መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 12
12
ሙሴ ድል ያደረጋቸው ነገሥት
1የእስራኤልም ልጆች የመቱአቸው፥ ከአርኖንም ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ በኩል ያለውን ዓረባ ሁሉ በዮርዳኖስም ማዶ በፀሐይ መውጫ ያለውን ሀገራቸውን የወረሱአቸው የምድር ነገሥት እነዚህ ናቸው፤ 2በሐሴቦን የተቀመጠው፥ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ኢያቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፤ 3በምሥራቅም በኩል ያለውን ዓረባ እስከ ኬኔሬት ባሕር ድረስ፥ በአሴሞት መንገድ አጠገብ እስካለው እስከ ዓረባ ባሕር እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ በደቡብም በኩል ከፋስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለውን ምድር የገዛው የአሞሬዎናውያን ንጉሥ ሴዎን፤ 4ከረዓይት ወገን የቀረ፥ በአስጣሮትና በኤንድራይን የተቀመጠው፥ 5የአርሞንኤምን ተራራ፥ ካሴኪን፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌርጌሲና እስከ መከጢ ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ የገዛው የባሳን ንጉሥ ዐግ፤ 6የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ገደሉአቸው፤ የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች፥ ለጋድም ልጆች፥ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው።
ኢያሱ ድል ያደረጋቸው ነገሥት
7የእስራኤል ልጆችና ኢያሱ በሊባኖስ ቆላ፥ በበላጋድ ባሕር፥ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሴይር በሚደርስ በኬልኪ ተራራ የገደሉአቸው የከነዓን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የአሞሬዎን” ሲል፥ ዕብ. “የሀገር” ይላል። ነገሥት እነዚህ ናቸው። ኢያሱም ያችን ምድር ለእስራኤል ወገኖች ሰጣቸው። 8በተራራና በሜዳ በዓረባ፥ በአሴዶት በቆላው፥ በናጌብ፥ በኬጤዎንና በአሞሬዎን፥ በከናኔዎንና በፌርዜዎን፥ በኢያቡሴዎንና በኤዌዎን ያለ ርስታቸውን አወረሳቸው። 9የኢያሪኮ ንጉሥ፥ በቤቴል አጠገብ ያለችው የጋይ ንጉሥ፥ 10የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ 11የኢያሪሙት ንጉሥ፥ የለኪስ ንጉሥ፥ 12የኤላም ንጉሥ፥ የጋዜር ንጉሥ፥ 13የዳቤር ንጉሥ፥ የጋሴ ንጉሥ፥ 14የኤርሞት ንጉሥ፥ የዓራድ ንጉሥ፥ 15የልብና ንጉሥ፥ የዓዶላም ንጉሥ፥ 16የመቄዳ ንጉሥ፥ 17የኤጣፋድ ንጉሥ፥ 18የኦፌር ንጉሥ፥ 19የአፌጠቀሰሩት ንጉሥ፥ የአሶር ንጉሥ፥ 20የስሚዖን ንጉሥ፥ የመምሮት ንጉሥ፥ 21የአዚፍ ንጉሥ፥ የቃዴስ ንጉሥ፥ 22የዘቃክ ንጉሥ፥ የማርዶት ንጉሥ፥ በቀርሜሎስ የነበረ የዴቆም ንጉሥ፥ 23በፌናድር ክፍል የምትሆን የኤዶር ንጉሥ፥ በጋልያ ክፍል የምትሆን የሐጌ ንጉሥ፥ የቲርሣ ንጉሥ፥ 24እነዚህ ነገሥት ሁሉ ሃያ ዘጠኝ#ዕብ. “31 ነገሥታት” ይላል።ናቸው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 12: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ