መዝሙረ ዳዊት 144
144
የዳዊት የምስጋና መዝሙር።
1አምላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥
ስምህንም ለዘለዓለም ዓለም አመሰግናለሁ።
2በየቀኑ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥
ለስምህም ለዘለዓለም ዓለም ምስጋና አቀርባለሁ።
3እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ ምስጋናውም እጅግ ብዙ ነው፤
ለታላቅነቱም ዳርቻ የለውም።
4የልጅ ልጆች ሥራህን ያደንቃሉ፥
ኀይልህንም ይናገራሉ፥
5የቅድስናህንም ክብር ታላቅነት ይናገራሉ፥
ተአምራትህንም ያስረዳሉ።
6“ኀይልህ ግሩም ነው” ይላሉ፥
ግርማህንም#ግእዝ “ኀይለ ግርማከ” ይላል። ይነጋገራሉ፥
ብርታትህንም ያስረዳሉ።
7የቸርነትህን ብዛት መታሰቢያ ይናገራሉ፥
በጽድቅህም ሐሤትን ያደርጋሉ።
8እግዚአብሔር ይቅር ባይና መሓሪ ነው፥
መዐቱ የራቀ፥ ምሕረቱ የበዛ እውነተኛ #በግእዝ ብቻ። ነው፤
9እግዚአብሔር ለሚታገሡት ቸር ነው።
ይቅርታውም በሥራው ሁሉ ላይ ነው።
10አቤቱ፥ ፍጥረትህ ሁሉ ያመሰግኑሃል፥
ጻድቃንህም ያመሰግኑሃል።
11“ለመንግሥትህ ክብር ይገባል” ይላሉ፥
ኀይልህንም ይነጋገራሉ፥
12ለሰው ልጆች ኀይልህን
የመንግሥትህንም ክብር ታላቅነት ያስታውቁ ዘንድ።
13መንግሥትህ የዘለዓለም ሁሉ መንግሥት ናት፥
ግዛትህም ለልጅ ልጅ ነው።
14እግዚአብሔር በቃሉ ሁሉ የታመነ ነው፥
በሥራውም ሁሉ ጻድቅ ነው፤
እግዚአብሔር የተፍገመገሙትን ሁሉ ይደግፋቸዋል፥
እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሣቸዋል።
15የሰው ሁሉ ዐይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፤
አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ።
16ቀኝ እጅህን ትዘረጋለህ፤
በሥርዐትህ ለሚኖሩ እንስሳ ሁሉ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን” ይላል። ታጠግባለህ።
17እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው
በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።
18እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፥
በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።
19ለሚፈሩት ፈቃዳቸውን ያደርጋል፥
ልመናቸውንም ይሰማል፥ ያድናቸዋልም።
20እግዚአብሔር የሚወድዱትን#ግእዝ “የሚፈሩትን” ይላል። ሁሉ ይጠብቃል፤
ኀጢአተኞችንም ሁሉ ያጠፋል።
21አፌ የእግዚአብሔርን ምስጋና ይናገራል፤
ሥጋም ሁሉ ለዘለዓለም ዓለም የተቀደሰውን ስሙን ያመሰግናል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 144: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ