ኦሪት ዘኍልቍ 18
18
የካህናትና የሌዋውያን ተግባር
1እግዚአብሔርም አሮንን እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህና የአባቶችህ ወገኖች፥ የክህነታችሁን ኀጢአት ትሸከማላችሁ። 2ደግሞም የአባትህን የሌዊን ነገድ ወንድሞችህን ወደ አንተ ሰብስብ፤ ከአንተም ጋር በአንድነት ይሁኑ፤ ያገልግሉህም፤ አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ትሆናላችሁ። 3እነርሱም ትእዛዝህን የድንኳኑንም ሕግ ይጠብቁ፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ፥ እናንተም ደግሞ ከእነርሱ ጋር እንዳትሞቱ፥ እነርሱ ወደ መቅደሱ ዕቃና ወደ መሠዊያው አይቅረቡ። 4ነገር ግን ከእናንተ ጋር በአንድነት ይሁኑ፤ ለድንኳኑም አገልግሎት ሁሉ የምስክሩን ድንኳን ሕግ ይጠብቁ፤ ከባዕድ ወገን የሆነ ሰው ወደ አንተ አይቅረብ። 5እንደ ገና በእስራኤል ልጆች ላይ ቍጣ እንዳይሆንባቸው እናንተ የመቅደሱንና የመሠዊያውን ሕግ ጠብቁ። 6እኔም፦ እነሆ፥ ሌዋውያንን ወንድሞቻችሁን ከእስራኤል ልጆች መካከል ወስጄአለሁ፤ የምስክሩን ድንኳን አገልግሎት ያደርጉ ዘንድ ለእግዚአብሔር የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው። 7አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ እንደ መሠዊያውና፥ በመጋረጃውም ውስጥ እንዳለው ሥርዐት ሁሉ ክህነታችሁን ጠብቁ፤ የሀብተ ክህነት አገልግሎታችሁንም አድርጉ፤ ከሌላም ወገን የሆነ ሰው ቢቀርብ ይገደል።”
ከመሥዋዕቱ የካህናት ድርሻ
8እግዚአብሔርም አሮንን ተናገረው፤ እንዲህም አለው፥ “እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ለእኔ የለዩትን የመጀመሪያውን ቍርባኔን ሁሉ ትጠብቁ ዘንድ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ፤ ለአንተ እስክታረጅ፥ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ የዘለዓለም ሕግ እንዲሆን ሰጥቼሃለሁ። 9በእሳት ከሚቀርበው ከተቀደሰው ይህ ለአንተ ይሆናል፤ ለእኔ የሚያመጡት መባቸው ሁሉ፥ ቍርባናቸውም ሁሉ፥ የኀጢአታቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ የበደላቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ ከተቀደሰውም ሁሉ ለአንተ ለልጆችህም ይሆናል። 10በቅዱሰ ቅዱሳን ብሉት፤ ወንዶች ሁሉ ይብሉት፤ አንተም ልጆችህም ብሉት፤ ለአንተ የተቀደሰ ነውና። 11ይህም ለእናንተ#ዕብ. “ለአንተ” ይላል። ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ ያቀረቡትን የመጀመሪያ ቍርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ የዘለዓለም ሕግ እንዲሆን ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው። 12ለእግዚአብሔር ከሚሰጡት የፍሬ መጀመሪያ ከዘይትና ከወይን ከስንዴም የተመረጠውን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ፤ 13ወደ እግዚአብሔር የሚያመጡት በምድራቸው ያለው የፍሬ መጀመሪያ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው፤ 14በእስራኤል ልጆች ዘንድ የተከለከለው ሁሉ ለአንተ ይሆናል። 15ከሰው እስከ እንስሳ ቢሆን፥ ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ሥጋ ሁሉ፥ መጀመሪያ የሚወለድ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትቤዠዋለህ፤ ያልነጹትንም እንስሳት በኵራት ትቤዣለህ። 16አንድ ወር የሆነው ልጅ ዋጋው በቤተ መቅደስ ሚዛን አምስት ሰቅል ነው። ይኸውም ሃያ አቦሊ ነው። 17ነገር ግን የላሞቹን በኵራት፥ ወይም የበጎቹን በኵራት፥ የፍየሎችንም በኵራት አትቤዥም፤ ቅዱሳን ናቸውና፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ ትረጨዋለህ፤ ስባቸውንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን መሥዋዕት ታደርገዋለህ። 18ሥጋውም ለአንተ ይሆናል፤ እንደሚያቀርቡት ፍርምባ እንደ ቀኙም ወርች ለአንተ ይሆናል። 19የእስራኤል ልጆች ለእግዚአብሔር የሚለዩትን የተቀደሰውን መባ ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ሰጥቼሃለሁ፤ ይህም ለአንተ ከአንተም በኋላ ለዘርህ በእግዚአብሔር ፊት የዘለዓለም ሕግና የሁልጊዜ ቃል ኪዳን ነው።” 20እግዚአብሔርም አሮንን አለው፥ “በምድራቸው ርስት አትወርስም፤ በመካከላቸውም ድርሻ አይሆንልህም፤ በእስራኤል ልጆች መካከል ድርሻህና ርስትህ እኔ ነኝ።
ከመሥዋዕቱ የሌዋውያን ድርሻ
21“ለሌዊም ልጆች እነሆ፥ በምስክሩ ድንኳን አገልግሎት ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ዐሥራት ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። 22ከዚህም በኋላ ለሞት የሚያበቃ በደል እንዳይሆንባቸው፥ የእስራኤል ልጆች ወደ ምስክሩ ድንኳን አይግቡ። 23ሌዋውያን ግን የምስክሩን ድንኳን አገልግሎት ይሥሩ፤ እነርሱም ኀጢአታቸውን ይሸከማሉ፤ ለልጅ ልጃችሁም የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል፤ በእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት አይወርሱም። 24ለእግዚአብሔር መባ አድርገው የሚለዩትን የእስራኤልን ልጆች ዐሥራት ለሌዋውያን ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ፤ ስለዚህ፦ በእስራኤል ልጆች መካከል ርስት አትወርሱም አልኋቸው።”
ሌዋውያን የሚሰጡት ዐሥራት
25እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 26“ለሌዋውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ከእናንተ ርስት አድርጌ የሰጠኋችሁን ዐሥራት በተቀበላችሁ ጊዜ፥ እናንተምከእርሱ ለእግዚአብሔር መባ አድርጋችሁ የዐሥራት ዐሥራት ታቀርባላችሁ። 27መባችሁም እንደ እህል ዐውድማው ስንዴና እንደ ወይን መጭመቂያው ፍሬ ይቈጠርላችኋል። 28እንዲሁ እናንተ ደግሞ ከእስራኤል ልጆች ከምትቀበሉት ዐሥራት ሁሉ ለእግዚአብሔር መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ የእግዚአብሔርንም መባ ለይታችሁ ለካህኑ ለአሮን ትሰጣላችሁ። 29ከምትቀበሉት ስጦታ ሁሉ፥ ከተመረጠው ከተቀደሰውም ድርሻ ሁሉ፥ የእግዚአብሔርን የመጀመሪያ መባ ሁሉ ታቀርባላችሁ። 30ስለዚህ ትላቸዋለህ፦ ከእርሱ ከመጀመሪያው በለያችሁ ጊዜ እንደ አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ፍሬ ለሌዋውያን ይቈጠርላቸዋል። 31እናንተም ቤተ ሰቦቻችሁም፥ በምስክሩ ድንኳን ውስጥ የማገልገላችሁ ዋጋ ነውና በሁሉ ስፍራ ትበሉታላችሁ። 32የመጀመሪያውንም ከእርሱ ባነሣችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኀጢአት አይሆንባችሁም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤል ልጆች የቀደሱትን አታርክሱ።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘኍልቍ 18: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ