የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 107

107
የዳ​ዊት የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር።
1ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑዕ ነው፤
አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ እዘ​ም​ራ​ለ​ሁም።
2ክብ​ሬም ይመ​ለ​ስ​ል​ኛል፥ በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ እነ​ሣ​ለሁ፤
ማል​ጄም እነ​ሣ​ለሁ፤
3አቤቱ፥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤
በወ​ገ​ኖ​ችም መካ​ከል እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ፤
4ምሕ​ረ​ትህ በሰ​ማይ ላይ ታላቅ ናትና፥
እው​ነ​ት​ህም እስከ ደመ​ናት ድረስ ነውና።
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ማ​ያት ላይ ከፍ ከፍ አለ፥
ክብ​ሩም በም​ድር ሁሉ ላይ ነው።
6ወዳ​ጆ​ችህ ይድኑ ዘንድ
በቀ​ኝህ አድን፥ አድ​ም​ጠ​ኝም።
7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ቅ​ደሱ ተና​ገረ፥
ደስ ይለ​ኛል፥ ሰቂ​ማ​ንም እካ​ፈ​ላ​ለሁ፥
የሸ​ለቆ ቦታ​ዎ​ችን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ድን​ኳ​ኖች” ይላል። እሰ​ፍ​ራ​ለሁ።
8ገለ​ዓድ የእኔ ነው፥ ምና​ሴም የእኔ ነው፤
ኤፍ​ሬም የራሴ መጠ​ጊያ ነው።
ይሁዳ ንጉሤ ነው፤
9ካህን ሞዓ​ብም ተስ​ፋዬ ነው፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሞአብ የተ​ስ​ፋዬ አፍ​ላል ነው” ሲል ዕብ. “ሞአብ መታ​ጠ​ቢ​ያዬ ነው” ይላል።
በኤ​ዶ​ም​ያስ ላይም ጫማ​ዬን እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤
ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ምም ይገ​ዙ​ል​ኛል።
10ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወ​ስ​ደ​ኛል?
ማንስ እስከ ኤዶ​ም​ያስ ይመ​ራ​ኛል?
11አቤቱ፥ የጣ​ል​ኸን አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?
አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ችን ጋር አት​ወ​ጣም።
12በመ​ከ​ራ​ችን ረድ​ኤ​ትን ስጠን፤
በሰ​ውም መታ​መን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሰው ማዳን” ይላል። ከንቱ ነው።
13በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤
እር​ሱም የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ንን ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ