የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 17

17
የም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ርስት
1የም​ናሴ ልጆች ነገድ ድን​በር ይህ ነው፤ የዮ​ሴፍ በኵር እርሱ ነውና። የም​ና​ሴም በኵር የገ​ለ​ዓድ አባት ማኪር ብርቱ ተዋጊ ስለ ነበረ ገለ​ዓ​ድ​ንና ባሳ​ንን ወረሰ። 2ዕጣ​ውም ለቀ​ሩት ለም​ናሴ ልጆች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው፥ ለኢ​ያ​ዜር ልጆች፥ ለቄ​ሌዝ ልጆች፥ ለኢ​የ​ዚ​ኤል ልጆች፥ ለሴ​ኬም ልጆች፥ ለሱ​ማ​ሪም ልጆች፥ ለኦ​ፌር ልጆች ሆነ፤ ወን​ዶቹ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው። 3ለኦ​ፌር ልጅ፥ ለሰ​ለ​ጰ​ዓድ ግን ሴቶች ልጆች እንጂ ወን​ዶች ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም፤ የሰ​ለ​ጰ​ዐ​ድም የሴ​ቶች ልጆቹ ስሞች፦ መሐላ፥ ኑዓ፥ ሔግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበሩ። 4እነ​ር​ሱም ወደ ካህኑ ወደ አል​ዓ​ዛ​ርና ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ አለ​ቆ​ችም ቀር​በው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን መካ​ከል ርስት እን​ዲ​ሰ​ጠን በሙሴ እጅ አዘዘ” አሉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ከአ​ባ​ታ​ቸው ወን​ድ​ሞች ጋር ርስት ሰጣ​ቸው። 5ዕጣ​ቸ​ውም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ከአ​ለው ከገ​ለ​ዓ​ድና ከባ​ሳን ሀገር በቀር ለም​ናሴ ዐሥር ዕጣ ሆነ፤ 6የም​ናሴ ሴቶች ልጆች በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል ርስት ተቀ​ብ​ለ​ዋ​ልና፤ የገ​ለ​ዓ​ድም ምድር ለቀ​ሩት ለም​ናሴ ልጆች ሆኖ​አ​ልና።
7የም​ና​ሴም ልጆች ድን​በር በሐ​ነት ልጆች ፊት ያለው ዴላ​ናታ ነው። በኢ​ያ​ሚ​ንና በኢ​ያ​ሲብ ድን​በር በተ​ፍ​ቶት ምንጭ ላይ ያል​ፋል። 8የጣ​ፌት ምድር ለም​ናሴ ነበረ፤ ጣፌት ግን በኤ​ፍ​ሬም ልጆ​ችና በም​ናሴ ልጆች አው​ራጃ ያለ ነው። 9ድን​በ​ራ​ቸ​ውም በደ​ቡብ በኩል ወዳ​ለው ወደ ቃራና ሸለ​ቆና ወደ ኢያ​ሪ​ያል ሸለቆ ይወ​ር​ዳል፤ የኤ​ፍ​ሬም ዕጣ የሆ​ነው ጤሬ​ሜ​ን​ቶስ የሚ​ባ​ለው ዛፍም በም​ናሴ ከተ​ሞች መካ​ከል አለ፤ የም​ና​ሴም ድን​በር በሰ​ሜን በኩል ወደ ወንዙ ይወ​ር​ዳል፤ መው​ጫ​ውም በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ። 10በደ​ቡብ በኩል ያለው ለኤ​ፍ​ሬም ነበረ፤ በሰ​ሜን በኩል ያለ​ውም ለም​ናሴ ነበረ፤ ድን​በ​ሩም ባሕር ነበረ፤ በሰ​ሜን በኩል ወደ አሴር፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወደ ይሳ​ኮር ይደ​ር​ሳል። 11በይ​ሳ​ኮ​ርና በአ​ሴር መካ​ከል ቤት​ሳ​ንና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ዶርና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ መጌ​ዶና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ የመ​ፌታ ሦስ​ተኛ እጅና መን​ደ​ሮ​ችዋ ለም​ናሴ ነበሩ። 12የም​ናሴ ልጆ​ችም የእ​ነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ሰዎች ማጥ​ፋት ተሳ​ና​ቸው፤ ነገር ግን ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በዚ​ያች ሀገር ለመ​ቀ​መጥ መጡ። 13የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በረ​ቱ​ባ​ቸው፤ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ገዙ​አ​ቸው፤ ነገር ግን ፈጽ​መው አላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም።
የኤ​ፍ​ሬ​ምና የም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ተጨ​ማሪ ርስት መጠ​የ​ቃ​ቸው
14የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ኢያ​ሱን፥ “እኛ ብዙ ሕዝብ ስን​ሆን እስከ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ባረ​ከን ለምን አንድ ክፍል፥ አን​ድም ዕጣ ብቻ ርስት አድ​ር​ገህ ሰጠ​ኸን?” ብለው ወቀ​ሱት። 15ኢያ​ሱም፥ “ብዙ ሕዝብ ከሆ​ና​ችሁ፥ ተራ​ራ​ማው የኤ​ፍ​ሬም ሀገ​ርም ከጠ​በ​ባ​ችሁ ወደ ዱር ወጥ​ታ​ችሁ መን​ጥ​ራ​ችሁ አቅ​ኑ​አት” አላ​ቸው። 16እነ​ር​ሱም፥ “ተራ​ራ​ማው የኤ​ፍ​ሬም ሀገር አይ​በ​ቃ​ንም፤ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ለሚ​ኖ​ሩት፥ በቤ​ት​ሳ​ንና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ልም ሸለቆ ለሚ​ኖ​ሩት ከነ​ዓ​ና​ው​ያን የተ​መ​ረጡ ፈረ​ሶ​ችና ሰይፍ አሏ​ቸው” አሉት። 17ኢያ​ሱም ለዮ​ሴፍ ልጆች፥ “እና​ንተ ብዙ ሕዝብ ከሆ​ና​ችሁ፥ ጽኑ ኀይ​ልም ከአ​ላ​ችሁ አንድ ዕጣ ብቻ አይ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁም፤ 18ነገር ግን ተራ​ራ​ማው ሀገር ለእ​ና​ንተ ይሆ​ናል፤ ዱር እንኳ ቢሆ​ንም ትመ​ነ​ጥ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለእ​ና​ን​ተም ይሆ​ናል፤ ለከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም የተ​መ​ረጡ ፈረ​ሶ​ችና የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች ቢሆ​ኑ​ላ​ቸው፥ የበ​ረቱ ቢሆ​ኑም እና​ንተ እስ​ክ​ታ​ጠ​ፉ​አ​ቸው ድረስ ትበ​ረ​ቱ​ባ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ