ሉቃስ 13:10-17

ሉቃስ 13:10-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በሰ​ን​በ​ትም በአ​ንድ ምኵ​ራብ ውስጥ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው። ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ሙሉ ጋኔን ያጐ​በ​ጣት አን​ዲት ሴት ነበ​ረች፤ ጐባ​ጣም ነበ​ረች፤ ከቶ ቀጥ ብላ መቆም አት​ች​ልም ነበር። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም አይቶ ራራ​ላት፥ ጠር​ቶም፥ “ሴትዮ፥ ከደ​ዌሽ ተፈ​ት​ተ​ሻል” አላት። እጁ​ንም በላ​ይዋ ጫነ፤ ያን​ጊ​ዜም ፈጥና ቀጥ አለች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገ​ነ​ችው። የም​ኵ​ራቡ ሹምም ጌታ ኢየ​ሱስ በሰ​ን​በት ፈው​ሶ​አ​ልና፤ እየ​ተ​ቈጣ መልሶ ሕዝ​ቡን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሥራ​ች​ሁን የም​ት​ሠ​ሩ​ባ​ቸው ስድ​ስት ቀኖች ያሉ አይ​ደ​ለ​ምን? ያን​ጊዜ ኑና ተፈ​ወሱ፤ በሰ​ን​በት ቀን ግን አይ​ሆ​ንም።” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ አላ​ቸው፥ “እና​ንት ግብ​ዞች፥ እና​ን​ተሳ አህ​ያ​ች​ሁን ወይም በሬ​አ​ች​ሁን በሰ​ን​በት ቀን ገለባ ከሚ​በ​ላ​በት አት​ፈ​ቱ​ት​ምን? ውኃ ልታ​ጠ​ጡ​ትስ አት​ወ​ስ​ዱ​ት​ምን? ይህቺ የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ እነሆ፥ ሰይ​ጣን ከአ​ሰ​ራት ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ነው፤ እር​ስ​ዋስ በሰ​ን​በት ቀን ከእ​ስ​ራቷ ልት​ፈታ አይ​ገ​ባ​ምን?” ይህ​ንም ባለ ጊዜ በእ​ርሱ ላይ በጠ​ላ​ት​ነት የተ​ነ​ሡ​በት ሁሉ አፈሩ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ሁሉ ከእ​ርሱ ስለ​ሚ​ደ​ረ​ገው ድንቅ ነገር ሁሉ ደስ አላ​ቸው።

ሉቃስ 13:10-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ኢየሱስ በሰንበት ቀን በአንድ ምኵራብ ያስተምር ነበር። በዚያም የድካም መንፈስ ዐሥራ ስምንት ዓመት ሙሉ አካለ ስንኩል ያደረጋት አንዲት ሴት ነበረች፤ እርሷም ከመጕበጧ የተነሣ ፈጽሞ ቀና ማለት አትችልም ነበር። ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና፣ “አንቺ ሴት፤ ከሕመምሽ ነጻ ወጥተሻል” አላት፤ እጁንም በላይዋ ጫነ፤ እርሷም ወዲያው ቀጥ ብላ ቆመች፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነች። የምኵራቡ አለቃ ግን፣ ኢየሱስ በሰንበት ቀን ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ ሕዝቡን፣ “ሥራ ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ ስለዚህ በእነዚያ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት ቀን አይደለም” አላቸው። ጌታም መልሶ እንዲህ አለው፤ “እናንተ ግብዞች፤ ከእናንተ መካከል አንድ ሰው በሬውን ወይም አህያውን በሰንበት ቀን ከማደሪያው ፈትቶ ውሃ ሊያጠጣ ይወስደው የለምን? ታዲያ፣ ይህች ሴት የአብርሃም ልጅ ሆና ሳለች ዐሥራ ስምንት ዓመት ሙሉ በሰይጣን ታስራ ስትኖር፣ ከዚህ እስራት በሰንበት ቀን መፈታት አይገባትምን?” ይህን በተናገረ ጊዜ ተቃዋሚዎቹ ሁሉ ዐፈሩ፤ ሕዝቡ ሁሉ ግን እርሱ ባደረገው ድንቅ ሥራ ሁሉ ደስ አላቸው።

ሉቃስ 13:10-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በሰንበትም በአንድ ምኵራብ ያስተምር ነበር። እነሆም፥ ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ የድካም መንፈስ ያደረባት ሴት ነበረች፥ እርስዋም ጐባጣ ነበረች ቀንታም ልትቆም ከቶ አልተቻላትም። ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና፦ አንቺ ሴት፥ ከድካምሽ ተፈትተሻል አላት፥ እጁንም ጫነባት፤ ያን ጊዜም ቀጥ አለች፥ እግዚአብሔርንም አመሰገነች። የምኵራብ አለቃ ግን ኢየሱስን በሰንበት ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ መለሰና ሕዝቡን፦ ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ እንግዲህ በእነርሱ መጥታችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት አይደለም አለ። ጌታም መልሶ፦ እናንተ ግብዞች፥ ከእናንተ እያንዳንዱ በሰንበት በሬውን ወይስ አህያውን ከግርግሙ ፈትቶ ውኃ ሊያጠጣው ይወስደው የለምን? ይህችም የአብርሃም ልጅ ሆና ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያሰራት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን? አለው። ይህንም ሲናገር ሳለ የተቃወሙት ሁሉ አፈሩ፤ ከእርሱም በተደረገው ድንቅ ሁሉ ሕዝቡ ሁሉ ደስ አላቸው።

ሉቃስ 13:10-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ኢየሱስ በሰንበት ቀን ከምኲራቦቹ በአንዱ ያስተምር ነበር፤ ከዚያም ከዐሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ርኩስ መንፈስ ጀርባዋን ያጐበጣት አንዲት ሴት ነበረች፤ እርስዋ ወገብዋ በመጒበጡ ቀና ለማለት በፍጹም አትችልም ነበር። ኢየሱስ ባያት ጊዜ ጠራትና “አንቺ ሴት ከበሽታሽ ተፈውሰሻል!” አላት። እጆቹን ጫነባት፤ ወዲያውም ቀጥ ብላ ቆመች፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነች። ኢየሱስ በሰንበት ቀን ስለ ፈወሰ የምኲራቡ አለቃ ተቈጣና ለሕዝቡ፦ “በሳምንት ውስጥ ሥራ የሚሠራባቸው ስድስት ቀኖች አሉ፤ በእነዚህ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ፤ በሰንበት ቀን ግን አይሆንም” ብሎ ተናገረ። ጌታ ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እናንተ ግብዞች፥ ከእናንተስ እያንዳንዱ በሰንበት ቀን በሬውን ከተዘጋበት አውጥቶ፥ ወይም አህያውን ከታሰረበት ፈቶ ውሃ ወደሚያጠጣበት ቦታ ይወስደው የለምን? እነሆ፥ የአብርሃም ዘር የሆነች ይህች ሴት ዐሥራ ስምንት ዓመት ሙሉ በሰይጣን ታስራ ስትሠቃይ ኖራለች፤ ታዲያ፥ እርስዋ ታስራ ከምትሠቃይበት በሽታ በሰንበት ቀን መፈታት አይገባትምን?” በዚህም ንግግሩ ኢየሱስ ተቃዋሚዎቹን ሁሉ አሳፈራቸው፤ ሕዝቡ ግን ኢየሱስ ባደረገው ድንቅ ነገር ሁሉ ተደሰተ።

ሉቃስ 13:10-17 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በሰንበት ቀንም ከምኵራቦቹ በአንዱ ያስተምር ነበር። እነሆም፥ ከዐሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ርኩስ መንፈስ በሽተኛ ያደረጋት አንዲት ሴት ነበረች፤ እርሷም ጎባጣ ነበረች፤ ቀጥ ብላ መቆምም በፍጹም አልተቻላትም። ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና “አንቺ ሴት! ከበሽታሽ ተፈውሰሻል፤” አላት፤ እጁንም ጫነባት፤ ያን ጊዜም ቀጥ አለች፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነች። የምኵራብ አለቃው ግን ኢየሱስ በሰንበት ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ ሕዝቡን “ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ እንግዲህ በእነርሱ መጥታችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት አይሆንም፤” አለ። ጌታም መልሶ እናንተ ግብዞች! ከእናንተ እያንዳንዱ በሰንበት በሬውን ወይስ አህያውን ከግርግሙ ፈትቶ ውሃ ሊያጠጣው ይወስደው የለምን? ይህች ለዐሥራ ስምንት ዓመት ሰይጣን ያሠራት የአብርሃም ልጅ በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን? አለው። ይህንንም ሲናገር የተቃወሙት ሁሉ አፈሩ፤ በእርሱም በተደረጉት ድንቅ ነገሮች ሁሉ ሕዝቡ በሙሉ ደስ አለው።