የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 36

36
ለአ​ገቡ ሴቶች የተ​መ​ደበ ርስት
1ከዮ​ሴፍ ልጆች ወገ​ኖች የም​ናሴ ልጅ የማ​ኪር ልጅ የገ​ለ​ዓድ ልጆች ወገን አለ​ቆች መጡ፤ በሙ​ሴና በካ​ህኑ በአ​ል​ዓ​ዛር፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አባ​ቶች አለ​ቆች ፊት ተና​ገሩ፤ አሉም፦ 2“ምድ​ሪ​ቱን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት አድ​ርጎ በዕጣ ከፍሎ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጌታ​ች​ንን አዘ​ዘው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የወ​ን​ድ​ማ​ች​ንን የሰ​ለ​ጰ​ዓ​ድን ርስት ለሴ​ቶች ልጆቹ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ጌታ​ች​ንን አዘ​ዘው። 3ከሌ​ላም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገድ ባል ቢያ​ገቡ፥ ርስ​ታ​ቸው ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ርስት ይነ​ቀ​ላል፤ እነ​ር​ሱም ለሚ​ገ​ቡ​በት ለሌ​ላው ነገድ ርስት ይጨ​መ​ራል፤ እን​ደ​ዚ​ህም የር​ስ​ታ​ችን ዕጣ ይጐ​ድ​ላል። 4ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኢዮ​ቤ​ልዩ በሆነ ጊዜ ርስ​ታ​ቸው ሴቶቹ ወደ አገ​ቡ​በት ወደ ሌላ ነገድ ርስት ይጨ​መ​ራል፤ እነሆ፥ ርስ​ታ​ቸው ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ነገድ ርስት ይጐ​ድ​ላል።”
5ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “የዮ​ሴፍ ልጆች ነገድ በእ​ው​ነት ተና​ገሩ። 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሰለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው፤ የወ​ደ​ዱ​ትን ያግቡ፤ ነገር ግን ከአ​ባ​ታ​ቸው ነገድ ብቻ ያግቡ። 7እን​ደ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት ከነ​ገድ ወደ ነገድ ምንም አይ​ተ​ላ​ለፍ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ አባ​ቶቹ ነገድ ርስት ይጠጋ። 8ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው የአ​ባ​ቶ​ቹን ርስት ይወ​ርስ ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገድ ሁሉ፥ ርስት ያላት ሴት ልጅ ሁሉ ከአ​ባቷ ነገድ ባል ታግባ። 9እን​ደ​ዚ​ህም ከአ​ንድ ነገድ ወደ ሌላ ነገድ ምንም ርስት አይ​ተ​ላ​ለፍ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ነገድ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ርስቱ ይጠጋ።”
10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች አደ​ረጉ። 11የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች መሐላ፥ ቴርሳ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ኑኃ ከአ​ባ​ታ​ቸው ወን​ድ​ሞች ልጆች ጋር ተጋቡ። 12ከዮ​ሴፍ ልጅ ከም​ናሴ ልጆች ወገ​ኖች ባሎ​ቻ​ቸ​ውን አገቡ፥ ርስ​ታ​ቸ​ውም በአ​ባ​ታ​ቸው ነገድ ጸና።
13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ ያዘ​ዛ​ቸው ትእ​ዛዝ፥ ሥር​ዐ​ትና ፍርድ እነ​ዚህ ናቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ