የማ​ቴ​ዎስ ወን​ጌል 22:34-40

የማ​ቴ​ዎስ ወን​ጌል 22:34-40 አማ2000

ፈሪሳውያንም ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው በሰሙ ጊዜ አብረው ተሰበሰቡ። ከእነርሱም አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው “መምህር ሆይ! ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት?” ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም እንዲህ አለው “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።’ ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም ‘ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ፤’ የምትለው ናት። በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።”