቸውን ትተዋል።
10እኔ ግን ከምስጋናና ከኑዛዜ ቃል ጋር እሠዋልሃለሁ፤
የድኅነቴ አምላክ ሆይ! የተሳልሁትን ለአንተ እከፍላለሁ።”
11እግዚአብሔርም ዓሣ አንበሪውን አዘዘው፤ እርሱም ዮናስን በየብስ ላይ ተፋው።
Currently Selected:
ትንቢተ ዮናስ 2: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
ትንቢተ ዮናስ 2
2
ጸሎተ ዮናስ
1እግዚአብሔርም ዮናስን ይውጠው ዘንድ ታላቅ ዓሣ አንበሪን አዘዘ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣ አንበሪው ሆድ ውስጥ ነበረ። 2ዮናስም በዓሣ አንበሪው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥
እንዲህም አለ፦
3“በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤
በሲኦልም ሆድ ውስጥ የጩኸቴን ድምፅ ሰማኝ፤
ቃሌንም አዳመጥህ።#ግእዝ “ቃሌንም አዳመጠ” ይላል።
4ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ፥#ግእዝ “... ጣለኝ ...” ይላል።
ፈሳሾችም ከበቡኝ፤
ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ ዐለፉ።
5እኔም፦ ከዐይንህ ፊት ተጣልሁ፤
ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁን? አልሁ።
6ውኃ እስከ ነፍሴ ድረስ ፈሰሰ፤
ጥልቁ ባሕር በዙሪያዬ ከበበኝ፤
7እነሆ ራሴ ወደ ታች ወደ ተራሮች መሠረት ወረደ፤
ከጥንት ጀምሮ መወርወሪያዎችዋ ወደ ተዘጉ ምድር ወረድሁ፤
አቤቱ ፈጣሪዬ! ሕይወቴ ጥፋት ሳያገኛት ወዳንተ ትውጣ።
8ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብሁት፤
ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ትግባ።
9ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ፤
ይቅርታቸውን ትተዋል።
10እኔ ግን ከምስጋናና ከኑዛዜ ቃል ጋር እሠዋልሃለሁ፤
የድኅነቴ አምላክ ሆይ! የተሳልሁትን ለአንተ እከፍላለሁ።”
11እግዚአብሔርም ዓሣ አንበሪውን አዘዘው፤ እርሱም ዮናስን በየብስ ላይ ተፋው።