መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 11
11
ኢያሱ ኢያቢስንና ሌሎች ነገሥታትን ድል እንዳደረገ
1እንዲህም ሆነ፤ የአሶር ንጉሥ ኢያቢስ ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ማሮን#ዕብ. “ማዶን” ይላል። ንጉሥ ወደ ዮባብ፥ ወደ ስሚዖን#ዕብ. “ሺምሮን” ይላል። ንጉሥ፥ ወደ አዚፍም ንጉሥ፥ 2በመስዕም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ ሲዶና” ይላል። በተራራማው ሀገር ፥ በከነሬትም ዐዜብ በዓረባ፥ በቆላውም ባለ በፊናዶር ሸለቆ ወደ ነበሩ ነገሥታት፥ 3በምሥራቃዊ ባሕር ዳርቻ ወዳለው ወደ ከነዓናዊው፥ ወደ አሞሬዎናዊውም፥ ወደ ኬጤዎናዊውም፥ ወደ ፌርዜዎናዊውም፥ በተራራማውም ሀገር ወዳለው ወደ ኢያቡሴዎናዊው፥ በቆላማውና በመሴፋ ወዳለው ወደ ኤዌዎናዊዉም ላከ። 4እነርሱ፥ ከእነርሱም ጋር ሠራዊቶቻቸው#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ንጉሦቻቸው” ይላል። ሁሉ ብዛታቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆነው ወጡ፤ ፈረሶችና ሰረገሎችም እጅግ ብዙዎች ነበሩ። 5እነዚህም ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበው መጡ፤ እስራኤልንም በማሮን ውኃ አጠገብ አንድ ሆነው ተያያዙአቸው።
6እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “በእስራኤል ፊት ይሞቱ ዘንድ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፤ የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ” አለው። 7ኢያሱና ተዋጊዎች ሕዝብም ሁሉ በድንገት ወደ ማሮን ውኃ መጡባቸው፤ በተራራማውም ቦታ ወደቁባቸው። 8እግዚአብሔርም በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ መቱአቸውም፤ ወደ ታላቂቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴሮንም፥ በምሥራቅም በኩል ወዳለው ወደ ሞሳሕ ሸለቆ አሳደዱአቸው፤ ማንንም ሳያስቀሩ መቱአቸው። 9ኢያሱም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገባቸው፤ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ቈረጠ፤ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት አቃጠለ።
10በእነዚያም ወራት ኢያሱ ተመልሶ አሶርን ያዘ፤ ንጉሥዋንም በሰይፍ ገደለ፤ አሶርም አስቀድሞ የእነዚህ መንግሥታት ዋና ከተማ ነበረች። 11በእርስዋም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ገደሉ፤ እስትንፋስ ያላቸውንም ሁሉ ሳያስቀሩ ሁሉንም አጠፉአቸው፤ አሶርንም በእሳት አቃጠላት፤ 12የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው፥ ኢያሱ የእነዚህን መንግሥታት ከተሞች ሁሉ፥ ንጉሦቻቸውንም ሁሉ ያዘ፤ በሰይፍም መታቸው፤ ፈጽሞም አጠፋቸው። 13ከአቃጠሏት#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኢያሱ ከአቃጠላት” ይላል። ከአሶር ብቻ በቀር እስራኤል በየአውራጃቸው የነበሩትን ሌሎች ከተሞች ሁሉ አላቃጠሉም። 14የእስራኤልም ልጆች የእነዚህን ከተሞች ምርኮ ሁሉ፥ ከብቶቹንም ለራሳቸው ዘረፉ፤ ሰዎቹን ሁሉ ግን እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍ ስለት መቱአቸው፤ እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ አንድም አላስቀሩም። 15እግዚአብሔርም አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ ሙሴ ኢያሱን አዝዞት ነበር፤ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን ካዘዘው ሁሉ ምንም አላስቀረም።
ኢያሱ ሌሎችን ግዛቶች እንደ ያዘ
16ኢያሱም ያን ምድር ሁሉ፥ ተራራማውን፥ ደቡቡንም ሁሉ፥ የጎሶምንም ምድር ሁሉ ፥ ሜዳውንም፥ በምዕራብ በኩል ያለውንም፥ የእስራኤልንም ተራራማውንና ቆላውን ያዘ፤ 17እስከ ሴይርም ከሚያወጣው ከኤኬል ተራራ ጀምሮ ከአርሞንዔም ተራራ በታች እስከ ሊባኖስ ሜዳና እስከ በላጋድ ድረስ፤ ንጉሦቻቸውን ሁሉ ይዞ መታቸው፤ ገደላቸውም። 18ኢያሱም ብዙ ዘመን ከእነዚሁ ነገሥታት ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር። 19በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዎናውያን#“በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዎናውያን” የሚለው በዕብ. ብቻ። በቀር፤ እስራኤል ያልያዙት ከተማ አልነበረም፥#“ከእስራኤል ያልያዙት ከተማ አልነበረም” በግእዝና በግሪክ ሰባ. ሊ. ብቻ። ሁሉን በጦርነት ያዙ። 20እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ፥ ያጠፉአቸው ዘንድ እንዳይራሩላቸው ፈጽመው እንዲያጠፉአቸው፥ ከእስራኤል ጋር ይጋጠሙ ዘንድ ልባቸውን እንዲያደነድኑ እግዚአብሔር ልባቸውን አጸና።
21በዚያ ጊዜም ኢያሱ ሄደ፤ በተራራማውም ሀገር የሚኖሩ ኤናቃውያንን ከኬብሮንና ከዳቤር፥ ከአናቦትም፥ ከእስራኤልም ተራራ ሁሉ፥ ከይሁዳም ተራራ ሁሉ አጠፋቸው፤ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው። 22በጋዛ፥ በጌትም፥ በአዛጦንም ከቀሩት በቀር በእስራኤል መካከል ከኤናቃውያን ማንንም አላስቀረም። 23እግዚአብሔርም ለሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያሱም ለእስራኤል እንደ ክፍላቸው በየነገዳቸው ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፤ ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 11: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ