በሰንበትም በአንድ ምኵራብ ውስጥ አስተማራቸው። ዐሥራ ስምንት ዓመት ሙሉ ጋኔን ያጐበጣት አንዲት ሴት ነበረች፤ ጐባጣም ነበረች፤ ከቶ ቀጥ ብላ መቆም አትችልም ነበር። ጌታችን ኢየሱስም አይቶ ራራላት፥ ጠርቶም፥ “ሴትዮ፥ ከደዌሽ ተፈትተሻል” አላት። እጁንም በላይዋ ጫነ፤ ያንጊዜም ፈጥና ቀጥ አለች፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነችው። የምኵራቡ ሹምም ጌታ ኢየሱስ በሰንበት ፈውሶአልና፤ እየተቈጣ መልሶ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፥ “ሥራችሁን የምትሠሩባቸው ስድስት ቀኖች ያሉ አይደለምን? ያንጊዜ ኑና ተፈወሱ፤ በሰንበት ቀን ግን አይሆንም።” ጌታችን ኢየሱስም መልሶ አላቸው፥ “እናንት ግብዞች፥ እናንተሳ አህያችሁን ወይም በሬአችሁን በሰንበት ቀን ገለባ ከሚበላበት አትፈቱትምን? ውኃ ልታጠጡትስ አትወስዱትምን? ይህቺ የአብርሃም ልጅ እነሆ፥ ሰይጣን ከአሰራት ዐሥራ ስምንት ዓመት ነው፤ እርስዋስ በሰንበት ቀን ከእስራቷ ልትፈታ አይገባምን?” ይህንም ባለ ጊዜ በእርሱ ላይ በጠላትነት የተነሡበት ሁሉ አፈሩ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ሁሉ ከእርሱ ስለሚደረገው ድንቅ ነገር ሁሉ ደስ አላቸው።
የሉቃስ ወንጌል 13 ያንብቡ
ያዳምጡ የሉቃስ ወንጌል 13
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሉቃስ ወንጌል 13:10-17
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች