የሉ​ቃስ ወን​ጌል 22:55-62

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 22:55-62 አማ2000

በግ​ቢ​ውም ውስጥ እሳት አን​ድ​ደው ተቀ​መጡ፤ ጴጥ​ሮ​ስም አብ​ሮ​አ​ቸው በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተቀ​መጠ። በእ​ሳ​ቱም ብር​ሃን በኩል ተቀ​ምጦ ሳለ አን​ዲት ብላ​ቴና አየ​ችው፤ እርሱ መሆ​ኑ​ንም ለየ​ች​ውና፥ “ይህም ከእ​ርሱ ጋር ነበር” አለች። እርሱ ግን፥ “ሴትዮ! የም​ት​ዪ​ውን አላ​ው​ቅም” ብሎ ካደ። ከጥ​ቂት ጊዜም በኋላ ሌላ ሰው አየ​ውና፥ “አን​ተም ከእ​ነ​ርሱ ወገን ነህ” አለው፤ ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አንተ ሰው! እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም” አለው። አን​ዲት ሰዓት ያህ​ልም ቈይቶ አንድ ሌላ ሰው፥ “ይህም በእ​ው​ነት ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ሰው​የ​ውም የገ​ሊላ ሰው ነው” ብሎ አስ​ጨ​ነ​ቀው። ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አንተ ሰው! የም​ት​ለ​ውን አላ​ው​ቅም” አለው፤ እር​ሱም ይህን ሲና​ገር ያን​ጊዜ ዶሮ ጮኸ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዘወር ብሎ ጴጥ​ሮ​ስን አየው፤ ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ዛሬ ዶሮ ሳይ​ጮኽ ሦስት ጊዜ ትክ​ደ​ኛ​ለህ” ያለ​ውን የጌ​ታ​ች​ንን ቃል ዐሰበ። ጴጥ​ሮ​ስም ወደ ውጭ ወጥቶ መራራ ልቅ​ሶን አለ​ቀሰ።