መጽሐፈ ምሳሌ 4
4
ከጥበብ የሚገኝ ጥቅም
1ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥
ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤
2መልካም ስጦታን እሰጣችኋለሁና፥
ሕጌን አትተዉ።
3እኔም አባቴን የምሰማ ልጅ ነበርሁና፥
በእናቴም ፊት እወደድ ነበር።
4ያስተምሩኝም ነበር፥ እንዲህም ይሉኝ ነበር፦
ቃላችን በልብህ ይኑር፤
ትእዛዞቻችንንም ጠብቅ፥ አትርሳቸውም።
5የአፌንም ቃል ቸል አትበል።
6አትተዋት፥ ትደግፍህማለች፤
ውደዳት፥ ትጠብቅህማለች።
7ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤
ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ።#ምዕ. 4 ቍ. 7 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
8ጠብቃት፥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤
አክብራት፥ እርስዋም ታቅፍሃለች።
9ለራስህ የሞገስ አክሊልን ትሰጥሃለች፥
በደስታ አክሊልም ትጠብቅሃለች።
10ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ንግግሬንም ተቀበል፤
የሕይወትህም ዓመታት ይበዙልሃል፥
የሕይወትህ መንገድ ይበዛ ዘንድ።
11የጥበብን መንገዶች አስተምርሃለሁና፤
በቀናች ጎዳና መራሁህ።
12ብትሄድ ፍለጋህ አይጠፋም፤
በሮጥህም ጊዜ አትሰናከልም።
13ምክሬን ያዝ፥ አትተውም፤
ለራስህ ጠብቃት፥ እርሷ ሕይወትህ ናትና።
14በክፉዎች መንገድ አትሂድ፥
በክፉ ሰዎችም ጎዳና አትቅና።
15በተጓዙበትም ቦታ አትሂድ፤
ከእነርሱ ፈቀቅ በል ተመለስም።
16ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥
ከዐይናቸው እንቅልፋቸው ይወገዳል አይተኙምም።
17የኀጢአት መብልን ይበላሉ፥
በግፍ የወይን ጠጅም ይሰክራሉ።
18የጻድቃን መንገዶች ግን እንደ ብርሃን ይበራሉ።
ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየጨመሩ ይበራሉ።
19የኃጥኣን መንገዶች ግን ጨለማ ናቸው።
እንዴት እንደሚሰናከሉም አያውቁም።
20ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ፤
ጆሮህንም ወደ ቃሌ አዘንብል።
21ምንጮችህ እንዳይደርቁ፥
በልብህ ጠብቃቸው።
22ለሚያገኙአቸው ሕይወት፥
ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ናቸውና።
23ልብህን አጥብቀህ ጠብቅ፥
የሕይወት መገኛ ከእርሱ ነውና።
24ክፉ አፍን ከአንተ አርቅ፥
ሐሰተኞች ከንፈሮችንም ከአንተ አስወግድ።
25ዐይኖችህም አቅንተው ይዩ፥
ሽፋሽፍቶችህም ወደ እውነት ያመልክቱ።
26ለእግርህ ቀና መሄጃ ሥራ፥
መንገዶችህንም አቅና።
27ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፤
እግርህንም ከመጥፎ መንገድ መልስ።
እግዚአብሔር የቀኝ መንገዶችን ያውቃልና፥
የግራ መንገዶች ግን ጠማሞች ናቸው።
እርሱም መሄጃህን የቀና ያደርጋል፥
አካሄድህንም በሰላም ያሳምራል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 4: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ምሳሌ 4
4
ከጥበብ የሚገኝ ጥቅም
1ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥
ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤
2መልካም ስጦታን እሰጣችኋለሁና፥
ሕጌን አትተዉ።
3እኔም አባቴን የምሰማ ልጅ ነበርሁና፥
በእናቴም ፊት እወደድ ነበር።
4ያስተምሩኝም ነበር፥ እንዲህም ይሉኝ ነበር፦
ቃላችን በልብህ ይኑር፤
ትእዛዞቻችንንም ጠብቅ፥ አትርሳቸውም።
5የአፌንም ቃል ቸል አትበል።
6አትተዋት፥ ትደግፍህማለች፤
ውደዳት፥ ትጠብቅህማለች።
7ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤
ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ።#ምዕ. 4 ቍ. 7 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
8ጠብቃት፥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤
አክብራት፥ እርስዋም ታቅፍሃለች።
9ለራስህ የሞገስ አክሊልን ትሰጥሃለች፥
በደስታ አክሊልም ትጠብቅሃለች።
10ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ንግግሬንም ተቀበል፤
የሕይወትህም ዓመታት ይበዙልሃል፥
የሕይወትህ መንገድ ይበዛ ዘንድ።
11የጥበብን መንገዶች አስተምርሃለሁና፤
በቀናች ጎዳና መራሁህ።
12ብትሄድ ፍለጋህ አይጠፋም፤
በሮጥህም ጊዜ አትሰናከልም።
13ምክሬን ያዝ፥ አትተውም፤
ለራስህ ጠብቃት፥ እርሷ ሕይወትህ ናትና።
14በክፉዎች መንገድ አትሂድ፥
በክፉ ሰዎችም ጎዳና አትቅና።
15በተጓዙበትም ቦታ አትሂድ፤
ከእነርሱ ፈቀቅ በል ተመለስም።
16ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥
ከዐይናቸው እንቅልፋቸው ይወገዳል አይተኙምም።
17የኀጢአት መብልን ይበላሉ፥
በግፍ የወይን ጠጅም ይሰክራሉ።
18የጻድቃን መንገዶች ግን እንደ ብርሃን ይበራሉ።
ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየጨመሩ ይበራሉ።
19የኃጥኣን መንገዶች ግን ጨለማ ናቸው።
እንዴት እንደሚሰናከሉም አያውቁም።
20ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ፤
ጆሮህንም ወደ ቃሌ አዘንብል።
21ምንጮችህ እንዳይደርቁ፥
በልብህ ጠብቃቸው።
22ለሚያገኙአቸው ሕይወት፥
ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ናቸውና።
23ልብህን አጥብቀህ ጠብቅ፥
የሕይወት መገኛ ከእርሱ ነውና።
24ክፉ አፍን ከአንተ አርቅ፥
ሐሰተኞች ከንፈሮችንም ከአንተ አስወግድ።
25ዐይኖችህም አቅንተው ይዩ፥
ሽፋሽፍቶችህም ወደ እውነት ያመልክቱ።
26ለእግርህ ቀና መሄጃ ሥራ፥
መንገዶችህንም አቅና።
27ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፤
እግርህንም ከመጥፎ መንገድ መልስ።
እግዚአብሔር የቀኝ መንገዶችን ያውቃልና፥
የግራ መንገዶች ግን ጠማሞች ናቸው።
እርሱም መሄጃህን የቀና ያደርጋል፥
አካሄድህንም በሰላም ያሳምራል።