የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 22

22
ኢያሱ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የመ​ጡ​ትን እን​ዳ​ሰ​ና​በተ
1በዚ​ያን ጊዜም ኢያሱ የሮ​ቤ​ልን ልጆ​ችና የጋ​ድን ልጆች የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ ጠርቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፦ 2“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ ሰም​ታ​ች​ኋል፤ እኔም ላዘ​ዝ​ኋ​ችሁ ነገር ሁሉ ታዝ​ዛ​ች​ኋል፤ 3ይህ​ንም ያህል ብዙ ጊዜ እስከ ዛሬ ድረስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አል​ተ​ዋ​ች​ሁም፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ጠብ​ቃ​ች​ኋል። 4አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ራ​ቸው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አሳ​ር​ፎ​አ​ቸ​ዋል፤ አሁን እን​ግ​ዲህ ተመ​ለሱ፤ ወደ ቤታ​ች​ሁና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሰጣ​ችሁ ወደ ርስ​ታ​ችሁ ምድር ሂዱ። 5ብቻ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሕጉን ታደ​ርጉ ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትወ​ድዱ ዘንድ፥ መን​ገ​ዱ​ንም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ትጠ​ብቁ ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ትከ​ተሉ ዘንድ፥ በፍ​ጹ​ምም ልባ​ችሁ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ታመ​ል​ኩት ዘንድ እጅግ ተጠ​ን​ቀቁ።” 6ኢያ​ሱም መረ​ቃ​ቸው፤ አሰ​ና​በ​ታ​ቸ​ውም፤ ወደ ቤታ​ቸ​ውም ሄዱ።
7ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ሙሴ በባ​ሳን ውስጥ ርስት ሰጥ​ቶ​አ​ቸው ነበር፤ ለቀ​ረው ለእ​ኩ​ሌ​ታው ግን ኢያሱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር በኩል በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል ርስት ሰጣ​ቸው። ኢያ​ሱም ወደ ቤታ​ቸው በአ​ሰ​ና​በ​ታ​ቸው ጊዜ እን​ዲህ ብሎ መረ​ቃ​ቸው፦ 8“በብዙ ብል​ጥ​ግና፥ በእ​ጅ​ግም ብዙ ከብት፥ በብ​ርም፥ በወ​ር​ቅም፥ በና​ስም፥ በብ​ረ​ትም፥ በእ​ጅ​ግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ የጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ምርኮ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ጋር ተካ​ፈሉ።”
9የሮ​ቤ​ልም ልጆች የጋ​ድም ልጆች የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ሄዱ፤ በሙ​ሴም እጅ በተ​ሰጠ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ወደ ተቀ​በ​ሉት ወደ ርስ​ታ​ቸው ወደ ገለ​ዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ በከ​ነ​ዓን ምድር ካለ​ችው ከሴሎ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ተመ​ለሱ።
በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ የተ​ሠራ መሠ​ዊያ
10በከ​ነ​ዓን ምድር ወዳ​ለው ወደ ዮር​ዳ​ኖስ አቅ​ራ​ቢ​ያም ወደ ገለ​ዓድ በመጡ ጊዜ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ በዚያ በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ የሚ​ታይ ታላቅ መሠ​ዊያ ሠሩ። 11የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ነ​ዓን ምድር ዳርቻ በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ ባለው በገ​ለ​ዓድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ባሉ​በት ወገን፥ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ መሠ​ዊያ እንደ ሠሩ ሰሙ። 12የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ይህን በሰሙ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ወጥ​ተው እነ​ር​ሱን ሊዋጉ በሴሎ ተሰ​በ​ሰቡ።
13የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በገ​ለ​ዓድ ምድር ወዳ​ሉት ወደ ሮቤል ልጆ​ችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የካ​ህኑ የአ​ሮ​ንን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛ​ርን ልጅ ፊን​ሐ​ስን ላኩ። 14ዐሥር አለ​ቆ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ አንድ አንድ የእ​የ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት አለቃ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በእ​ስ​ራ​ኤል አእ​ላ​ፋት መካ​ከል የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት አለቃ ነበረ። 15በገ​ለ​ዓ​ድም ምድር ወዳ​ሉት ወደ ሮቤል ልጆ​ችና ወደ ጋድ ልጆች፥ ወደ ምና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ደረሱ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው 16የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር ሁሉ የሚ​ለው ይህ ነው፥ “ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መከ​ተ​ልን ትተዉ ዘንድ፥ መሠ​ዊ​ያም ትሠሩ ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ዛሬ ትክ​ዱት ዘንድ ይህ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ፊት ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ኀጢ​አት ምን​ድን ነው? 17እኛ እስከ ዛሬ ድረስ ከእ​ርሱ ያል​ነ​ጻ​ን​በት የፌ​ጎር ኀጢ​አት ጥቂት ነውን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር ላይ መቅ​ሠ​ፍት ወረደ። 18እና​ንተ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መከ​ተ​ልን ትታ​ች​ኋል፤ ዛሬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ብታ​ምፁ ነገ በእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ላይ መቅ​ሠ​ፍት ይሆ​ናል። 19ነገር ግን የር​ስ​ታ​ችሁ ምድር ቢያ​ን​ሳ​ችሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ወደ​ሚ​ቀ​መ​ጥ​በት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ምድር አል​ፋ​ችሁ ከእኛ ጋር ውረሱ፤ ከአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ውጭ ለእ​ና​ንተ መሠ​ዊያ ሠር​ታ​ች​ኋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​ካዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አት​ተ​ዉት። 20የዛራ ልጅ አካን እርም ነገር በመ​ው​ሰድ ኀጢ​አ​ትን ስለ ሠራ በእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ላይ ቍጣ አል​ወ​ረ​ደ​ምን? እር​ሱም ብቻ​ውን ቢበ​ድል በኀ​ጢ​አቱ ብቻ​ውን ሞተን?”
21የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ለእ​ስ​ራ​ኤል አእ​ላ​ፋት አለ​ቆች እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ላ​ቸው፦ 22“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነው፤ ጌታም ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ#“የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ነው፤ እርሱ ያው​ቃል። እስ​ራ​ኤ​ልም ያው​ቀ​ዋል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ግ​ነው ለበ​ደ​ልና ለመ​ካድ ከሆነ ዛሬ አያ​ድ​ነን፤ 23አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ድ​ን​ክ​ደው፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ልን ቍር​ባን እን​ድ​ና​ሳ​ር​ግ​በት፥ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት እን​ድ​ና​ቀ​ር​ብ​በት መሠ​ዊያ ሠር​ተን እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ራሱ ይመ​ራ​መ​ረን፤ 24ይል​ቁ​ንም ከል​ባ​ችን ፍር​ሀት የተ​ነሣ፦ ነገ ልጆ​ቻ​ችሁ ልጆ​ቻ​ች​ንን፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ምን አላ​ችሁ? እን​ዳ​ይ​ሉ​አ​ቸው ስለ​ፈ​ራን ይህን የሠ​ራ​ነው ካል​ሆነ፥ እና​ንተ የሮ​ቤ​ልና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ፥ 25እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኛና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ዮር​ዳ​ኖ​ስን ድን​በር አድ​ር​ጎ​አ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ዕድል ፋንታ የላ​ች​ሁም ይሉ​አ​ቸ​ዋል፤ በዚ​ሁም ልጆ​ቻ​ችሁ ልጆ​ቻ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከማ​ም​ለክ እን​ዳ​ያ​ወ​ጡ​አ​ቸው ብለን ይህን አደ​ረ​ግን። 26ስለ​ዚ​ህም መሠ​ዊያ እን​ሥራ አልን፤ ነገር ግን ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ወይም ለቍ​ር​ባን አይ​ደ​ለም፤ 27ነገር ግን በእ​ኛና በእ​ና​ንተ መካ​ከል፥ ከእ​ኛም በኋላ በት​ው​ል​ዳ​ች​ንና በት​ው​ል​ዳ​ችሁ መካ​ከል በሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና በቍ​ር​ባን፥ በደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ልክ ዘንድ፥ ነገ ልጆ​ቻ​ችሁ ልጆ​ቻ​ች​ንን፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ዕድል ፋንታ የላ​ች​ሁም እን​ዳ​ይሉ ምስ​ክር ይሆ​ናል። 28ኋላ ይህ በተ​ደ​ረገ ጊዜ ነገ ለእኛ ወይም ለት​ው​ል​ዳ​ችን ይህን ሲሉ፥ እኛ፦ እነሆ፥ አባ​ቶ​ቻ​ችን ያደ​ረ​ጉ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሠ​ዊያ ምሳሌ እዩ፤ በእ​ኛና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምስ​ክር ነው እንጂ ስለ​ሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ስለ ቍር​ባን አይ​ደ​ለም እን​ላ​ለን። 29በድ​ን​ኳኑ ፊት ካለው ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሌላ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ለሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕት፥ ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ትም የሚ​ሆን መሠ​ዊ​ያን የሠ​ራ​ነው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ በማ​መፅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ዛሬ መከ​ተ​ልን ለመ​ተው በማ​ለት እንደ ሆነ ይህ ከእኛ ይራቅ።”
30ካህኑ ፊን​ሐ​ስና የማ​ኅ​በሩ አለ​ቆች፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት የእ​ስ​ራ​ኤል መሳ​ፍ​ንት ሁሉ ፥ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የተ​ና​ገ​ሩ​ትን ቃል በሰሙ ጊዜ ዝም አሉ፤ ደስም አሰ​ኛ​ቸው። 31የካ​ህ​ኑም የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ ለሮ​ቤል ልጆ​ችና ለጋድ ልጆች ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ፥ “ይህን መተ​ላ​ለፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን እን​ዳለ ዛሬ እና​ው​ቃ​ለን፤ አሁን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ አድ​ና​ች​ኋል” አላ​ቸው። 32የካ​ህ​ኑም የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ ከእ​ር​ሱም ጋር የማ​ኅ​በሩ አለ​ቆች ከሮ​ቤል ልጆ​ችና ከጋድ ልጆች፥ ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ዘንድ ከገ​ለ​ዓድ ሀገር ወደ ከነ​ዓን ሀገር ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ለሱ፤ ወሬም አመ​ጡ​ላ​ቸው። 33ነገ​ሩም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ደስ አሰኘ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በነ​ገ​ሩ​አ​ቸው ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ፤ ከዚ​ያም ወዲያ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ለመ​ው​ጋት አን​ወ​ጣም ተባ​ባሉ። 34ኢያ​ሱም መሠ​ዊ​ያ​ውን “የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ምስ​ክር” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው እንደ ሆነ ይህ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ምስ​ክር ነውና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ