የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 15

15
ለይ​ሁዳ ነገድ የተ​ሰጠ ርስት
1የይ​ሁ​ዳም ነገድ ድን​በር በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከኤ​ዶ​ም​ያስ ዳርቻ፥ ከጺን ምድረ በዳ ጀምሮ በዐ​ዜብ በኩል እስከ ቃዴስ ድረስ ነው። 2በደ​ቡ​ብም በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸው እስከ ጨው ባሕር ዳርቻ ወደ ሊባ እስ​ከ​ሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ነበረ። 3ከዚ​ያም በአ​ቅ​ረ​ቢን ዐቀ​በት ፊት ይሄ​ዳል፤ ወደ ጺንም ይወ​ጣል፤ በቃ​ዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ይወ​ጣል፤ በአ​ስ​ሮ​ንም በኩል ያል​ፋል፤ ወደ ሰራ​ዳም ይወ​ጣል፥ ወደ ቃዴስ ምዕ​ራ​ብም ይዞ​ራል። 4ወደ አጽ​ሞ​ንም ያል​ፋል፤ በግ​ብ​ፅም ሸለቆ በኩል ይወ​ጣል፤ የድ​ን​በ​ሩም መውጫ በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ፤ በደ​ቡብ በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸው ይህ ነው። 5በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸው እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮር​ዳ​ኖ​ስም ነበረ። በሰ​ሜ​ንም በኩል ያለው ድን​በር በዮ​ር​ዳ​ኖስ መጨ​ረሻ እስ​ካ​ለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበረ፤ 6ከዚ​ያም ድን​በ​ራ​ቸው ወደ ቤተ ገለ​ዓም ይወ​ጣል፤ በቤ​ት​ዓ​ረባ በሰ​ሜን በኩል ያል​ፋል፤ ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ወደ ሮቤል ልጅ ወደ ሊቶን ቢዮን ይወ​ጣል፤ 7ድን​በ​ሩም በአ​ኮር ሸለቆ አራ​ተኛ ክፍል ላይ ይወ​ጣል፤ በአ​ዱ​ሚን ዐቀ​በት ፊት ለፊት፥ በደ​ቡብ በኩል ወዳ​ለ​ችው ወደ ጌል​ገላ ይወ​ር​ዳል፤ ድን​በ​ሩም ወደ ፀሐይ ምንጭ ውኃ ያል​ፋል፤ መው​ጫ​ውም በሮ​ጌል ምንጭ አጠ​ገብ ነበረ፤ 8ድን​በ​ሩም በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ አጠ​ገብ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ​ም​ት​ባ​ለው ወደ ኢያ​ቡስ ወደ ደቡብ ወገን ይወ​ጣል፤ ድን​በ​ሩም በሰ​ሜን በኩል በራ​ፋ​ይም ሸለቆ ዳር ባለው በሄ​ኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በባ​ሕር በኩል ወዳ​ለው ተራራ ራስ ላይ ይወ​ጣል፤ 9ድን​በ​ሩም ከተ​ራ​ራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ይሄ​ዳል፤ ወደ ዔፍ​ሮ​ንም ተራራ ይደ​ር​ሳል፤ ወደ ኢያ​ሪም ከተማ ወደ በኣላ ይደ​ር​ሳል። 10ድን​በ​ሩም ከበ​ኣላ በባ​ሕር በኩል ያል​ፋል፤ ከዚ​ያም በኢ​ያ​ሪም ከተማ ደቡብ በኩ​ልና በኪ​ስ​ሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥ​ራ​ቱስ ድን​በር ያል​ፋል፤ በፀ​ሐይ ከተ​ማም ላይ ይወ​ር​ዳል፤ በሊ​ባም በኩል ያል​ፋል። 11ድን​በ​ሩም ወደ አቃ​ሮን ደቡብ ይወ​ጣል፤ ወደ ሰሜን ወገን ይመ​ለ​ሳል፤ ድን​በሩ ወደ ሰቆት ይወ​ጣል፤ ወደ ደቡ​ብም ያል​ፋል፤ በሌ​ብና በኩ​ልም ይወ​ጣል፤ የድ​ን​በ​ሩም መውጫ በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ። 12በባ​ሕር በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸ​ውም እስከ ታላቁ ባሕ​ርና እስከ ዳር​ቻው ድረስ ነበረ። ለይ​ሁዳ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው በዙ​ሪ​ያው ያለ ድን​በ​ራ​ቸው ይህ ነው።
ካሌብ ኬብ​ሮ​ን​ንና ዳቤ​ርን እንደ ያዘ
(መሳ. 1፥11-15)
13በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ለዮ​ፎኒ ልጅ ለካ​ሌብ በይ​ሁዳ ልጆች መካ​ከል ድር​ሻ​ውን ሰጠው፤ ኢያ​ሱም የዔ​ናቅ#ዕብ. “አር​ቦ​ቅን የኤ​ናቅ አባት” ይላል። ዋና ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን የአ​ር​ቦ​ቅን ከተማ ሰጠው። እር​ስ​ዋም ኬብ​ሮን ናት። 14የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌ​ብም ሦስ​ቱን የዔ​ና​ቅን ልጆች ሱሲን፥ ተለ​ሚ​ንና አካ​ሚን ከዚያ አጠ​ፋ​ቸው። 15ከዚ​ያም ካሌብ በዳ​ቤር ሰዎች ላይ ዘመተ፤ የዳ​ቤ​ርም ስም አስ​ቀ​ድሞ “ሀገረ መጻ​ሕ​ፍት” ነበረ። 16ካሌ​ብም፥ “ሀገረ መጻ​ሕ​ፍ​ትን ለሚ​መታ፥ ለሚ​ይ​ዛ​ትም ልጄን አክ​ሳን#ግእዙ “አስካ” ይላል። ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ” አለ። 17የካ​ሌብ ወን​ድም የቄ​ኔዝ ልጅ ጎቶ​ን​ያል ያዛት፤ ልጁን አክ​ሳ​ንም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው። 18እር​ስ​ዋም ወደ እርሱ በመ​ጣች ጊዜ “አባ​ቴን እርሻ ልለ​ም​ነው” ብላ አማ​ከ​ረ​ችው፤ እር​ስ​ዋም በአ​ህ​ያዋ ላይ ሆና ጮኸች፤ ካሌ​ብም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት። 19እር​ስ​ዋም፥ “በረ​ከ​ትን ስጠኝ፤ በደ​ቡብ በኩል ያለ​ውን ምድር ሰጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና አሁን ደግሞ የው​ኃ​ውን ምን​ጭ ስ​ጠኝ” አለ​ችው። እር​ሱም የላ​ይ​ኛ​ው​ንና የታ​ች​ኛ​ውን ምንጭ ሰጣት።
የይ​ሁዳ ነገድ ርስት
20በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም የይ​ሁዳ ልጆች ነገድ ርስት ይህ ነው።
21በደ​ቡ​ብም በኩል በም​ድ​ራ​ቸው ዳርቻ እስከ ኤዶ​ም​ያስ ድን​በር ያሉት የይ​ሁዳ ልጆች ነገድ ከተ​ሞች እነ​ዚህ ነበሩ፤ ቤሴ​ሌ​ኤል፥ አራ፥ አሦር፤ 22ኤቃም፥ ሬግማ፥ አሩ​ሔል፤ 23ቃዴስ፥ አሶ​ር​ዮ​ስም፤ ሚናን፤ 24በል​ማ​ንና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም፤ 25የአ​ሴ​ሮም ከተ​ሞች እር​ስ​ዋም አሶር ናት። 26ሲን፥ ሰላ​ማዓ፥ ሞላዳ፤ 27ሴሪ፥ ቤፋ​ላድ፤ 28ኮላ​ሴ​ዎል፥ ቤር​ሳ​ቤ​ሕና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው። 29ባላ፥ ባቆ​ብና አሶም፤ 30ኤለ​ቦ​ሂ​ዳድ፥ ቤቴ​ልና ኤር​ማም፤ 31ሴቄ​ላቅ፥ ማኬ​ሪ​ምር፥ ሴቱ​ናቅ፤ 32ላቦስ ሳሌ፥ ኤር​ሞ​ትም ሃያ ዘጠኝ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።
33በቆ​ላው፥ አስ​ጣል፥ ሳራዓ፥ አሳ፤ 34ራሜ፥ ጣኖ፥ ኢዱ​ቶት፥ መሐ​ንስ፤ 35ኤር​ሙት፥ ኤዶ​ላም፥ ሜም​ብራ፥ ሰአክ፥ አዚቃ፤ 36ሴቃ​ርም፥ ጋዴ​ርና ሰፈ​ሮ​ችዋ፥ ዐሥራ አራት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።
37ሴና፥ አዳ​ሶን፥ ማጋ​ዳ​ል​ጋድ፤ 38አዶ​ላል፥ መሴፋ፥ ይቃ​ሩል፥ ለኪስ፤ 39በሴ​ዶት ይዴሃ፥ ደል​ያም፤ 40ኮብራ፥ ማኬስ፥ መሐ​ኮ​ስም፤ 41ጌዶር፥ በጋ​ድ​ያል፥ ኖማን፥ መቄ​ዶም፥ ዐሥራ ስድ​ስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።
42ሌምና፥ ኤተቅ፥ አኖክ፥ 43ኢድና ናሲ​ብም፤ 44ኤላም፥ አቁ​ዛም፥ ኬዜብ ቴርሳ፥ ኤሎ​ምም፥ ዐሥር ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።
45አቃ​ሮን ከመ​ን​ደ​ሮ​ች​ዋና ከመ​ሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ችዋ ጋር። 46ከአ​ቃ​ሮ​ንና ከጌ​ምና ጀምሮ በአ​ሴ​ዶት አቅ​ራ​ቢያ ያሉ ሁሉና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው፤
47አሴ​ያ​ዶት መን​ደ​ሮ​ች​ዋና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም፥ ጋዛም መን​ደ​ሮ​ች​ዋና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ፥ ታላቁ ባሕ​ርም ወሰኑ ነው።
48የሳ​ምር ተራ​ራ​ዎች ፥ ኢዩ​ቴር፥ ሦካ፤ 49ሬና፥ የመ​ጽ​ሐፍ ሀገር የሆ​ነች ዳቤር፤ 50አኖን፥ ሴቄማ፥ ኤሳ​ማም፤ 51ጎሶም ከሉም፥ ከናም፥ ዐሥራ አንድ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።
52ኤሬም፥ ሬምና፥ ሶማ፤ 53ኢያ​ማ​ይን፥ ቤታ​ቁም፥ ፋቁሕ፤ 54ኤውማ፥ የአ​ር​ቦቅ ከተማ እር​ስ​ዋም ኬብ​ሮን ናት፥ ሶሬት፥ ዘጠኝ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው። 55ማሖር፥ ኬር​ሜል፥ አዚብ፥ ኢጣን፤ 56ኢያ​ሬ​ዬል፥ ኢያ​ሪ​ቅም፥ ዘቃ​ይ​ንም፤ 57ጋባ፥ ተምና፥ ዘጠኝ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።
58አሌዋ፥ ቤተ​ሱር፥ ጌዶር፤ 59ማዕ​ራት፥ ቤት​አ​ኖት፥ ኤል​ት​ቆን፥ ስድ​ስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።
60ቴቆ፥ ኤፍ​ራታ፥ ይኽ​ች​ውም ቤተ ልሔም ናት፤ ፋጎ​ርም፥ ኤጣ​ንም፥ ቁሎን፥ ጠጦ​ንም፥ ሶብ​ሄም፥ ቃሬም፥ ጌሌም፥ ኤቴር፥ መነ​ኮም፥ ዐሥራ አንድ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው፥ ቅር​ያ​ት​በ​ኣል፥ ይኽ​ች​ውም የኢ​ያ​ርም ከተማ ናት፤ ሶቤታ፥ ሁለቱ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።
61ባዳ​ር​ጊስ፥ ተራ​ብ​ዐ​ምም፥ ኤኖን፤ ሴኬ​ዎ​ዛን፥ 62ናፍ​ላ​ዛ​ንና ከተ​ሞ​ቻ​ቸው፥ ሳዶን፥ አቃ​ዴስ፥ ሰባት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።
63በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ግን የይ​ሁዳ ልጆች ሊያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ቸው አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም፤ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም እስከ ዛሬ ድረስ በይ​ሁዳ ልጆች መካ​ከል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ