የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 22

22
ባላቅ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንን እን​ዲ​ረ​ግ​ም​ለት በለ​ዓ​ምን እንደ አስ​ጠራ
1የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተጓዙ፤ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በሞ​ዓብ ምዕ​ራ​ብም ሰፈሩ።
2የሴ​ፎር ልጅ ባላቅ እስ​ራ​ኤል በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ አየ። 3ብዙም ነበ​ረና ሞዓብ ከሕ​ዝቡ እጅግ ፈራ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የተ​ነሣ ሞዓብ ደነ​ገጠ። 4ሞዓ​ብም የም​ድ​ያ​ምን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “በሬ የለ​መ​ለ​መ​ውን ሣር እን​ደ​ሚ​ጨ​ርስ ይህ ሠራ​ዊት በዙ​ሪ​ያ​ችን ያለ​ውን ሁሉ ይጨ​ር​ሳል” አላ​ቸው። በዚ​ያን ጊዜ የሶ​ፎር ልጅ ባላቅ የሞ​ዓብ ንጉሥ ነበረ። 5በወ​ን​ዙም አጠ​ገብ ባለ​ችው በሕ​ዝቡ ልጆች ምድር በፋ​ቱራ ወደ ተቀ​መ​ጠው ወደ ቢዖር ልጅ ወደ በለ​ዓም፥ “እነሆ፥ ከግ​ብፅ የወጣ ሕዝብ አለ፤ 6እነ​ሆም፥ የም​ድ​ሩን ሁሉ ፊት ሸፈነ፤ በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያ​ች​ንም ተቀ​ም​ጦ​አል፤ አሁ​ንም ይህ ሕዝብ ከእኔ ይበ​ል​ጣ​ልና ልወ​ጋ​ቸ​ውና ከም​ድ​ሪቱ ላሳ​ድ​ዳ​ቸው እችል እንደ ሆነ፥ ና ርገ​ም​ልኝ፤ አንተ የመ​ረ​ቅ​ኸው ምሩቅ፥ የረ​ገ​ም​ኸ​ውም ርጉም እንደ ሆነ አው​ቃ​ለ​ሁና” ብሎ ይጠ​ሩት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።
7የሞ​ዓብ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የም​ድ​ያም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም የም​ዋ​ር​ቱን ዋጋ በእ​ጃ​ቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለ​ዓ​ምም መጡ፤ የባ​ላ​ቅ​ንም ቃል ነገ​ሩት። 8እር​ሱም፥ “ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ፤ እግ​ዚ​እ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ነ​ግ​ረ​ኝን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው፤ የሞ​ዓብ አለ​ቆ​ችም በበ​ለ​ዓም ዘንድ አደሩ። 9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ በለ​ዓም መጥቶ፥ “እነ​ዚህ በአ​ንተ ዘንድ ያሉ ሰዎች እነ​ማን ናቸው?” አለው። 10በለ​ዓ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ አለው፥ “የሞ​ዓብ ንጉሥ የሶ​ፎር ልጅ ባላቅ፦ እን​ዲህ ሲል ወደ እኔ ልኮ​አ​ቸ​ዋል፤ 11እነሆ፥ ከግ​ብፅ የወጣ ሕዝብ የም​ድ​ርን ፊት ሸፈነ፤ በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያ​ዬም ተቀ​ም​ጦ​አል፤ ምና​ል​ባት እወ​ጋው፥ አሳ​ድ​ደ​ውም ዘንድ እችል እንደ ሆነ አሁ​ንም ና እር​ሱን ርገ​ም​ልኝ።” 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በለ​ዓ​ምን፥ “ከእ​ነ​ርሱ ጋር አት​ሂድ፤ የተ​ባ​ረከ ነውና ሕዝ​ቡን አት​ር​ገም” አለው። 13በለ​ዓ​ምም ሲነጋ ተነ​ሥቶ የባ​ላ​ቅን አለ​ቆች፥ “ከእ​ና​ንተ ጋር እሄድ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ፈ​ቀ​ደ​ል​ኝ​ምና ወደ ጌታ​ችሁ ሂዱ” አላ​ቸው። 14የሞ​ዓብ አለ​ቆ​ችም ተነሡ፤ ወደ ባላ​ቅም መጥ​ተው፥ “በለ​ዓም ከእኛ ጋር ይመጣ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም” አሉት።
15ባላ​ቅም ደግሞ ከእ​ነ​ዚያ የበ​ዙና የከ​በሩ ሌሎ​ችን አለ​ቆች ሰደደ። 16ወደ በለ​ዓ​ምም መጥ​ተው፥ “የሶ​ፎር ልጅ ባላቅ፦ እባ​ክህ ወደ እኔ መም​ጣ​ትን ቸል አት​በል፤ 17ክብ​ር​ህን እጅግ ታላቅ አደ​ር​ገ​ዋ​ለ​ሁና፥ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ው​ንም ሁሉ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለ​ሁና ና፥ ይህን ሕዝብ ርገ​ም​ልኝ ብሏል” አሉት። 18በለ​ዓ​ምም መልሶ የባ​ላ​ቅን አለ​ቆች፥ “ባላቅ በቤቱ የሞ​ላ​ውን ወር​ቅና ብር ቢሰ​ጠኝ፥ በት​ንሹ ወይም በት​ልቁ ቢሆን የአ​ም​ላ​ኬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እተ​ላ​ለፍ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም፤ 19አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደግሞ የሚ​ነ​ግ​ረ​ኝን አውቅ ዘንድ ዛሬ ሌሊት ደግሞ በዚህ እደሩ” አላ​ቸው። 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ በለ​ዓም በሌ​ሊት መጥቶ፥ “ሰዎቹ ይጠ​ሩህ ዘንድ መጥ​ተው እንደ ሆነ፥ ተነሣ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የም​ነ​ግ​ር​ህን ቃል ታደ​ር​ጋ​ለህ” አለው።
በለ​ዓ​ምና አህ​ያው
21በለ​ዓ​ምም ሲነጋ ተነሣ፤ አህ​ያ​ዪ​ቱ​ንም ጭኖ ከሞ​ዓብ አለ​ቆች ጋር ሄደ። 22እር​ሱም ስለ ሄደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቈጣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ሊያ​ሰ​ና​ክ​ለው ተነሣ።#ዕብ. “በመ​ን​ገድ ላይ ቆመ” ይላል። 23እር​ሱም በአ​ህ​ያ​ዪቱ ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ሁለ​ቱም ብላ​ቴ​ና​ዎቹ ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ። አህ​ያ​ዪ​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ በመ​ን​ገድ ላይ ቆሞ የተ​መ​ዘ​ዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየች፤ ከመ​ን​ገ​ዱም ላይ ፈቀቅ ብላ ወደ ሜዳ ውስጥ ገባች፤ በለ​ዓ​ምም ወደ መን​ገድ ይመ​ል​ሳት ዘንድ አህ​ያ​ዪ​ቱን መታት። 24የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከወ​ይኑ ቦታ​ዎች መካ​ከል በወ​ዲ​ያና በወ​ዲህ ወገን ግንብ በነ​በ​ረ​በት ቆመ። 25አህ​ያ​ዪ​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ አይታ ወደ ቅጥሩ ተጠ​ጋች፤ የበ​ለ​ዓ​ም​ንም እግ​ሩን ላጠ​ችው፤#ዕብ. “የበ​ለ​ዓ​ምን እግር ከቅ​ጥሩ ጋር አጣ​በ​ቀች” ይላል። እር​ሱም ደግሞ መታት። 26የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወደ ፊት ሄደ፤ በቀ​ኝና በግራ መተ​ላ​ለ​ፊያ በሌ​ለ​በት በጠ​ባብ ስፍራ ቆመ። 27አህ​ያ​ዪ​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ አየች፤ ከበ​ለ​ዓ​ምም በታች ተኛች፤ በለ​ዓ​ምም ተቈጣ፤ አህ​ያ​ዪ​ቱ​ንም በበ​ትሩ ደበ​ደ​ባት። 28እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የአ​ህ​ያ​ዪ​ቱን አፍ ከፈተ፤ በለ​ዓ​ም​ንም፥ “ሦስት ጊዜ የመ​ታ​ኸኝ ምን አድ​ር​ጌ​ብህ ነው?” አለ​ችው። 29በለ​ዓ​ምም አህ​ያ​ዪ​ቱን፥ “ስለ​ዘ​በ​ት​ሽ​ብኝ ነው፤ በእ​ጄስ ሰይፍ ቢኖር አሁን በገ​ደ​ል​ሁሽ ነበር” አላት። 30አህ​ያ​ዪ​ቱም በለ​ዓ​ምን፥ “ከወ​ጣ​ት​ነ​ትህ ጀምሮ እስከ ዛሬ የም​ት​ቀ​መ​ጥ​ብኝ አህ​ያህ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? በውኑ አን​ተን ቸል ያል​ሁ​በት፥ በአ​ን​ተም እን​ዲህ ያደ​ረ​ግ​ሁ​በት ጊዜ ነበ​ርን?” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ግ​ሽ​ብ​ኝም” አላት።
31እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የበ​ለ​ዓ​ምን ዐይ​ኖች ከፈተ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መል​አክ በመ​ን​ገድ ላይ ቆሞ፥ የተ​መ​ዘ​ዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ሰገ​ደ​ለት። 32የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “አህ​ያ​ህን ሦስት ጊዜ ለምን መታህ? እነሆ፥ መን​ገ​ድህ በፊቴ ቀና አል​ነ​በ​ረ​ምና ላሰ​ና​ክ​ልህ ወጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ 33አህ​ያ​ዪ​ቱም አይ​ታኝ ከፊቴ ፈቀቅ አለች፤ ይህም ሦስ​ተኛ ጊዜ ነው፤ ከፊ​ቴስ ፈቀቅ ባላ​ለች በእ​ው​ነት አሁን አን​ተን በገ​ደ​ል​ሁህ፤ እር​ሷ​ንም ባዳ​ን​ኋት ነበር” አለው። 34በለ​ዓ​ምም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ፥ “በድ​ያ​ለሁ፤ አንተ በመ​ን​ገድ ላይ በፊቴ እንደ ቆም​ህ​ብኝ አላ​ወ​ቅ​ሁም፤ እን​ግ​ዲህ አሁን አት​ወ​ድድ እን​ደ​ሆነ እመ​ለ​ሳ​ለሁ” አለው። 35የእ​ግ​ዚ​እ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በለ​ዓ​ምን፥ “ከሰ​ዎቹ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የም​ና​ገ​ር​ህን ቃል ብቻ ለመ​ና​ገር ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። በለ​ዓ​ምም ከባ​ላቅ አለ​ቆች ጋር ሄደ።
36“ባላ​ቅም በለ​ዓም እንደ መጣ በሰማ ጊዜ ከዳ​ር​ቻ​ዎች በአ​ን​ደኛ ክፍል በአ​ለ​ችው በአ​ር​ኖን ዳርቻ ወደ አለ​ችው ወደ ሞዓብ ከተማ ሊገ​ና​ኘው ወጣ። 37ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን፥ “አን​ተን ለመ​ጥ​ራት የላ​ክ​ሁ​ብህ አይ​ደ​ለ​ምን? ለም​ንስ ወደ እኔ አል​መ​ጣ​ህም? አን​ተን ለማ​ክ​በር እኔ አል​ች​ል​ምን?” አለው። 38በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን፥ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ አሁን አን​ዳ​ችን ነገር ለመ​ና​ገር እች​ላ​ለ​ሁን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፌ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ቃል እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለው። 39በለ​ዓ​ምም ከባ​ላቅ ጋር ሄደ፤ ወደ ቅጽር ግቢ​ውም#ዕብ. “ወደ ቂር​ያት ሐጾ​ትም” ይላል። ገቡ። 40ባላ​ቅም በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ችን አርዶ ወደ በለ​ዓም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ወዳ​ሉት አለ​ቆች ላከ። 41በነ​ጋ​ውም ባላቅ በለ​ዓ​ምን ይዞ ወደ በአል ኮረ​ብታ አወ​ጣው፤ በዚ​ያም ሆኖ የሕ​ዝ​ቡን አንድ ወገን አሳ​የው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ