መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 21
21
ለሌዋውያን የተሰጡ ከተሞች
1የሌዊ ልጆች አለቆች ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ እስራኤልም ሕዝብ አባቶች ነገዶች አለቆች መጡ፤ 2በከነዓን ምድር ባለችው በሴሎ፥ “እግዚአብሔር በሙሴ እጅ የምንቀመጥባቸውን ከተሞች፥ ለከብቶቻችንም መሰማሪያዎች ትሰጡን ዘንድ አዝዞአል” ብለው ተናገሩአቸው። 3የእስራኤልም ልጆች እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ከርስታቸው እነዚህን ከተሞችና መሰማርያቸውን ለሌዋውያን ሰጡአቸው።
4ለቀዓትም ወገኖች ልጆች ዕጣ ወጣ፤ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ከይሁዳ ነገድ፥ ከስምዖንም ነገድ፥ ከብንያምም ነገድ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተሰጡአቸው።
5ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከኤፍሬም ነገድ፥ ከዳንም ነገድ፥ ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተሰጡአቸው።
6ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተሰጡአቸው።
7ለሜራሪም ልጆች በየወገኖቻቸው ከሮቤል ነገድ፥ ከጋድም ነገድ፥ ከዛብሎንም ነገድ ዐሥራ ሁለት ከተሞች ተሰጡአቸው።
8እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ። 9የይሁዳም ልጆች ነገድ፥ የስምዖንም ልጆች ነገድ፥ የብንያምም ልጆች ነገድ በስማቸው የተጠሩትን እነዚህን ከተሞች ሰጡአቸው። 10የፊተኛው ዕጣ ለእነርሱ ስለወጣ የሌዊ ልጆች የቀዓት ወገን ለሆኑ ለአሮን ልጆች ሆኑ። 11የኤናቅ ልጆች ከተማ ቅርያትያርቦቅንና በዙሪያዋ ያሉ መሰማሪያዎችን ሰጡአቸው፤ ይህችውም በይሁዳ ተራራ ያለች ኬብሮን ናት። 12ኢያሱም የከተማዪቱን እርሻ መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ልጆች ርስት አድርጎ ሰጣቸው።
13ለካህኑም ለአሮን ልጆች እነዚህን ሰጡ፤ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንንና መሰማርያዋን፤ ሌምናንና መሰማርያዋን፥ 14ኤቴርንና#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኤሎም” ይላል። መሰማርያዋን፥ ኤታምንንና መሰማርያዋን፤ 15ሄሎንንና መሰማርያዋን፥ ዳቤርንና መሰማርያዋን፥ 16አሳንና መሰማርያዋን፥ ዮጣንንና መሰማርያዋን፥ ቤትሳሚስንና መሰማርያዋን፤ ከእነዚህ ከሁለቱ ነገዶች ዘጠኝ ከተሞችን ሰጡ። 17ከብንያምም ነገድ ገባዖንንና መሰማርያዋን፥ ጋቲትንና መሰማርያዋን፤ 18ዓናቶትንና መሰማርያዋን፥ አልሞንንና መሰማርያዋን፤ አራት ከተሞችን ሰጡ። 19የካህናቱ የአሮን ልጆች ከተሞች ከመሰማሪያዎቻቸው ጋር ዐሥራ ሦስት ናቸው፤
20ለቀሩትም ለሌዋውያኑ ለቀዓት ልጆች የዕጣቸው ከተሞች ከኤፍሬም ነገድ ደረሱአቸው። 21#ዕብ. “በኤፍሬም ተራራማ ሀገር” ይላል።ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰማርያዋን፥ ጌዜርንና መሰማርያዋን፤ 22ቄብጻይምንና መሰማርያዋን፥#“ቄብጻይምንና መሰማርያዋን” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ቤቶሮንና መሰማርያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 23ከዳንም ነገድ ኤልቆታይምንና መሰማርያዋን፥ ገባቶንንና መሰማርያዋን፤ 24ኤሎንንና መሰማርያዋን፥ ጌቴራሞንንና መሰማርያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 25ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ጠናሕንና መሰማርያዋን፥ ዬባታንና መሰማርያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 26የቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች ከተሞች ሁሉ ከመሰማርያቸው ጋር ዐሥር ናቸው።
27ለሌዋውያንም ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ በባሳን ውስጥ የሆነችውን ጎላንንና መሰማርያዋን፥ ቦሶርንና መሰማርያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 28ከይሳኮርም ነገድ ቂሶንንና መሰማርያዋን፥ ዳብራትንና መሰማርያዋን፤ 29ሬማትንና መሰማርያዋን፥ ዓይንጋኒምንና መሰማርያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 30ከአሴርም ነገድ መሴላንና መሰማርያዋን፥ አቤዶንንና መሰማርያዋን፥ 31ሔልቃትንንና መሰማርያዋን፥ ረዓብንና መሰማርያዋን፤ አራቱንም ከተሞች ሰጡአቸው። 32ከንፍታሌምም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማርያዋን፥ ኤማትንና መሰማርያዋን፥ ቃርቴንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 33የጌድሶን ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው ዐሥራ ሦስት ከተሞች ከመሰማርያቸው ጋር ናቸው።
34ከሌዋውያን ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ወገን ከዛብሎን ነገድ ዮቅናምንና መሰማርያዋን፥ ቃዴስንና መሰማርያዋን፥ 35ዲምናንና መሰማርያዋን፥ ሴላንና መሰማርያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። 36በዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ በኩል ከሮቤል ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ በሚሶን ምድረ በዳ ቦሶርንና መሰማርያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማርያዋን፤ 37ቄዴሞትንና መሰማርያዋን፥ ሜፍዐትንና መሰማርያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። 38ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማርያዋን፥ ቃሚንንና መሰማርያዋን፤ 39ሐሴቦንንና መሰማርያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማርያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። 40ከሌዊ ወገኖች የቀሩት የሜራሪ ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ ዕጣቸውም ዐሥራ ሁለት ከተማ ነበረ።
41በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ካሉ ከመሰማርያዎቻቸው ጋር አርባ ስምንት ከተሞች ነበሩ። 42እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው ከመሰማርያቸው ጋር ነበሩ፤ እነዚህም ከተሞች ሁሉ እንዲሁ ነበሩ። [ኢያሱም በየድንበሮቻቸው ምድርን ማካፈልን ጨረሰ። የእስራኤል ልጆችም ለኢያሱ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ድርሻውን ሰጡት፤ እርሱ የሚፈልጋትን ከተማ በኤፍሬም ተራራ የምትገኘውን ቴምናሴራን ሰጡት፤ ከተማም ሠራባት፤ በውስጧም ተቀመጠ። ኢያሱም በምደረ በዳ በመንገድ የተወለዱትን የገረዘባቸውን የድንጋይ ባልጩቶች ወስዶ በቴምናሴራ አኖራቸው።]#በቅንፍ ውስጥ ያለው በግሪክ ሰባ. ሊ. ብቻ።
እስራኤል ምድሪቱን ወርሰው ዕረፍት እንዳገኙ
43እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። 44እግዚአብሔርም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፤ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ይቋቋማቸው ዘንድ ማንም ሰው አልቻለም፤ እግዚአብሔርም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። 45እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 21: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ