መዝሙረ ዳዊት 107
107
የዳዊት የምስጋና መዝሙር።
1ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑዕ ነው፤
አመሰግናለሁ እዘምራለሁም።
2ክብሬም ይመለስልኛል፥ በበገናና በመሰንቆ እነሣለሁ፤
ማልጄም እነሣለሁ፤
3አቤቱ፥ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤
በወገኖችም መካከል እዘምርልሃለሁ፤
4ምሕረትህ በሰማይ ላይ ታላቅ ናትና፥
እውነትህም እስከ ደመናት ድረስ ነውና።
5እግዚአብሔርም በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ አለ፥
ክብሩም በምድር ሁሉ ላይ ነው።
6ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ
በቀኝህ አድን፥ አድምጠኝም።
7እግዚአብሔር በመቅደሱ ተናገረ፥
ደስ ይለኛል፥ ሰቂማንም እካፈላለሁ፥
የሸለቆ ቦታዎችን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ድንኳኖች” ይላል። እሰፍራለሁ።
8ገለዓድ የእኔ ነው፥ ምናሴም የእኔ ነው፤
ኤፍሬም የራሴ መጠጊያ ነው።
ይሁዳ ንጉሤ ነው፤
9ካህን ሞዓብም ተስፋዬ ነው፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሞአብ የተስፋዬ አፍላል ነው” ሲል ዕብ. “ሞአብ መታጠቢያዬ ነው” ይላል።
በኤዶምያስ ላይም ጫማዬን እዘረጋለሁ፤
ፍልስጥኤምም ይገዙልኛል።
10ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወስደኛል?
ማንስ እስከ ኤዶምያስ ይመራኛል?
11አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን?
አምላካችን ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።
12በመከራችን ረድኤትን ስጠን፤
በሰውም መታመን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሰው ማዳን” ይላል። ከንቱ ነው።
13በእግዚአብሔር ኀይልን እናደርጋለን፤
እርሱም የሚያስጨንቁንን ያዋርዳቸዋል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 107: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ