የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 18

18
የካ​ህ​ና​ትና የሌ​ዋ​ው​ያን ተግ​ባር
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “አንተ ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ች​ህና የአ​ባ​ቶ​ችህ ወገ​ኖች፥ የክ​ህ​ነ​ታ​ች​ሁን ኀጢ​አት ትሸ​ከ​ማ​ላ​ችሁ። 2ደግ​ሞም የአ​ባ​ት​ህን የሌ​ዊን ነገድ ወን​ድ​ሞ​ች​ህን ወደ አንተ ሰብ​ስብ፤ ከአ​ን​ተም ጋር በአ​ን​ድ​ነት ይሁኑ፤ ያገ​ል​ግ​ሉ​ህም፤ አንተ ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ችህ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ትሆ​ና​ላ​ችሁ። 3እነ​ር​ሱም ትእ​ዛ​ዝ​ህን የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም ሕግ ይጠ​ብቁ፤ ነገር ግን እን​ዳ​ይ​ሞቱ፥ እና​ን​ተም ደግሞ ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ዳ​ት​ሞቱ፥ እነ​ርሱ ወደ መቅ​ደሱ ዕቃና ወደ መሠ​ዊ​ያው አይ​ቅ​ረቡ። 4ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ጋር በአ​ን​ድ​ነት ይሁኑ፤ ለድ​ን​ኳ​ኑም አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሕግ ይጠ​ብቁ፤ ከባ​ዕድ ወገን የሆነ ሰው ወደ አንተ አይ​ቅ​ረብ። 5እንደ ገና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ቍጣ እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው እና​ንተ የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንና የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ሕግ ጠብቁ። 6እኔም፦ እነሆ፥ ሌዋ​ው​ያ​ንን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ወስ​ጄ​አ​ለሁ፤ የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ያደ​ርጉ ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰጡ ስጦ​ታ​ዎች ናቸው። 7አን​ተም ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ችህ እንደ መሠ​ዊ​ያ​ውና፥ በመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም ውስጥ እን​ዳ​ለው ሥር​ዐት ሁሉ ክህ​ነ​ታ​ች​ሁን ጠብቁ፤ የሀ​ብተ ክህ​ነት አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ች​ሁ​ንም አድ​ርጉ፤ ከሌ​ላም ወገን የሆነ ሰው ቢቀ​ርብ ይገ​ደል።”
ከመ​ሥ​ዋ​ዕቱ የካ​ህ​ናት ድርሻ
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእኔ የለ​ዩ​ትን የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ቍር​ባ​ኔን ሁሉ ትጠ​ብቁ ዘንድ ለአ​ንተ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ለአ​ንተ እስ​ክ​ታ​ረጅ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ችህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ። 9በእ​ሳት ከሚ​ቀ​ር​በው ከተ​ቀ​ደ​ሰው ይህ ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ ለእኔ የሚ​ያ​መ​ጡት መባ​ቸው ሁሉ፥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም ሁሉ፥ የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ፥ የበ​ደ​ላ​ቸ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ፥ ከተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ሁሉ ለአ​ንተ ለል​ጆ​ች​ህም ይሆ​ናል። 10በቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳን ብሉት፤ ወን​ዶች ሁሉ ይብ​ሉት፤ አን​ተም ልጆ​ች​ህም ብሉት፤ ለአ​ንተ የተ​ቀ​ደሰ ነውና። 11ይህም ለእ​ና​ንተ#ዕብ. “ለአ​ንተ” ይላል። ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለስ​ጦታ ያቀ​ረ​ቡ​ትን የመ​ጀ​መ​ሪያ ቍር​ባን ሁሉ ለአ​ንተ ከአ​ን​ተም ጋር ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ልጆ​ችህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ በቤ​ትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብ​ላው። 12ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጡት የፍሬ መጀ​መ​ሪያ ከዘ​ይ​ትና ከወ​ይን ከስ​ን​ዴም የተ​መ​ረ​ጠ​ውን ሁሉ ለአ​ንተ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ 13ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​መ​ጡት በም​ድ​ራ​ቸው ያለው የፍሬ መጀ​መ​ሪያ ሁሉ ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ በቤ​ትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብ​ላው፤ 14በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ የተ​ከ​ለ​ከ​ለው ሁሉ ለአ​ንተ ይሆ​ናል። 15ከሰው እስከ እን​ስሳ ቢሆን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ሥጋ ሁሉ፥ መጀ​መ​ሪያ የሚ​ወ​ለድ ሁሉ ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ ነገር ግን የሰ​ውን በኵ​ራት ፈጽሞ ትቤ​ዠ​ዋ​ለህ፤ ያል​ነ​ጹ​ት​ንም እን​ስ​ሳት በኵ​ራት ትቤ​ዣ​ለህ። 16አንድ ወር የሆ​ነው ልጅ ዋጋው በቤተ መቅ​ደስ ሚዛን አም​ስት ሰቅል ነው። ይኸ​ውም ሃያ አቦሊ ነው። 17ነገር ግን የላ​ሞ​ቹን በኵ​ራት፥ ወይም የበ​ጎ​ቹን በኵ​ራት፥ የፍ​የ​ሎ​ች​ንም በኵ​ራት አት​ቤ​ዥም፤ ቅዱ​ሳን ናቸ​ውና፤ ደማ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ ስባ​ቸ​ው​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን መሥ​ዋ​ዕት ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ። 18ሥጋ​ውም ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ፍር​ምባ እንደ ቀኙም ወርች ለአ​ንተ ይሆ​ናል። 19የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ዩ​ትን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን መባ ሁሉ ለአ​ንተ ከአ​ን​ተም ጋር ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ልጆ​ችህ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ይህም ለአ​ንተ ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግና የሁ​ል​ጊዜ ቃል ኪዳን ነው።” 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን አለው፥ “በም​ድ​ራ​ቸው ርስት አት​ወ​ር​ስም፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ድርሻ አይ​ሆ​ን​ል​ህም፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ድር​ሻ​ህና ርስ​ትህ እኔ ነኝ።
ከመ​ሥ​ዋ​ዕቱ የሌ​ዋ​ው​ያን ድርሻ
21“ለሌ​ዊም ልጆች እነሆ፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ስለ​ሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ዐሥ​ራት ርስት አድ​ርጌ ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለሁ። 22ከዚ​ህም በኋላ ለሞት የሚ​ያ​በቃ በደል እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን አይ​ግቡ። 23ሌዋ​ው​ያን ግን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ይሥሩ፤ እነ​ር​ሱም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል ርስት አይ​ወ​ር​ሱም። 24ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አድ​ር​ገው የሚ​ለ​ዩ​ትን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ዐሥ​ራት ለሌ​ዋ​ው​ያን ርስት አድ​ርጌ ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ርስት አት​ወ​ር​ሱም አል​ኋ​ቸው።”
ሌዋ​ው​ያን የሚ​ሰ​ጡት ዐሥ​ራት
25እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 26“ለሌ​ዋ​ው​ያን እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእ​ና​ንተ ርስት አድ​ርጌ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁን ዐሥ​ራት በተ​ቀ​በ​ላ​ችሁ ጊዜ፥ እና​ን​ተ​ም​ከ​እ​ርሱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አድ​ር​ጋ​ችሁ የዐ​ሥ​ራት ዐሥ​ራት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። 27መባ​ች​ሁም እንደ እህል ዐው​ድ​ማው ስን​ዴና እንደ ወይን መጭ​መ​ቂ​ያው ፍሬ ይቈ​ጠ​ር​ላ​ች​ኋል። 28እን​ዲሁ እና​ንተ ደግሞ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከም​ት​ቀ​በ​ሉት ዐሥ​ራት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አድ​ር​ጋ​ችሁ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መባ ለይ​ታ​ችሁ ለካ​ህኑ ለአ​ሮን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ። 29ከም​ት​ቀ​በ​ሉት ስጦታ ሁሉ፥ ከተ​መ​ረ​ጠው ከተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ድርሻ ሁሉ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የመ​ጀ​መ​ሪያ መባ ሁሉ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። 30ስለ​ዚህ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ ከእ​ርሱ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው በለ​ያ​ችሁ ጊዜ እንደ አው​ድ​ማው እህ​ልና እንደ ወይን መጭ​መ​ቂ​ያው ፍሬ ለሌ​ዋ​ው​ያን ይቈ​ጠ​ር​ላ​ቸ​ዋል። 31እና​ን​ተም ቤተ ሰቦ​ቻ​ች​ሁም፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ የማ​ገ​ል​ገ​ላ​ችሁ ዋጋ ነውና በሁሉ ስፍራ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ። 32የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ው​ንም ከእ​ርሱ ባነ​ሣ​ችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኀጢ​አት አይ​ሆ​ን​ባ​ች​ሁም፤ እን​ዳ​ት​ሞ​ቱም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የቀ​ደ​ሱ​ትን አታ​ር​ክሱ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ