የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 20

20
ጌታ ለሕ​ዝቡ ከዐ​ለት ውኃ እንደ አፈ​ለቀ
(ዘፀ. 17፥1-7)
1የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝ​ቡም በቃ​ዴስ ተቀ​መጡ፤ ማር​ያ​ምም በዚያ ሞተች፤ ተቀ​በ​ረ​ችም። 2ለማ​ኅ​በ​ሩም ውኃ አል​ነ​በ​ረም፤ ሕዝ​ቡም በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ ተሰ​በ​ሰቡ። 3ሙሴ​ንም ተጣ​ሉት፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገ​ሩት፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞ​ትን ኖሮ፤ 4እኛ፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ንም በዚያ እን​ሞት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማኅ​በር ወደ​ዚህ ምድረ በዳ ለምን አወ​ጣ​ችሁ? 5ዘር ወደ​ማ​ይ​ዘ​ራ​በት፥ በለ​ስና ወይ​ንም፥ ሮማ​ንም፥ የሚ​ጠ​ጣም ውኃ ወደ​ሌ​ለ​በት ወደ​ዚህ ክፉ ስፍራ ታመ​ጡን ዘንድ ከግ​ብፅ ለምን አወ​ጣ​ች​ሁን?” 6ሙሴና አሮ​ንም ከማ​ኅ​በሩ ፊት ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ዳጃፍ ሄደው በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወደቁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው። 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 8“ይህ​ችን በት​ር​ህን ውሰድ፤ አን​ተና ወን​ድ​ምህ አሮ​ንም ማኅ​በ​ሩን ሰብ​ስቡ፤ ዐለ​ቷ​ንም በፊ​ታ​ቸው እዘ​ዟት፤ ውኃ ትሰ​ጣ​ለች፤ ከድ​ን​ጋ​ይ​ዋም ውኃ ታወ​ጡ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ እን​ዲ​ሁም ማኅ​በ​ሩን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ታጠ​ጡ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።” 9ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አዘ​ዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የነ​በ​ረ​ች​ውን በት​ሩን ወሰደ።
10ሙሴና አሮ​ንም ማኅ​በ​ሩን በዐ​ለቷ ፊት ሰብ​ስ​በው፥ “እና​ንተ ዓመ​ፀ​ኞች፥ እን​ግ​ዲህ ስሙ፤ በውኑ ከዚ​ህች ዐለት ውኃን እና​ወ​ጣ​ላ​ችሁ ነበር?” አሏ​ቸው። 11ሙሴም እጁን ዘር​ግቶ ዐለ​ቷን ሁለት ጊዜ በበ​ትሩ መታት፤ ብዙም ውኃ ወጣ፤ ማኅ​በ​ሩም፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ጠጡ። 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ትቀ​ድ​ሱኝ ዘንድ በእኔ አላ​መ​ና​ች​ሁ​ምና ስለ​ዚህ ወደ ሰጠ​ኋ​ችሁ ምድር ይህን ማኅ​በር ይዛ​ችሁ አት​ገ​ቡም” አላ​ቸው። 13የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተከ​ራ​ክ​ረ​ው​በ​ታ​ልና ይህ ውኃ የክ​ር​ክር ውኃ ተባለ። እር​ሱም ቅዱስ መሆኑ የተ​ገ​ለ​ጠ​በት ይህ የክ​ር​ክር ውኃ ነው።
የኤ​ዶም ንጉሥ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን በሀ​ገሩ እን​ዳ​ያ​ልፉ ስለ መከ​ል​ከሉ
14ሙሴም ከቃ​ዴስ ወደ ኤዶ​ም​ያስ ንጉሥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን እን​ዲህ ብሎ ላከ፥ “ወን​ድ​ምህ እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ ይላል፦ ያገ​ኘ​ንን መከራ ሁሉ አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ 15አባ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በግ​ብ​ፅም እጅግ ዘመን ተቀ​መ​ጥን፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም እኛ​ንና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን በደሉ። 16ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጮኽን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ድም​ፃ​ች​ንን ሰማ፤ መል​አ​ክ​ንም ልኮ ከግ​ብፅ አወ​ጣን፤ እነ​ሆም፥ በም​ድ​ርህ ዳርቻ ባለ​ችው ከተማ በቃ​ዴስ ተቀ​ም​ጠ​ናል። 17እባ​ክህ፥ በም​ድ​ርህ ላይ እን​ለፍ፤ ወደ እር​ሻም ወደ ወይ​ንም አን​ገ​ባም፤ ከጕ​ድ​ጓ​ዶ​ችም ውኃን አን​ጠ​ጣም፤ በን​ጉሡ ጎዳና እን​ሄ​ዳ​ለን፤ ዳር​ቻ​ህ​ንም እስ​ክ​ና​ልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አን​ልም።” 18የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ “በእኔ በኩል አታ​ል​ፍም፤ ይህ ካል​ሆነ ግን እን​ዋ​ጋ​ለን፤ በጦ​ርም እቀ​በ​ልህ ዘንድ እወ​ጣ​ለሁ” አለው። 19የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ “በተ​ራ​ራው በኩል እና​ል​ፋ​ለን፤ እኛም ከብ​ቶ​ቻ​ች​ንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እኔም ከብ​ቶ​ችም” ይላል። ከው​ኃህ ብን​ጠጣ ዋጋ​ውን እን​ከ​ፍ​ላ​ለን፤ ይህ ምንም አይ​ደ​ለም፤ በተ​ራ​ራው እን​ለፍ” አሉት። 20እር​ሱም፥ “በእኔ በኩል አታ​ል​ፍም” አለ። የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ በብዙ ሠራ​ዊት በጽኑ እጅ ሊገ​ጥ​መው ወጣ። 21የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ እስ​ራ​ኤል በዳ​ር​ቻው እን​ዲ​ያ​ልፍ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤል ከእ​ርሱ ተመ​ለሰ።
የአ​ሮን ሞት
22ከቃ​ዴ​ስም ተጓዙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሖር ተራራ ሰፈሩ። 23እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ 24“አሮን ወደ ወገኑ ይጨ​መር፤ በክ​ር​ክር ውኃ ዘንድ ስለ አሳ​ዘ​ና​ች​ሁኝ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ ሰጠ​ኋት ምድር አት​ገ​ቡም። 25አሮ​ን​ንና ልጁን አል​ዓ​ዛ​ርን ይዘህ በማ​ኅ​በሩ ሁሉ ፊት ወደ ሖር ተራራ ላይ አም​ጣ​ቸው፤ 26ከአ​ሮ​ንም ልብ​ሱን አውጣ፤ ልጁ​ንም አል​ዓ​ዛ​ርን አል​ብ​ሰው፤ አሮ​ንም ወደ ወገኑ ይጨ​መር፤ በዚ​ያም ይሙት።” 27ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘዘ አደ​ረገ፤ በማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ ፊት እያዩ ወደ ሖር ተራራ አወ​ጣ​ቸው። 28ሙሴም የአ​ሮ​ንን ልብስ አወጣ፤ ልጁ​ንም አል​ዓ​ዛ​ርን አለ​በ​ሰው፤ አሮ​ንም በዚያ በተ​ራ​ራው ራስ ላይ ሞተ፤ ሙሴና አል​ዓ​ዛ​ርም ከተ​ራ​ራው ራስ ላይ ወረዱ። 29ማኅ​በ​ሩም ሁሉ አሮን እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ለአ​ሮን ሠላሳ ቀን አለ​ቀሱ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ