የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 14

14
በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ያለው ርስት አከ​ፋ​ፈል
1የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ነ​ዓን ምድር የወ​ረ​ሱት ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርና የነዌ ልጅ ኢያሱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ነገድ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አለ​ቆች ያወ​ረ​ሱ​አ​ቸው ርስት ይህ ነው። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኢያሱ” ይላል። እጅ እን​ዳ​ዘዘ ለዘ​ጠኙ ነገ​ድና ለእ​ኩ​ሌ​ታው በየ​ር​ስ​ታ​ቸው በዕጣ አከ​ፋ​ፈ​ሉ​አ​ቸው። 3ለሁ​ለቱ ነገ​ድና ለእ​ኩ​ሌ​ታው ነገድ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ርስት አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም። 4የዮ​ሴፍ ልጆች ምና​ሴና ኤፍ​ሬም ሁለት ነገ​ዶች ነበሩ፤ ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ከሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው ከተ​ሞች ለእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው ከሚ​ሆን ማሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸ​ውና ከእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም በቀር በም​ድሩ ውስጥ ድርሻ አል​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውም። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረጉ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ተካ​ፈሉ።
ኬብ​ሮን ለካ​ሌብ እንደ ተሰ​ጠች
6የይ​ሁ​ዳም ልጆች በጌ​ል​ገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ቄኔ​ዛ​ዊ​ውም የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ አለው፥ “ለአ​ም​ላክ ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃ​ዴስ በርኔ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ታው​ቃ​ለህ። 7የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ምድ​ርን እሰ​ልል ዘንድ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ከኝ ጊዜ እኔ የአ​ርባ ዓመት ሰው ነበ​ርሁ፤ እኔም በልቡ የነ​በ​ረ​ውን ቃል መለ​ስ​ሁ​ለት። 8ከእኔ ጋር የወጡ ወን​ድ​ሞች ግን የሕ​ዝ​ቡን ልብ አስ​ካዱ፤ እኔ ግን አም​ላ​ኬን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሜ እከ​ተ​ለው ዘንድ ተመ​ለ​ስሁ። 9ሙሴም በዚያ ቀን፦ ‘አም​ላ​ኬን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽ​መህ ተከ​ት​ለ​ሃ​ልና እግ​ርህ የረ​ገ​ጠው ምድር ለአ​ን​ተና ለል​ጆ​ችህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በር​ግጥ ርስት ይሆ​ናል’ ብሎ ማለ። 10አሁ​ንም፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተ​ና​ገረ በኋላ፥ እስ​ራ​ኤል በም​ድረ በዳ ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተና​ገ​ረኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አርባ አም​ስት ዓመ​ታት በሕ​ይ​ወት አኖ​ረኝ፤ አሁ​ንም፥ እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማ​ንያ አም​ስት ዓመት ሆነኝ። 11ሙሴም በላ​ከኝ ጊዜ ጽኑዕ እንደ ነበ​ርሁ፥ ዛሬም ገና እን​ዲሁ ለመ​ዋ​ጋት ለመ​ው​ጣ​ትም ለመ​ግ​ባ​ትም ጽኑዕ ነኝ። 12አሁን እን​ግ​ዲህ በዚያ ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ይህን ተራ​ራማ ሀገር ስጠኝ፤ አንተ በዚያ ቀን ዔና​ቃ​ው​ያን፥ ታላ​ላ​ቆ​ችና የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ችም በዚያ እን​ዳሉ ሰም​ተህ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ረኝ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።”
13ኢያ​ሱም የቄ​ኔዝ ልጅ፥ የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌ​ብን ባረ​ከው፤ ኬብ​ሮ​ን​ንም ርስት አድ​ርጎ ሰጠው። 14ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ስለ ተከ​ተለ ኬብ​ሮን እስከ ዛሬ ለቄ​ኔ​ዛ​ዊው ለዮ​ፎኒ ልጅ ለካ​ሌብ ርስት ሆነች። 15የኬ​ብ​ሮ​ንም ስም አስ​ቀ​ድሞ የአ​ር​ቦቅ ከተማ ትባል ነበር፤ እር​ስ​ዋም የዔ​ና​ቃ​ው​ያን ዋና ከተማ ነበ​ረች። ምድ​ሪ​ቱም ከው​ጊያ ዐረ​ፈች።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ