የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 6

6
የኢ​ያ​ሪኮ ቅጥር መው​ደቅ
1ኢያ​ሪ​ኮም በግ​ንብ ታጥራ#ዕብ. “ኢያ​ሪ​ኮም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የተ​ነሣ” የሚል ይጨ​ም​ራል። ተዘ​ግታ ነበር፤ ወደ እር​ስዋ የሚ​ገባ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ወጣ አል​ነ​በ​ረም። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን አለው፥ “እነሆ፥ ኢያ​ሪ​ኮ​ንና ንጉ​ሥ​ዋን ጽኑ​ዓን፥ ኀያ​ላ​ን​ዋ​ንም በእ​ጅህ ሰጥ​ቼ​አ​ለሁ። 3አን​ተም ተዋ​ጊ​ዎ​ችን ሁሉ በዙ​ሪ​ያው አሰ​ል​ፋ​ቸው። ተዋ​ጊ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ አንድ ጊዜ ይዙሩ፤ እን​ዲ​ሁም ስድ​ስት ቀን አድ​ርጉ።#“ተዋ​ጊ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ ይዙሩ ፤ እን​ዲ​ሁም ስድ​ስት ቀን አድ​ርጉ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 4ሰባ​ትም ካህ​ናት ሰባት ቀንደ መለ​ከት በታ​ቦቱ ፊት ይያዙ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፤ ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ይንፉ።#ምዕ. 6 ቍ. 4 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 5ቀንደ መለ​ከ​ቱም ባለ​ማ​ቋ​ረጥ ሲነፋ፥ የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ ስት​ሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ቅጥር ይወ​ድ​ቃል፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ፊት ለፊት እየ​ሮጠ ይገ​ባ​ባ​ታል።” 6የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ ካህ​ና​ቱን ጠርቶ፥ “የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ከሙ፤ ሰባ​ትም ካህ​ናት ሰባት ቀንደ መለ​ከት ወስ​ደው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሂዱ” አላ​ቸው። 7ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ሂዱ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ዙሩ፤ ተዋ​ጊ​ዎ​ችም ከጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሂዱ ብላ​ችሁ እዘ​ዙ​አ​ቸው” አላ​ቸው።
8በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ይሄዱ ዘንድ ኢያሱ እንደ ነገ​ራ​ቸው ሰባቱ ካህ​ናት የተ​ቀ​ደሱ ሰባ​ቱን ቀንደ መለ​ከት ይዘው ሄዱ፤ በሄ​ዱም ጊዜ አሰ​ም​ተው በም​ል​ክት ነፉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕጉ ታቦት ትከ​ተ​ላ​ቸው ነበር። 9ሰል​ፈ​ኞ​ችም ፊት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ካህ​ና​ቱም ነጋ​ሪት ይመቱ ነበር፤ ከታ​ቦቱ በኋላ ይከ​ተሉ የነ​በ​ሩ​ትም ቀንደ መለ​ከ​ቱን እየ​ነፉ ይሄዱ ነበር። 10ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን፦ እን​ዳ​ይ​ጮኹ ማንም ድም​ፃ​ቸ​ውን እን​ዳ​ይ​ሰማ፥ እን​ዲ​ጮኹ እስ​ኪ​ያ​ዛ​ቸ​ውም ድረስ ከአ​ፋ​ቸው ቃል እን​ዳ​ይ​ወጣ አዘ​ዛ​ቸው። 11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የቃል ኪዳኑ ታቦት ሄደች፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ዞረች፤ ወደ ሰፈ​ርም ተመ​ልሳ በዚያ አደ​ረች።#ዕብ. “እን​ዲሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት አንድ ጊዜ ከተ​ማ​ዪ​ቱን አዙ​ረው፥ እነ​ር​ሱም ወደ ሰፈሩ ተመ​ል​ሰው አደሩ” ይላል።
12ኢያ​ሱም በማ​ግ​ሥቱ ማለዳ ተነሣ፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕ​ጉን ታቦት ተሸ​ከሙ። 13ሰባ​ቱም ካህ​ናት ሰባ​ቱን ቀንደ መለ​ከት ይዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ቀንደ መለ​ከ​ቱ​ንም ይነፉ ነበር፤ ተዋ​ጊ​ዎ​ችም በፊ​ታ​ቸው ይሄዱ ነበር፤ የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት በኋላ ይሄዱ ነበር፤ ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ይነፉ ነበር። 14በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የቀ​ረው ሕዝብ ሁሉ ከተ​ማ​ዪ​ቱን አንድ ጊዜ ዞረው ወደ ሰፈር ተመ​ለሱ፤ ስድ​ስት ቀንም እን​ዲህ አደ​ረጉ።
15በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን በነጋ ጊዜ ማል​ደው ተነሡ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ ዞሩ፤ በዚ​ያም ቀን ብቻ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ ዞሩ። 16እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ በዞ​ሩና ካህ​ናቱ ቀንደ መለ​ከ​ቱን በነፉ ጊዜ፤ ኢያሱ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና ጩኹ። 17ከተ​ማ​ዪ​ቱም በእ​ር​ስ​ዋም ያለው ሁሉ ለሠ​ራ​ዊት ጌታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርም ይሆ​ናሉ፤ የላ​ክ​ና​ቸ​ውን መል​እ​ክ​ተ​ኞች ስለ ሸሸ​ገች#“የላ​ክ​ና​ቸ​ውን መል​እ​ክ​ተ​ኞች ስለ ሸሸ​ገች” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ዘማ​ዊቱ ረዓብ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር በቤቷ ውስጥ ያሉ ሁሉ ብቻ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራሉ። 18እና​ንተ ግን እርም ብለን ከተ​ው​ነው እን​ዳ​ት​ወ​ስዱ ተጠ​ን​ቀቁ፤ ከእ​ር​ሱም ተመ​ኝ​ታ​ችሁ አት​ው​ሰዱ፤ ብት​ወ​ስዱ ግን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰፈር የተ​ረ​ገ​መች ታደ​ር​ጓ​ታ​ላ​ችሁ፤ እኛ​ንም ታጠ​ፉ​ና​ላ​ችሁ። 19ነገር ግን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ የና​ስና የብ​ረ​ትም ዕቃ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሁን፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግምጃ ቤት ይግባ።” 20ሕዝ​ቡም ጮኹ፥#“ሕዝ​ቡም ጮኹ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ነፉ፤ ሕዝ​ቡም የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታላቅ ጩኸት ጮኹ፤ ቅጥ​ሩም ወደቀ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ገቡ፤ ሁሉም ወደ ፊታ​ቸው ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ሮጡ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም እጅ አደ​ረጉ። 21ኢያ​ሱም ከተ​ማ​ዋን፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ውስጥ የነ​በ​ሩ​ትን ሁሉ፥ ከወ​ንድ እስከ ሴት፥ ከሕ​ፃን እስከ ሽማ​ግሌ፥ ከበሬ እስከ በግና እስከ አህያ በሰ​ይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋ።
22ኢያ​ሱም ምድ​ሪ​ቱን የሰ​ለሉ ሁለ​ቱን ሰዎች፥ “ወደ ዘማ​ዪቱ ቤት ግቡ፤ ከዚ​ያም ሴቲ​ቱ​ንና ያላ​ትን ሁሉ እን​ደ​ማ​ላ​ች​ሁ​ላት አውጡ” አላ​ቸው። 23እነ​ዚ​ያም ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሰ​ለሉ ሁለቱ ጐል​ማ​ሶች ወደ ዘማ​ዪቱ ረዓብ ቤት ገብ​ተው ረዓ​ብን፥ አባ​ቷ​ንና እና​ቷን፥ ወን​ድ​ሞ​ች​ዋ​ንም፥ ያላ​ት​ንም ሁሉ፥ ቤተ ዘመ​ዶ​ች​ዋ​ንም ሁሉ አወ​ጡ​አ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰፈር በውጭ አስ​ቀ​መ​ጡ​አ​ቸው።
24ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም፥ በእ​ር​ስ​ዋም የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ፤ ነገር ግን ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ የና​ሱ​ንና የብ​ረ​ቱ​ንም ዕቃ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግምጃ ቤት ውስጥ አገቡ። 25ኢያ​ሪ​ኮን ሊሰ​ልሉ ኢያሱ የላ​ካ​ቸ​ው​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች ስለ ሸሸ​ገች ዘማ​ዊ​ቱን ረዓ​ብን፥ የአ​ባ​ቷ​ንም ቤተ ሰብ፥ ያላ​ት​ንም ሁሉ ኢያሱ አዳ​ና​ቸው፤ እር​ስ​ዋም በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​ም​ጣ​ለች።
26በዚ​ያ​ችም ቀን ኢያሱ፥ “ይህ​ችን ከተማ ኢያ​ሪ​ኮን ለመ​ሥ​ራት የሚ​ነሣ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠ​ረ​ቷን በበ​ኵር ልጁ የሚ​ጥል፥ በሮ​ች​ዋ​ንም በታ​ናሹ ልጁ የሚ​ያ​ቆም ርጉም ይሁን” ብሎ ማለ።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የቤ​ቴሉ ኦዛን በበ​ኵር ልጁ በአ​ቤ​ሮን መሠ​ረ​ቷን ጣለ ፤ በሕ​ይ​ወት በነ​በ​ረው በታ​ናሹ ልጁም በሮ​ች​ዋን አቆመ” የሚል ይጨ​ም​ራል። 27እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከኢ​ያሱ ጋር ነበረ፤ ስሙም በም​ድር ሁሉ ላይ ደረሰ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ