ኦሪት ዘኍልቍ 20
20
ጌታ ለሕዝቡ ከዐለት ውኃ እንደ አፈለቀ
(ዘፀ. 17፥1-7)
1የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ፤ ማርያምም በዚያ ሞተች፤ ተቀበረችም። 2ለማኅበሩም ውኃ አልነበረም፤ ሕዝቡም በሙሴና በአሮን ላይ ተሰበሰቡ። 3ሙሴንም ተጣሉት፤ እንዲህም ብለው ተናገሩት፥ “ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞትን ኖሮ፤ 4እኛ፥ ከብቶቻችንም በዚያ እንሞት ዘንድ የእግዚአብሔርን ማኅበር ወደዚህ ምድረ በዳ ለምን አወጣችሁ? 5ዘር ወደማይዘራበት፥ በለስና ወይንም፥ ሮማንም፥ የሚጠጣም ውኃ ወደሌለበት ወደዚህ ክፉ ስፍራ ታመጡን ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣችሁን?” 6ሙሴና አሮንም ከማኅበሩ ፊት ወደ ምስክሩ ድንኳን ዳጃፍ ሄደው በግንባራቸው ወደቁ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠላቸው። 7እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 8“ይህችን በትርህን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮንም ማኅበሩን ሰብስቡ፤ ዐለቷንም በፊታቸው እዘዟት፤ ውኃ ትሰጣለች፤ ከድንጋይዋም ውኃ ታወጡላቸዋላችሁ፤ እንዲሁም ማኅበሩን፥ ከብቶቻቸውንም ታጠጡላቸዋላችሁ።” 9ሙሴም እግዚአብሔር እንደ አዘዘው በእግዚአብሔር ፊት የነበረችውን በትሩን ወሰደ።
10ሙሴና አሮንም ማኅበሩን በዐለቷ ፊት ሰብስበው፥ “እናንተ ዓመፀኞች፥ እንግዲህ ስሙ፤ በውኑ ከዚህች ዐለት ውኃን እናወጣላችሁ ነበር?” አሏቸው። 11ሙሴም እጁን ዘርግቶ ዐለቷን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታት፤ ብዙም ውኃ ወጣ፤ ማኅበሩም፥ ከብቶቻቸውም ጠጡ። 12እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፥ “በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋችሁ ምድር ይህን ማኅበር ይዛችሁ አትገቡም” አላቸው። 13የእስራኤል ልጆች ተከራክረውበታልና ይህ ውኃ የክርክር ውኃ ተባለ። እርሱም ቅዱስ መሆኑ የተገለጠበት ይህ የክርክር ውኃ ነው።
የኤዶም ንጉሥ እስራኤላውያን በሀገሩ እንዳያልፉ ስለ መከልከሉ
14ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ፥ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ ያገኘንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ፤ 15አባቶቻችን ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በግብፅም እጅግ ዘመን ተቀመጥን፤ ግብፃውያንም እኛንና አባቶቻችንን በደሉ። 16ወደ እግዚአብሔርም ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ድምፃችንን ሰማ፤ መልአክንም ልኮ ከግብፅ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል። 17እባክህ፥ በምድርህ ላይ እንለፍ፤ ወደ እርሻም ወደ ወይንም አንገባም፤ ከጕድጓዶችም ውኃን አንጠጣም፤ በንጉሡ ጎዳና እንሄዳለን፤ ዳርቻህንም እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።” 18የኤዶምያስም ንጉሥ “በእኔ በኩል አታልፍም፤ ይህ ካልሆነ ግን እንዋጋለን፤ በጦርም እቀበልህ ዘንድ እወጣለሁ” አለው። 19የእስራኤልም ልጆች፥ “በተራራው በኩል እናልፋለን፤ እኛም ከብቶቻችንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እኔም ከብቶችም” ይላል። ከውኃህ ብንጠጣ ዋጋውን እንከፍላለን፤ ይህ ምንም አይደለም፤ በተራራው እንለፍ” አሉት። 20እርሱም፥ “በእኔ በኩል አታልፍም” አለ። የኤዶምያስም ንጉሥ በብዙ ሠራዊት በጽኑ እጅ ሊገጥመው ወጣ። 21የኤዶምያስም ንጉሥ እስራኤል በዳርቻው እንዲያልፍ አልፈቀደም፤ ስለዚህ እስራኤል ከእርሱ ተመለሰ።
የአሮን ሞት
22ከቃዴስም ተጓዙ፤ የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በሖር ተራራ ሰፈሩ። 23እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን በኤዶምያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ 24“አሮን ወደ ወገኑ ይጨመር፤ በክርክር ውኃ ዘንድ ስለ አሳዘናችሁኝ ለእስራኤል ልጆች ወደ ሰጠኋት ምድር አትገቡም። 25አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ በማኅበሩ ሁሉ ፊት ወደ ሖር ተራራ ላይ አምጣቸው፤ 26ከአሮንም ልብሱን አውጣ፤ ልጁንም አልዓዛርን አልብሰው፤ አሮንም ወደ ወገኑ ይጨመር፤ በዚያም ይሙት።” 27ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘ አደረገ፤ በማኅበሩም ሁሉ ፊት እያዩ ወደ ሖር ተራራ አወጣቸው። 28ሙሴም የአሮንን ልብስ አወጣ፤ ልጁንም አልዓዛርን አለበሰው፤ አሮንም በዚያ በተራራው ራስ ላይ ሞተ፤ ሙሴና አልዓዛርም ከተራራው ራስ ላይ ወረዱ። 29ማኅበሩም ሁሉ አሮን እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ፥ የእስራኤል ቤት ሁሉ ለአሮን ሠላሳ ቀን አለቀሱ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኍልቍ 20: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ