መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 5
5
1እንዲህም ሆነ፤ በዮርዳኖስ ማዶ በባሕር በኩል#“በባሕር በኩል” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። የነበሩት የአሞራውያን ነገሥት ሁሉ፥ በባሕሩም አጠገብ የነበሩ የፊኒቃውያን ነገሥት ሁሉ፥ እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት የዮርዳኖስን ውኃ እስኪሻገሩ ድረስ እንዳደረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባቸው ቀለጠ፤ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ አእምሮአቸውን ሳቱ።
የእስራኤል ልጆች በጌልጌላ እንደ ተገረዙ
2በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ኢያሱን፥ “ከሻፎ ድንጋይ የባልጩት መቍረጫ ሠርተህ የእስራኤልን ልጆች ዳግመኛ ግረዛቸው” አለው። 3ኢያሱም የባልጩት መቍረጫ ሠርቶ የግርዛት ኮረብታ በተባለ ስፍራ የእስራኤልን ልጆች ገረዘ። 4ኢያሱ ሕዝቡን ሁሉ የገረዘበት ምክንያት ይህ ነው፤ ከግብፅ የወጡ ወንዶች ተዋጊዎች ሁሉ ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ በምድረ በዳ ሞቱ፤ የወጡትም ወንዶች ሁሉ ተገርዘው ነበር። 5ነገር ግን ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመንገድ፥ በምድረ በዳ የተወለዱ ሕዝብ ሁሉ አልተገረዙም ነበርና፥ ኢያሱ እነዚህን ሁሉ ገረዛቸው። 6እግዚአብሔርም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻችን የማለላቸውን ምድር እንደማያሳያቸው የማለባቸውን፥ ከግብፅ የወጡ የእግዚአብሔርንም ቃል ያልሰሙ፥ እነዚያ ተዋጊዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ የእስራኤል ልጆች አርባ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አርባ ሁለት” ይላል። ዓመት በመድበራ ምድረ በዳ ይዞሩ ነበር። 7ልጆቻቸውን በእነርሱ ፋንታ አስነሣ፤ እነዚህንም ኢያሱ ገረዛቸው፤ በመንገድ ስለተወለዱ አልተገረዙም ነበርና። 8በተገረዙም ጊዜ እስኪድኑ ድረስ በሰፈር ውስጥ ተቀመጡ። 9እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “ዛሬ የግብፅን ተግዳሮት ከእናንተ ላይ አስወግጃለሁ” አለው፤ ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተብሎ ተጠራ።
10የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፤#“የእስራኤልም ልጆች በጌልጌላ ሰፈሩ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ከወሩም በዐሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ ምዕራብ ፋሲካን አደረጉ። 11#ዕብ. “ከፋሲካው በኋላ በነጋው” የሚል ይጨምራል።ከምድሪቱም ፍሬ ቂጣና አዲስ እህል በዚያው ቀን በሉ። 12በነጋውም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ዳግመኛ መና አላገኙም፤ በዚያው ዓመት የፊኒቆንን ምድር ፍሬ ሰበሰቡ።
ኢያሱና ባለ ሰይፉ ሰው
13እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ፤ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?” አለው። 14እርሱም፥ “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ፤ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና፥ “በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል?” አለው። 15የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን፥ “አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ” አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ።#“ኢያሱም እንዲሁ አደረገ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 5: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ