መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 16
16
ለኤፍሬምና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ የተሰጠ ርስት
1የዮሴፍም ልጆች ድንበራቸው በኢያሪኮ አንጻር በምሥራቅ በኩል ካለው ከዮርዳኖስ አንሥቶ በምድረ በዳውና በተራራማው በኩል ከኢያሪኮ ሎዛ ትባል ወደ ነበረችው ቤቴል ይደርሳል፤ 2ከቤቴል ሎዛም በከሮንቲ ዳርቻ በኩል ወደ አጣሮት አውራጃ ይደርሳል፤ 3ወደ ምዕራብም እስከ የፍሌጣውያን ዳርቻ እስከ ታችኛው ቤቶሮን ዳርቻ ድረስ ይወርዳል፤ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። 4የዮሴፍም ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን ወረሱ።
የኤፍሬም ልጆች ርስት
5የኤፍሬምም ልጆች ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፤ የርስታቸው ድንበር ከአጣሮትና፥ ከኤሮሕ ምሥራቅ ከጋዛራ እስከ ላይኛው ቤቶሮን ድረስ ነበረ፤ 6ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አካስሞን በቴርማ ሰሜን ያልፋል፤ ወደ ምሥራቅም ወደ ቲናስና ሴላስ ይዞራል፥ ከምሥራቅም ወደ ኢያኖክ ያልፋል። 7ከኢያኖክም ወደ መአኮና፥ ወደ አጣሮትም፥ ወደ መንደሮቻቸውም ያልፋል፤ ወደ ኢያሪኮም ይገባል፥ ወደ ዮርዳኖስም ይወጣል። 8ድንበሩም ከጣፉ ወደ ባሕር እስከ ኬልቃን ወንዝ ድረስ ያልፋል፥ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። የኤፍሬም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። 9ይኸውም በምናሴ ልጆች ርስት መካከል ለኤፍሬም ልጆች ከተለዩ ከተሞች ጋር፥ ከተሞች ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር ነው። 10በጋዜርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን ኤፍሬም አላጠፋቸውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ ገባርም ሆኑ።#“ገባርም ሆኑ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ነገር ግን የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ወጥቶ እስከ ያዛትና በእሳት እስከ አቃጠላት ድረስ ከነዓናውያንንና ፌርዜዎናውያንን በጋዛ የሚኖሩትንም እስከ አጠፋ ድረስ፤ እርሷንም ፈርዖን ለሴት ልጁ ለማጫ ሰጣት፥ የሚለውን ይጨምራል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 16: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ