መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 4
4
እስራኤል መታሰቢያ ድንጋዮችን እንዳቆሙ
1እንዲህም ሆነ፤ ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው በተሻገሩ ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2“ከሕዝቡ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ዐሥራ ሁለት ሰዎችን ውሰድ፦ 3በዮርዳኖስ መካከል የካህናት እግር ከቆመበት ስፍራ#“የካህናት እግር ከቆመበት ስፍራ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ዐሥራ ሁለት ቀላል ድንጋዮችን እንዲያነሡ እዘዛቸው፤ ከእናንተም ጋር ውሰዱአቸው፤ ከዚያም ሌሊት በምታድሩበት ቦታ በየነገዳችሁ ጠብቋቸው።”
4ኢያሱም ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ከእስራኤል ልጆች የታወቁትን ዐሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ። 5ኢያሱም አላቸው፥ “በእኔና በእግዚአብሔር ፊት#ዕብ. “ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ታቦት ፊት” ይላል። ወደ ዮርዳኖስ መካከል ዕለፉ፤ እያንዳንዱ ሰው በዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ቍጥር በትከሻው ላይ አንድ አንድ ድንጋይ ከዚያ ይሸከም። 6እነዚህም ምልክት ይሆኑላችኋል፤ ልጅህ ነገ፦ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው?’ ብሎ በጠየቀህ ጊዜ፥ ልጅህን እንዲህ ትለዋለህ፦ 7አንተ በምድር ሁሉ ጌታ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ስንሻገር የዮርዳኖስ ወንዝ ስለ ደረቀ ነው፤ እነዚህ ድንጋዮችም ለእስራኤል ልጆች ለዘለዓለም መታሰቢያ ይሆናሉ።”
8የእስራኤልም ልጆች ኢያሱ እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እግዚአብሔር ኢያሱን እንዳዘዘው” ይላል። የእስራኤልም ልጆች ዮርዳኖስን አካትተው በተሻገሩ ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን እንደ አዘዘው በእስራኤል ነገድ ቍጥር#“በእስራኤል ነገድ ቍጥር” የሚለው በዕብ. የለም። ከዮርዳኖስ መካከል ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሥተው ወደ ሰፈራቸው ወሰዱ፤ በዚያም አኖሩአቸው። 9ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ። 10ኢያሱም ለሕዝቡ እንዲነግር፥ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ እስኪፈጽም ድረስ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል ቆመው ነበር፤ ሕዝቡም ፈጥነው ተሻገሩ። 11ሕዝቡም ሁሉ አካትተው በተሻገሩ ጊዜ ታቦተ ሕጉ#ግሪክ ሰባ ሊ. “የእግዚአብሔር የሕጉ ታቦት” ሲል ዕብ. “የእግዚአብሔር ታቦት” ይላል። ተሻገረች፤ እነዚያም ድንጋዮች#ዕብ. “ካህናቱ” ይላል። በፊታቸው ተሻገሩ። 12ሙሴም እንዳዘዛቸው የሮቤል ልጆች፥ የጋድም ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ታጥቀው በእስራኤል ልጆች ፊት ተሻገሩ። 13አርባ ሺህ ያህል ለጦርነት የታጠቁ ሰዎች የኢያሪኮን ሀገር ይወጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ተሻገሩ። 14በዚያም ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ አደረገው፤ ሙሴንም እንደ ፈሩ በዕድሜው ሁሉ ፈሩት።
15እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 16“የቃል ኪዳኑን ታቦት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የእግዚአብሔርን የምስክሩን ታቦት” ይላል። የሚሸከሙትን ካህናት ከዮርዳኖስ እንዲወጡ እዘዛቸው።” 17ኢያሱም ካህናቱን፥ “ከዮርዳኖስ ውጡ” ብሎ አዘዛቸው። 18የእግዚአብሔርንም የቃል ኪዳን ታቦተ ሕግ የተሸከሙ ካህናት ከዮርዳኖስ መካከል በወጡ ጊዜ፥ በእግራቸውም የብስ በረገጡ ጊዜ፥ የዮርዳኖስ ውኃ ተወርውሮ ወደ ስፍራው ተመለሰ፤ ቀድሞም እንደ ነበረ ሂዶ ዳር እስከ ዳር ሞላ።
19ሕዝቡም በመጀመሪያው ወር በዐሥረኛው ቀን ከዮርዳኖስ ወጡ፤ በኢያሪኮም በምሥራቅ በኩል በጌልገላ ሰፈሩ። 20ኢያሱም ከዮርዳኖስ ውስጥ የወሰዱአቸውን እነዚያን ዐሥራ ሁለቱን ድንጋዮች በጌልገላ አቆማቸው። 21ኢያሱም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፥ “ልጆቻችሁ፦ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው?’ ብለው በሚጠይቋችሁ ጊዜ፥ 22ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ትነግሯቸዋላችሁ፦ ‘እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ተሻገረ፤’ 23እስክናልፍ ድረስ አምላካችን እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር ከፊታችን እንዳደረቀ እንዲሁ እስክንሻገር ድረስ አምላካችን እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ውኃ ከፊታችን አደረቀ። 24ይኸውም የእግዚአብሔር ኀይል ጠንካራ እንደ ሆነች የምድር አሕዛብ ሁሉ እንዲያውቁ፥ አምላካችሁንም እግዚአብሔርን በሥራው ሁሉ እንድትፈሩ ነው።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 4: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ