ኦሪት ዘኍልቍ 36
36
ለአገቡ ሴቶች የተመደበ ርስት
1ከዮሴፍ ልጆች ወገኖች የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጆች ወገን አለቆች መጡ፤ በሙሴና በካህኑ በአልዓዛር፥ በእስራኤልም ልጆች አባቶች አለቆች ፊት ተናገሩ፤ አሉም፦ 2“ምድሪቱን ለእስራኤል ልጆች ርስት አድርጎ በዕጣ ከፍሎ ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር ጌታችንን አዘዘው፤ እግዚአብሔርም የወንድማችንን የሰለጰዓድን ርስት ለሴቶች ልጆቹ ይሰጣቸው ዘንድ ጌታችንን አዘዘው። 3ከሌላም ከእስራኤል ልጆች ነገድ ባል ቢያገቡ፥ ርስታቸው ከአባቶቻችን ርስት ይነቀላል፤ እነርሱም ለሚገቡበት ለሌላው ነገድ ርስት ይጨመራል፤ እንደዚህም የርስታችን ዕጣ ይጐድላል። 4ለእስራኤልም ልጆች ኢዮቤልዩ በሆነ ጊዜ ርስታቸው ሴቶቹ ወደ አገቡበት ወደ ሌላ ነገድ ርስት ይጨመራል፤ እነሆ፥ ርስታቸው ከአባቶቻችን ነገድ ርስት ይጐድላል።”
5ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንደ እግዚአብሔር ቃል እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፥ “የዮሴፍ ልጆች ነገድ በእውነት ተናገሩ። 6እግዚአብሔር ስለ ሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች ያዘዘው ነገር ይህ ነው፤ የወደዱትን ያግቡ፤ ነገር ግን ከአባታቸው ነገድ ብቻ ያግቡ። 7እንደዚህም የእስራኤል ልጆች ርስት ከነገድ ወደ ነገድ ምንም አይተላለፍ፤ ከእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ ወደ አባቶቹ ነገድ ርስት ይጠጋ። 8ከእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ ሰው የአባቶቹን ርስት ይወርስ ዘንድ፥ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ፥ ርስት ያላት ሴት ልጅ ሁሉ ከአባቷ ነገድ ባል ታግባ። 9እንደዚህም ከአንድ ነገድ ወደ ሌላ ነገድ ምንም ርስት አይተላለፍ። ከእስራኤልም ልጆች ነገድ እያንዳንዱ ወደ ርስቱ ይጠጋ።”
10እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች አደረጉ። 11የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች መሐላ፥ ቴርሳ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ኑኃ ከአባታቸው ወንድሞች ልጆች ጋር ተጋቡ። 12ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ልጆች ወገኖች ባሎቻቸውን አገቡ፥ ርስታቸውም በአባታቸው ነገድ ጸና።
13እግዚአብሔር በሙሴ እጅ የእስራኤልን ልጆች በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ምዕራብ ያዘዛቸው ትእዛዝ፥ ሥርዐትና ፍርድ እነዚህ ናቸው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኍልቍ 36: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ