የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 35

35
ለሌ​ዋ​ው​ያን የተ​ሰጡ ከተ​ሞች
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 2“ሌዋ​ው​ያን የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ውን ከተ​ሞች ከሚ​ካ​ፈ​ሉት ርስ​ታ​ቸው ይሰጡ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እዘ​ዛ​ቸው፤ በከ​ተ​ሞ​ቹም ዙሪያ ያሉ​ትን መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎች ለሌ​ዋ​ው​ያን ይስ​ጡ​አ​ቸው። 3ከተ​ሞ​ቹም ለእ​ነ​ርሱ መኖ​ሪያ ይሆ​ናሉ፤ መሰ​ማ​ር​ያ​ቸ​ውም ለከ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ለእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው ይሁን። 4ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም የም​ት​ሰ​ጡት የከ​ተማ መሰ​ማ​ርያ በከ​ተ​ማው ዙሪያ ከቅ​ጥሩ ወደ ውጭ አንድ ሺህ ክንድ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሁለት ሺህ ክንድ” ይላል። ይሁን። 5ከከ​ተ​ማው ውጭ በም​ሥ​ራቅ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፥ በደ​ቡብ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፥ በም​ዕ​ራብ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፥ በሰ​ሜ​ንም በኩል ሁለት ሺህ ክንድ ትከ​ነ​ዳ​ላ​ችሁ፤ ከተ​ማ​ውም በመ​ካ​ከል ይሆ​ናል፤ ይህም የከ​ተ​ሞቹ መሰ​ማ​ርያ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል። 6ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ከተ​ሞ​ችን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ከም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውም ከተ​ሞች ስድ​ስቱ ነፍሰ ገዳይ የሚ​ሸ​ሽ​ባ​ቸው የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች ናቸው፤ ከእ​ነ​ዚህ ሌላ አርባ ሁለት ከተ​ሞ​ችን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ። 7ለሌ​ዋ​ው​ያን የም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸው ከተ​ሞች ሁሉ አርባ ስም​ንት ከተ​ሞች ይሆ​ናሉ፤ እነ​ዚ​ህም ከመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር ናቸው። 8ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት ለሌ​ዋ​ው​ያን የም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ከተ​ሞች እን​ዲህ ስጡ፤ ከብ​ዙ​ዎቹ ብዙ፥ ከጥ​ቂ​ቶቹ ጥቂት ትወ​ስ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ ወረ​ሱት እንደ ርስ​ታ​ቸው መጠን ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ይሰ​ጣሉ።”
የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች
(ዘዳ. 19፥1-13ኢያ. 20፥1-9)
9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 10“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ 11እነሆ፥ ወደ ከነ​ዓን ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ባላ​ማ​ወቅ ነፍስ የገ​ደለ ወደ​ዚያ ይሸሽ ዘንድ የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ችሁ ከተ​ሞ​ችን ለእ​ና​ንተ ለዩ። 12ነፍሰ ገዳዩ በማ​ኅ​በሩ ፊት ለፍ​ርድ እስ​ከ​ሚ​ቆም ድረስ እን​ዳ​ይ​ሞት፥ ከተ​ሞቹ ከደም ተበ​ቃይ የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ። 13የም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውም ስድ​ስቱ ከተ​ሞች የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ። 14በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ሦስት ከተ​ሞ​ችን ትለ​ያ​ላ​ችሁ፤ በከ​ነ​ዓ​ንም ምድር ሦስት ከተ​ሞ​ችን ትለ​ያ​ላ​ችሁ፤ የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞ​ችም ይሆ​ናሉ። 15ባለ​ማ​ወቅ ነፍስ የገ​ደለ ሁሉ ይሸ​ሽ​ባ​ቸው ዘንድ እነ​ዚህ ስድ​ስት ከተ​ሞች ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለሚ​ቀ​መጡ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች መማ​ፀኛ ይሆ​ናሉ።
16“በብ​ረት መሣ​ሪያ ቢመ​ታው፥ ቢሞ​ትም ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳ​ዩም ፈጽሞ ይገ​ደል። 17ሰውም በሚ​ሞ​ት​በት በእጁ ባለው ድን​ጋይ ቢመ​ታው፥ የተ​መ​ታ​ውም ቢሞት፥ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳ​ዩም ፈጽሞ ይገ​ደል። 18ሰውም በሚ​ሞ​ት​በት በእጁ ባለው በእ​ን​ጨት መሣ​ሪያ ቢመ​ታው፥ የተ​መ​ታ​ውም ቢሞት፥ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳ​ዩም ፈጽሞ ይገ​ደል። 19ደም ተበ​ቃዩ ራሱ ነፍሰ ገዳ​ዩን ይግ​ደል፤ ባገ​ኘው ጊዜ ይግ​ደ​ለው። 20ጥል ቢጣ​ላው፥ ወይም ሸምቆ አን​ዳች ነገር ቢጥ​ል​በት፥ ቢሞ​ትም፥ 21ወይም በጥ​ላቻ እስ​ኪ​ሞት ድረስ በእጁ ቢመ​ታው፥ የመ​ታው ፈጽሞ ይገ​ደል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ባለ ደሙ ወይም ተበ​ቃዩ ባገ​ኘው ጊዜ ነፍሰ ገዳ​ዩን ይግ​ደ​ለው።
22“ነገር ግን ያለ ጥላቻ ድን​ገት ቢደ​ፋው፥ ሳይ​ሸ​ም​ቅም አን​ዳች ነገር ቢጥ​ል​በት፥ 23ወይም ሳያ​የው እስ​ኪ​ሞት ድረስ ሰው የሚ​ሞ​ት​በ​ትን ድን​ጋይ ቢጥ​ል​በት፥ 24ጠላ​ቱም ባይ​ሆን፥ ክፉም ያደ​ር​ግ​በት ዘንድ ባይሻ፥ ማኅ​በሩ በመ​ቺ​ውና በባለ ደሙ መካ​ከል ፍር​ድን እን​ደ​ዚህ ይፍ​ረዱ፤ 25ማኅ​በ​ሩም ነፍሰ ገዳ​ዩን ከባለ ደሙ እጅ ያድ​ኑ​ታል፤ ማኅ​በ​ሩም ወደ ሸሸ​በት ወደ መማ​ፀ​ኛው ከተማ ይመ​ል​ሱ​ታል፤ በቅ​ዱስ ዘይ​ትም የተ​ቀ​ባው ታላቁ ካህን እስ​ኪ​ሞት ድረስ በዚያ ይቀ​መ​ጣል። 26ነፍሰ ገዳዩ ግን ከሸ​ሸ​በት ከመ​ማ​ፀ​ኛው ከተማ ዳርቻ ቢወጣ፥ ባለ ደሙም ከመ​ማ​ፀ​ኛው ከተማ ዳርቻ ውጭ ቢያ​ገ​ኘው፥ 27ባለ ደሙም ነፍሰ ገዳ​ዩን ቢገ​ድ​ለው፥ በደል የለ​በ​ትም፤ 28ታላቁ ካህን እስ​ኪ​ሞት ድረስ በመ​ማ​ፀ​ኛው ከተማ ውስጥ መቀ​መጥ ይገ​ባው ነበ​ርና። ታላቁ ካህን ከሞተ በኋላ ግን ነፍሰ ገዳዩ ወደ ርስቱ ምድር ይመ​ለ​ሳል።
29“እነ​ዚ​ህም ነገ​ሮች ለልጅ ልጃ​ችሁ በማ​ደ​ሪ​ያ​ችሁ ሁሉ ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ። 30ነፍሰ ገዳይ ሁሉ በም​ስ​ክ​ሮች ቃል ይገ​ደ​ላል፤ በአ​ንድ ምስ​ክር ግን ማና​ቸ​ው​ንም ሰው መግ​ደል አይ​ገ​ባም። 31ሞት የተ​ፈ​ረ​ደ​በ​ትን ነፍሰ ገዳ​ዩ​ንም ለማ​ዳን የነ​ፍስ ዋጋ አት​ቀ​በሉ፤ እርሱ ፈጽሞ ይገ​ደል። 32ታላቁ ካህን እስ​ኪ​ሞት ወደ ምድሩ ትመ​ል​ሱት ዘንድ ወደ መማ​ፀ​ኛው ከተማ ከሸ​ሸው ዋጋ አት​ቀ​በሉ። 33ምድ​ርን የሚ​ያ​ረ​ክ​ሳት ደም ነውና የም​ት​ኖ​ሩ​ባ​ትን ምድር በነ​ፍስ ግድያ አታ​ር​ክ​ሷት። ምድ​ሪ​ቱም በደም አፍ​ሳሹ ደም ካል​ሆነ በቀር ከፈ​ሰ​ሰ​ባት ደም አት​ነ​ጻም። 34እና​ንተ በው​ስ​ጥዋ የም​ት​ኖ​ሩ​ባ​ትን፥ እኔም ከእ​ና​ንተ ጋር የማ​ድ​ር​ባ​ትን ምድር አታ​ር​ክ​ሱ​ኣት፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል የማ​ድር እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ