መጽሐፈ ምሳሌ 3
3
የአባት ምክር ለልጆች
1ልጄ ሆይ! ሕጎቼን አትርሳ፥
ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ።
2ብዙ ዘመናትንና ረጅም ዕድሜን
ሰላምንም ይጨምሩልሃልና።
3ምጽዋትና ሃይማኖት ከአንተ አይራቁ፤
በአንገትህ እሰራቸው፤
በልብህ ጽላትም ጻፋቸው፤#“በልብህ ጽላትም ጻፋቸው” የሚለው በግሪኩ የለም።
4ባላሟልነትን ታገኛለህና፥
በእግዚአብሔርና በሰው ፊት መልካምን ዐስብ።
5በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታምነህ ኑር፥
በራስህም ጥበብ አትደገፍ፤
6በመንገድህ ሁሉ ጥበብን ዕወቃት፥
እርስዋም መንገድህን ታቃናልሃለች።
7በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤
እግዚአብሔርን ፍራው፥ ከክፋትም ሁሉ ራቅ፤
8ይህም ለሥጋህ ፈውስ፥
ለአጥንትህም ጠገን ይሆንልሃል።
9እግዚአብሔርን በእውነት በአገኘኸው ሀብትህ አክብረው።
ከእውነተኛ ፍሬህም ሁሉ ቀዳምያቱን አግባለት።
10ጐተራህም እህልን ይሞላል።
የወይን መጥመቂያህም ወይን ይሞላል።
11ልጄ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ ቸል አትበል፥
በመገሠጹም ከእርሱ የተነሣ አትመረር።
12አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ
እግዚአብሔር የሚወድደውን ይገሥጻል፥
የሚቀበላቸውን ልጆቹን ይገርፋልና።
13ጥበብን የሚያገኝ፥
ማስተዋልንም የሚያውቅ መዋቲ ሰው ብፁዕ ነው።
14በወርቅና በብር፥ በብዙም መዛግብት
ከመነገድ ይልቅ በእርስዋ መነገድ ይሻላልና።
15ዋጋው ብዙ ከሆነ ዕንቍም የከበረች ናት።
ክፉ ነገር አይቃወማትም፥
ለሚቀርቧትም መልካም ናት።
ክብርም ሁሉ አይተካከላትም።
16ረጅም ዕድሜና የሕይወት ዘመን በቀኝዋ ነው።
ባለጠግነትና ክብርም በግራዋ፥
ከአፏ ጽድቅ ይወጣል።
ሕግንና ምጽዋትንም በአንደበትWa ትለብሳለች።
17መንገዶችዋ መልካም መንገዶች ናቸው።
ጎዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው።
18እርስዋ ለሚመረኰዛት ሁሉ የሕይወት ዛፍ ናት፥
የሚታመኑባትም በእግዚአብሔር እንደ ጸና ሰው ናቸው።
19እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፥
በማስተዋልም ሰማያትን አዘጋጀ።
20በዕውቀቱ ቀላያት መነጩ፥
ደመናትም ጠልን ያንጠባጥባሉ።
21ልጄ ሆይ፥ ቸል አትበል
ዐሳቤንና ምክሬን ጠብቅ፤
22ነፍስህ ትድን ዘንድ፥
ለአንገትህም ሞገስ ይሆንህ ዘንድ።
ለሥጋህ ፈውስ፥ ለአጥንትህም ጠገን ይሆንልሃል።
23በመንገድህም ሁሉ በመተማመን ትሄዳለህ፥
እግሮችህም አይሰነካከሉም።
24በተቀመጥህም ጊዜ አትፈራም፤
ብትተኛም መልካም እንቅልፍ ትተኛለህ።
25ከሚመጣብህም አስደንጋጭ ነገር፥
ከሚመጣውም የክፉዎች ሰዎች አደጋ አትፈራም፤
26እግዚአብሔር በመንገድህ ሁሉ ይኖራልና፥
እግሮችህም እንዳይነዋወጡ ያቆማቸዋልና።
27ለተቸገረው ሰው በጎ ነገር ማድረግን ቸል አትበል፥
በእጅህ ያለውን ያህል ርዳው።
28በጎ ነገርን ማድረግ ሲቻልህ፥
ወዳጅህን፦ “ሂድና ተመለስ፤
ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው፥
ነገ የምትወልደውን አታውቅምና።
29እርሱ ተማምኖብህ ከአንተ ጋር ተቀምጦ ሳለ፥
እንደገና በወዳጅህ ላይ ክፉ አታስብ፤
30እርሱ በላይህ የሠራው ክፉ ነገር ከሌለ፥
ከሰው ጋር በከንቱ አትጣላ።
31ከክፉ ሰዎች ዘንድ ሽሙጥን ገንዘብ አታድርግ፥
በመንገዳቸውም አትቅና።
32ኀጢአተኛ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና፤
ከጻድቃንም ጋር አንድ አይሆንም።
33የእግዚአብሔር መርገም በክፉዎች ቤት ነው፥
በጻድቃን ቤት ግን በረከት አለ።
34እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማቸዋል፤
ለትሑታን ግን ክብርን ይሰጣል።
35ጠቢባን ክብርን ይወርሳሉ፤
ሰነፎች ግን ውርደታቸውን ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 3: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ምሳሌ 3
3
የአባት ምክር ለልጆች
1ልጄ ሆይ! ሕጎቼን አትርሳ፥
ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ።
2ብዙ ዘመናትንና ረጅም ዕድሜን
ሰላምንም ይጨምሩልሃልና።
3ምጽዋትና ሃይማኖት ከአንተ አይራቁ፤
በአንገትህ እሰራቸው፤
በልብህ ጽላትም ጻፋቸው፤#“በልብህ ጽላትም ጻፋቸው” የሚለው በግሪኩ የለም።
4ባላሟልነትን ታገኛለህና፥
በእግዚአብሔርና በሰው ፊት መልካምን ዐስብ።
5በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታምነህ ኑር፥
በራስህም ጥበብ አትደገፍ፤
6በመንገድህ ሁሉ ጥበብን ዕወቃት፥
እርስዋም መንገድህን ታቃናልሃለች።
7በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤
እግዚአብሔርን ፍራው፥ ከክፋትም ሁሉ ራቅ፤
8ይህም ለሥጋህ ፈውስ፥
ለአጥንትህም ጠገን ይሆንልሃል።
9እግዚአብሔርን በእውነት በአገኘኸው ሀብትህ አክብረው።
ከእውነተኛ ፍሬህም ሁሉ ቀዳምያቱን አግባለት።
10ጐተራህም እህልን ይሞላል።
የወይን መጥመቂያህም ወይን ይሞላል።
11ልጄ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ ቸል አትበል፥
በመገሠጹም ከእርሱ የተነሣ አትመረር።
12አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ
እግዚአብሔር የሚወድደውን ይገሥጻል፥
የሚቀበላቸውን ልጆቹን ይገርፋልና።
13ጥበብን የሚያገኝ፥
ማስተዋልንም የሚያውቅ መዋቲ ሰው ብፁዕ ነው።
14በወርቅና በብር፥ በብዙም መዛግብት
ከመነገድ ይልቅ በእርስዋ መነገድ ይሻላልና።
15ዋጋው ብዙ ከሆነ ዕንቍም የከበረች ናት።
ክፉ ነገር አይቃወማትም፥
ለሚቀርቧትም መልካም ናት።
ክብርም ሁሉ አይተካከላትም።
16ረጅም ዕድሜና የሕይወት ዘመን በቀኝዋ ነው።
ባለጠግነትና ክብርም በግራዋ፥
ከአፏ ጽድቅ ይወጣል።
ሕግንና ምጽዋትንም በአንደበትWa ትለብሳለች።
17መንገዶችዋ መልካም መንገዶች ናቸው።
ጎዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው።
18እርስዋ ለሚመረኰዛት ሁሉ የሕይወት ዛፍ ናት፥
የሚታመኑባትም በእግዚአብሔር እንደ ጸና ሰው ናቸው።
19እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፥
በማስተዋልም ሰማያትን አዘጋጀ።
20በዕውቀቱ ቀላያት መነጩ፥
ደመናትም ጠልን ያንጠባጥባሉ።
21ልጄ ሆይ፥ ቸል አትበል
ዐሳቤንና ምክሬን ጠብቅ፤
22ነፍስህ ትድን ዘንድ፥
ለአንገትህም ሞገስ ይሆንህ ዘንድ።
ለሥጋህ ፈውስ፥ ለአጥንትህም ጠገን ይሆንልሃል።
23በመንገድህም ሁሉ በመተማመን ትሄዳለህ፥
እግሮችህም አይሰነካከሉም።
24በተቀመጥህም ጊዜ አትፈራም፤
ብትተኛም መልካም እንቅልፍ ትተኛለህ።
25ከሚመጣብህም አስደንጋጭ ነገር፥
ከሚመጣውም የክፉዎች ሰዎች አደጋ አትፈራም፤
26እግዚአብሔር በመንገድህ ሁሉ ይኖራልና፥
እግሮችህም እንዳይነዋወጡ ያቆማቸዋልና።
27ለተቸገረው ሰው በጎ ነገር ማድረግን ቸል አትበል፥
በእጅህ ያለውን ያህል ርዳው።
28በጎ ነገርን ማድረግ ሲቻልህ፥
ወዳጅህን፦ “ሂድና ተመለስ፤
ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው፥
ነገ የምትወልደውን አታውቅምና።
29እርሱ ተማምኖብህ ከአንተ ጋር ተቀምጦ ሳለ፥
እንደገና በወዳጅህ ላይ ክፉ አታስብ፤
30እርሱ በላይህ የሠራው ክፉ ነገር ከሌለ፥
ከሰው ጋር በከንቱ አትጣላ።
31ከክፉ ሰዎች ዘንድ ሽሙጥን ገንዘብ አታድርግ፥
በመንገዳቸውም አትቅና።
32ኀጢአተኛ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና፤
ከጻድቃንም ጋር አንድ አይሆንም።
33የእግዚአብሔር መርገም በክፉዎች ቤት ነው፥
በጻድቃን ቤት ግን በረከት አለ።
34እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማቸዋል፤
ለትሑታን ግን ክብርን ይሰጣል።
35ጠቢባን ክብርን ይወርሳሉ፤
ሰነፎች ግን ውርደታቸውን ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።