የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 6:17-42

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 6:17-42 አማ2000

ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ወርዶ በሰፊ ቦታ ቆመ፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወገን ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከመ​ላው ይሁ​ዳና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ከጢ​ሮ​ስና ከሲ​ዶና ባሕር ዳርቻ ትም​ህ​ር​ቱን ሊሰሙ፥ ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውም ሊፈ​ወሱ የመ​ጡት ከሕ​ዝቡ ወገን እጅግ ብዙ​ዎች ነበሩ። ክፉ​ዎች አጋ​ን​ንት ያደ​ሩ​ባ​ቸ​ውም ይፈ​ወሱ ነበር። ሕዝቡ ሁሉ ሊዳ​ስ​ሱት ይሹ ነበር፤ ኀይል ከእ​ርሱ ይወጣ ነበ​ርና፥ ሁሉ​ንም ይፈ​ው​ሳ​ቸው ነበር። እር​ሱም ወደ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ድሆች፥ ብፁ​ዓን ናችሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት የእ​ና​ንተ ናትና። ዛሬ የም​ት​ራቡ፥ ብፁ​ዓን ናችሁ፤ ትጠ​ግ​ባ​ላ​ች​ሁና፤ ዛሬ የም​ታ​ለ​ቅሱ፥ ብፁ​ዓን ናችሁ፤ ትስ​ቃ​ላ​ች​ሁና። ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ቢጠ​ሉ​አ​ችሁ፥ ከሰው ለይ​ተው ቢአ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ችሁ፥ ቢሰ​ድ​ቡ​አ​ችሁ፥ ክፉ ስምም ቢአ​ወ​ጡ​ላ​ችሁ ብፁ​ዓን ናችሁ። ያን​ጊዜ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ በደ​ስ​ታም ዝለሉ፤ ዋጋ​ችሁ በሰ​ማይ ብዙ ነውና፤ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ነቢ​ያ​ትን እን​ዲሁ አድ​ር​ገ​ዋ​ቸው ነበ​ርና። ነገር ግን እና​ንተ ባለ​ጠ​ጎች፥ ወዮ​ላ​ችሁ፥ ደስ​ታ​ች​ሁን ጨር​ሳ​ች​ኋ​ልና። ዛሬ ለም​ት​ጠ​ግቡ፥ ወዮ​ላ​ችሁ፥ ትራ​ባ​ላ​ች​ሁና፤ ዛሬ ለም​ት​ስ​ቁም ወዮ​ላ​ችሁ፥ ታዝ​ና​ላ​ች​ሁና፤ ታለ​ቅ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ምና። ሰዎች ሁሉ ስለ እና​ንተ መል​ካ​ሙን ነገር ቢና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ ወዮ​ላ​ችሁ፥ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ለሐ​ሰ​ተ​ኞች ነቢ​ያት እን​ዲህ ያደ​ርጉ ነበ​ርና። “ለም​ት​ሰ​ሙኝ ለእ​ና​ንተ ግን እን​ዲህ እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ውደዱ፤ ለሚ​ጠ​ሉ​አ​ች​ሁም መል​ካም አድ​ርጉ። የሚ​ረ​ግ​ሙ​አ​ች​ሁን መር​ቁ​አ​ቸው፤ ለሚ​በ​ድ​ሉ​አ​ች​ሁም ጸል​ዩ​ላ​ቸው። ጕን​ጭ​ህን ለሚ​መ​ታ​ህም ሁለ​ተ​ኛ​ይ​ቱን ስጠው፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ህን ለሚ​ወ​ስ​ድም ቀሚ​ስ​ህን ደግሞ አት​ከ​ል​ክ​ለው። ለሚ​ለ​ም​ን​ህም ሁሉ ስጥ፤ ገን​ዘ​ብ​ህን የሚ​ወ​ስ​ደ​ው​ንም እን​ዲ​መ​ልስ አት​ጠ​ይ​ቀው። ሰዎች ሊያ​ደ​ር​ጉ​ላ​ችሁ እን​ደ​ም​ት​ወ​ዱ​ትም እን​ዲሁ እና​ንተ አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው። የሚ​ወ​ድ​ዱ​አ​ች​ሁን ብቻ ብት​ወ​ዱማ እን​ግ​ዲህ ዋጋ​ችሁ ምን​ድን ነው? ይህ​ንስ ኃጥ​ኣ​ንም ያደ​ር​ጋሉ፤ የሚ​ወ​ድ​ዳ​ቸ​ው​ንም ይወ​ድ​ዳሉ። በጎ ለሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ላ​ችሁ በጎ ብታ​ደ​ርጉ እን​ግ​ዲህ ዋጋ​ችሁ ምን​ድን ነው? እን​ዲ​ህስ ኃጥ​ኣ​ንም ያደ​ር​ጋሉ። እን​ዲ​ከ​ፍ​ላ​ችሁ ተስፋ ለም​ታ​ደ​ር​ጉት ብታ​በ​ድሩ እን​ግ​ዲህ ዋጋ​ችሁ ምን​ድን ነው? ኃጥ​ኣ​ንም በአ​በ​ደ​ሩት ልክ ይከ​ፍ​ሉ​አ​ቸው ዘንድ ለኃ​ጥ​ኣን ያበ​ድ​ራ​ሉና። አሁ​ንም ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ውደዱ፤ መል​ካ​ምም አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​መ​ል​ሱ​ላ​ችሁ ተስፋ ሳታ​ደ​ርጉ አበ​ድሩ፤ ዋጋ​ች​ሁም ብዙ ይሆ​ናል፤ የል​ዑ​ልም ልጆች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እርሱ ለበ​ጎ​ዎ​ችና ለክ​ፉ​ዎች ቸር ነውና። ሰማ​ያዊ አባ​ታ​ችሁ የሚ​ራራ እንደ ሆነ እና​ን​ተም የም​ት​ራሩ ሁኑ። አት​ፍ​ረዱ፥ አይ​ፈ​ረ​ድ​ባ​ች​ሁ​ምም፤ አት​በ​ድሉ፥ አይ​በ​ድ​ሉ​አ​ች​ሁ​ምም፤ ይቅር በሉ፥ ይቅ​ርም ይሉ​አ​ች​ኋል። ስጡ፥ ይሰ​ጣ​ች​ኋ​ልም፤ የሞ​ላና የበዛ፥ የተ​ት​ረ​ፈ​ረ​ፈም መል​ካም መስ​ፈ​ሪያ በዕ​ቅ​ፋ​ችሁ ይሰ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ በሰ​ፈ​ራ​ች​ሁ​በ​ትም መስ​ፈ​ሪያ ይሰ​ፍ​ሩ​ላ​ች​ኋል።” ምሳ​ሌም መሰ​ለ​ላ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ዕውር ዕው​ርን ሊመራ ይች​ላ​ልን? ሁለ​ቱስ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ ይወ​ድቁ የለ​ምን? ከመ​ም​ህሩ የሚ​በ​ልጥ ደቀ መዝ​ሙር የለም፤ ለሁ​ሉም መጠኑ እንደ መም​ህሩ ይሆ​ናል። በወ​ን​ድ​ምህ ዐይን ውስጥ ያለ​ውን ጕድፍ ለምን ታያ​ለህ? በዐ​ይ​ንህ ውስጥ ያለ​ውን ምሰሶ አታ​ይ​ምን? ወን​ድ​ም​ህ​ንም፦ ወን​ድሜ ሆይ፥ ታገሥ፤ በዐ​ይ​ንህ ያለ​ውን ጕድፍ ላው​ጣ​ልህ ልት​ለው እን​ደ​ምን ትች​ላ​ለህ? አንተ ግን በዐ​ይ​ንህ ውስጥ ያለ​ውን ምሰሶ አታ​ይም፤ አንተ ግብዝ፥ አስ​ቀ​ድሞ ከዐ​ይ​ንህ ምሰ​ሶ​ውን አውጣ፤ ከዚህ በኋላ በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ዐይን ውስጥ ያለ​ውን ጕድፍ ታወጣ ዘንድ አጥ​ር​ተህ ታያ​ለህ።