ሉቃስ 22:55-62

ሉቃስ 22:55-62 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በግ​ቢ​ውም ውስጥ እሳት አን​ድ​ደው ተቀ​መጡ፤ ጴጥ​ሮ​ስም አብ​ሮ​አ​ቸው በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተቀ​መጠ። በእ​ሳ​ቱም ብር​ሃን በኩል ተቀ​ምጦ ሳለ አን​ዲት ብላ​ቴና አየ​ችው፤ እርሱ መሆ​ኑ​ንም ለየ​ች​ውና፥ “ይህም ከእ​ርሱ ጋር ነበር” አለች። እርሱ ግን፥ “ሴትዮ! የም​ት​ዪ​ውን አላ​ው​ቅም” ብሎ ካደ። ከጥ​ቂት ጊዜም በኋላ ሌላ ሰው አየ​ውና፥ “አን​ተም ከእ​ነ​ርሱ ወገን ነህ” አለው፤ ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አንተ ሰው! እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም” አለው። አን​ዲት ሰዓት ያህ​ልም ቈይቶ አንድ ሌላ ሰው፥ “ይህም በእ​ው​ነት ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ሰው​የ​ውም የገ​ሊላ ሰው ነው” ብሎ አስ​ጨ​ነ​ቀው። ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አንተ ሰው! የም​ት​ለ​ውን አላ​ው​ቅም” አለው፤ እር​ሱም ይህን ሲና​ገር ያን​ጊዜ ዶሮ ጮኸ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዘወር ብሎ ጴጥ​ሮ​ስን አየው፤ ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ዛሬ ዶሮ ሳይ​ጮኽ ሦስት ጊዜ ትክ​ደ​ኛ​ለህ” ያለ​ውን የጌ​ታ​ች​ንን ቃል ዐሰበ። ጴጥ​ሮ​ስም ወደ ውጭ ወጥቶ መራራ ልቅ​ሶን አለ​ቀሰ።

ሉቃስ 22:55-62 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ሰዎቹ በግቢው ውስጥ እሳት አቀጣጥለው በአንድነት ተቀምጠው ነበር። ጴጥሮስም መጥቶ አብሮ ተቀመጠ። ጴጥሮስ በእሳቱ አጠገብ ተቀምጦ ሳለ አንዲት ገረድ በእሳቱ ብርሃን አየችው፤ ወደ እርሱ ትኲር ብላ ተመልክታም “ይህም ከኢየሱስ ጋር ነበር!” አለች። ጴጥሮስ ግን፥ “አንቺ ሴት! እኔ አላውቀውም!” ሲል ካደ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ አንድ ሌላ ሰው ጴጥሮስን አየውና “አንተም ከእነርሱ አንዱ ነህ!” አለው። ጴጥሮስ ግን “አንተ ሰው! አይደለሁም!” አለ። አንድ ሰዓት ያኽል ቈይቶም አንድ ሌላ ሰው ጴጥሮስን “ይህ ሰው ገሊላዊ ነውና በእርግጥ ከእርሱ ጋር ነበረ!” በማለት አጥብቆ ተናገረ። ጴጥሮስ ግን፥ “አንተ ሰው! የምትለውን አላውቅም!” አለ። ይህን ሲናገር ሳለ ወዲያውኑ ዶሮ ጮኸ። በዚህ ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ዞር ብሎ ጴጥሮስን አየው፤ ጴጥሮስም “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” በማለት ጌታ ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አስታወሰ። ወደ ውጪ ወጥቶም ምርር ብሎ አለቀሰ።