የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 12

12
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ እስከ መቼ ፈጽ​መህ ትረ​ሳ​ኛ​ለህ?
እስከ መቼስ ፊት​ህን ከእኔ ትመ​ል​ሳ​ለህ?
2እስከ መቼ በነ​ፍሴ ኀዘ​ንን አኖ​ራ​ለሁ?#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እመ​ካ​ከ​ራ​ለሁ” ይላል።
እስከ መቼ ልቤ ሁል​ጊዜ ትጨ​ነ​ቅ​ብ​ኛ​ለች?
እስከ መቼ ጠላ​ቶች በላዬ ይታ​በ​ያሉ?#ግሪክ ሰባ. ሊ. በነ​ጠላ።
3አቤቱ አም​ላኬ፥ ተመ​ል​ከ​ተኝ ስማ​ኝም፤
ለሞ​ትም እን​ዳ​ያ​ን​ቀ​ላፉ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እን​ዳ​ላ​ን​ቀ​ላፋ” ይላል። ዐይ​ኖቼን አብ​ራ​ቸው።
ጠላ​ቶ​ቼም አሸ​ነ​ፍ​ነው እን​ዳ​ይሉ፥
4የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ኝም እኔ ብና​ወጥ ደስ እን​ዳ​ይ​ላ​ቸው፥
5እኔ ግን በቸ​ር​ነ​ትህ ታመ​ንሁ፥
ልቤም በማ​ዳ​ንህ ደስ ይለ​ዋል።
6የረ​ዳ​ኝን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ፤
ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስምም እዘ​ም​ራ​ለሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ