የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 23

23
የበ​ለ​ዓም የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ትን​ቢት
1በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን፥ “ሰባት መሠ​ዊያ በዚህ ሥራ​ልኝ፤ ሰባ​ትም ወይ​ፈን፥ ሰባ​ትም አውራ በግ በዚህ አዘ​ጋ​ጅ​ልኝ” አለው። 2ባላ​ቅም በለ​ዓም እንደ ተና​ገረ አደ​ረገ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አንድ ወይ​ፈ​ንና አንድ አውራ በግ አሳ​ረገ። 3በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን፥ “በመ​ሥ​ዋ​ዕ​ትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢገ​ለ​ጥ​ልኝ፥ ቢገ​ና​ኘ​ኝም እሄ​ዳ​ለሁ፤ የሚ​ገ​ል​ጥ​ል​ኝ​ንም ቃል እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” አለው። ባላ​ቅም በመ​ሠ​ዊ​ያው ዘንድ ቆመ፤ በለ​ዓም ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይጠ​ይቅ ዘንድ አቅ​ንቶ ሄደ።#ዕብ. “ወደ ጕብ​ታው ሄደ” ይላል። 4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለበ​ለ​ዓም ታየው፤ በለ​ዓ​ምም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “እነሆ፥ ሰባት መሠ​ዊ​ያ​ዎች አዘ​ጋ​ጀሁ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ አንድ ወይ​ፈ​ንና አንድ አውራ በግ አሳ​ረ​ግሁ” አለው። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በበ​ለ​ዓም አፍ ቃልን አኖረ፤ “ወደ ባላቅ ተመ​ለስ፤ እን​ዲ​ህም በል” አለው። 6ወደ እር​ሱም ተመ​ለሰ፤ እነ​ሆም፥ እር​ሱና የሞ​ዓብ አለ​ቆች ሁሉ በመ​ሥ​ዋ​ዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ወደ እርሱ መጣ፤ 7በም​ሳ​ሌም ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦
“የሞ​ዓብ ንጉሥ ባላቅ ከም​ሥ​ራቅ ተራ​ሮች፤ ከሜ​ስ​ጴ​ጦ​ምያ ጠርቶ አመ​ጣኝ፤
ና፥ ያዕ​ቆ​ብን ርገ​ም​ልኝ፤
ና፥ እስ​ራ​ኤ​ልን ተጣ​ላ​ልኝ” ብሎ።
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያል​ረ​ገ​መ​ውን እን​ዴት እረ​ግ​ማ​ለሁ?
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ያል​ተ​ጣ​ላ​ውን እን​ዴት እጣ​ላ​ለሁ?
9በተ​ራ​ሮች ራስ ላይ ሆኜ አየ​ዋ​ለሁ፤
በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ላይ ሆኜ እመ​ለ​ከ​ተ​ዋ​ለሁ፤
እነሆ፥ ብቻ​ውን የሚ​ቀ​መጥ ሕዝብ ነው፤
በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል አይ​ቈ​ጠ​ርም።
10የያ​ዕ​ቆ​ብን ዘር ማን ያው​ቀ​ዋል?
የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንስ ሕዝብ ማን ይቈ​ጥ​ረ​ዋል?
ሰው​ነ​ቴም ከጻ​ድ​ቃን ሰው​ነት ጋር ትሙት፤
ዘሬም እንደ እነ​ርሱ ዘር ትሁን።”
11ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን፥ “ያደ​ረ​ግ​ኽ​ብኝ ምን​ድን ነው? ጠላ​ቶ​ችን ትረ​ግ​ም​ልኝ ዘንድ ጠራ​ሁህ፤ እነ​ሆም፥ መባ​ረ​ክን ባረ​ክ​ሃ​ቸው” አለው። 12በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን መልሶ፥ “በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፌ ያደ​ረ​ገ​ውን እና​ገር ዘንድ የም​ጠ​ነ​ቀቅ አይ​ደ​ለ​ምን?”
የበ​ለ​ዓም ሁለ​ተ​ኛው ትን​ቢት
13ባላ​ቅም፥ “በዚያ እነ​ር​ሱን ወደ​ማ​ታ​ይ​በት ወደ ሌላ ቦታ እባ​ክህ፥ ከእኔ ጋር ና፤ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዱን ወገን ብቻ ታያ​ለህ፤ ሁሉን ግን አታ​ይም፤ በዚ​ያም እነ​ር​ሱን ርገ​ም​ልኝ” አለው። 14በሜዳ ወደ ተገ​ነባ ግንብ ራስ ላይም ወሰ​ደው፤ አዞ​ረ​ውም፤ ሰባ​ትም መሠ​ዊ​ያ​ዎች ሠራ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ አንድ ወይ​ፈን፥ አን​ድም አውራ በግ አሳ​ረገ። 15በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን አለው፥ “በዚህ በመ​ሥ​ዋ​ዕ​ትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ይቅ ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ።” 16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በለ​ዓ​ምን ተገ​ና​ኘው፤ ቃል​ንም በአፉ አኖረ፥ “ወደ ባላቅ ተመ​ለስ፤ እን​ዲ​ህም በለው።” 17ወደ እር​ሱም መጣ፤ እነሆ፥ እርሱ ከእ​ር​ሱም ጋር የሞ​ዓብ አለ​ቆች በመ​ሥ​ዋ​ዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን አለ?” 18በም​ሳ​ሌም ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦
“ባላቅ ሆይ፥ ተነሣ፤ ስማ፤
የሶ​ፎር ልጅ ሆይ፥ ምስ​ክር ሁነህ አድ​ምጥ፤
19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰው የሚ​ታ​ለል አይ​ደ​ለም።
እንደ ሰው ልጅም የሚ​ዛ​ት​በት አይ​ደ​ለም፤
እርሱ ያለ​ውን አያ​ደ​ር​ገ​ው​ምን?
አይ​ና​ገ​ረ​ው​ምን? አይ​ፈ​ጽ​መ​ው​ምን?
20እነሆ፥ መጥ​ቻ​ለሁ፤ እባ​ር​ካ​ለሁ፤ አል​መ​ለ​ስ​ምም፤
21በያ​ዕ​ቆብ ላይ ድካም የለም፤
በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕማም አይ​ታ​ይም፤
አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነው፤
የአ​ለ​ቆ​ችም ክብር ለእ​ርሱ ነው።
22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ያወ​ጣው እርሱ
ጕል​በቱ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ክብር ነው።
23በያ​ዕ​ቆብ ላይ ጥን​ቆላ የለም፤
በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ምዋ​ርት የለም፤
በየ​ጊ​ዜው ስለ ያዕ​ቆ​ብና ስለ እስ​ራ​ኤል፦
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን አደ​ረገ? ይባ​ላል።
24እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ አን​በሳ ደቦል ያገ​ሣል፤
እንደ አን​በ​ሳም ይነ​ሣል፤
ያደ​ነ​ውን እስ​ኪ​በላ፥
የገ​ደ​ለ​ው​ንም ደሙን እስ​ኪ​ጠጣ አይ​ተ​ኛም።”
25ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን አለው፥ “ከቶ አት​ር​ገ​ማ​ቸው፤ ከቶም አት​ባ​ር​ካ​ቸው።” 26በለ​ዓ​ምም መልሶ ባላ​ቅን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ኝን ቃል ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ ብዬ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁ​ህ​ምን?”
የበ​ለ​ዓም ሦስ​ተ​ኛው ትን​ቢት
27ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን አለው፥ “ና፥ ወደ ሌላ ስፍራ እወ​ስ​ድ​ሃ​ለሁ፤ ምና​ል​ባት በዚህ ሆነህ እነ​ር​ሱን ትረ​ግ​ም​ልኝ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይወ​ድድ ይሆ​ናል።” 28ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን በም​ድረ በዳ ወደ ተከ​በ​በው ወደ ፌጎር ተራራ ወሰ​ደው። 29በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን፥ “በዚህ ሰባት መሠ​ዊ​ያ​ዎች ሥራ​ልኝ፤ በዚ​ህም ሰባት ወይ​ፈን፥ ሰባ​ትም አውራ በግ አዘ​ጋ​ጅ​ልኝ” አለው። 30ባላ​ቅም በለ​ዓም እን​ዳ​ለው አደ​ረገ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ አንድ ወይ​ፈ​ንና አንድ አውራ በግ አሳ​ረገ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ