የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 148

148
የሐ​ጌና የዘ​ካ​ር​ያስ መዝ​ሙር።
ሃሌ ሉያ።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከሰ​ማ​ያት አመ​ስ​ግ​ኑት፤
በአ​ር​ያም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. መዝ. 148 ከቍ. 2 እስከ 5 “አመ​ስ​ግ​ኑት” ይላል።
2መላ​እ​ክቱ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
ሠራ​ዊቱ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።
3ፀሐ​ይና ጨረቃ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
ከዋ​ክ​ብ​ትና ብር​ሃን ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።
4ሰማየ ሰማ​ያት፥
ከሰ​ማ​ያት በላይ ያለ ውኃም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።
5የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።
እርሱ ብሎ​አ​ልና፥ ሆኑ፤
እርሱ አዝ​ዞ​አ​ልና፥ ተፈ​ጠሩ፤
6ለዘ​ለ​ዓ​ለም አቆ​ማ​ቸው፤
ትእ​ዛ​ዝን ሰጣ​ቸው፥ አላ​ለ​ፉ​ምም።
7እባ​ቦ​ችና ጥል​ቆች ሁሉ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከም​ድር አመ​ስ​ግ​ኑት፤
8እሳ​ትና በረዶ፥ አመ​ዳ​ይና ውርጭ፥
ቃሉን የሚ​ያ​ደ​ርግ ዐውሎ ነፋ​ስም፤
9ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶ​ችም ሁሉ፥
የሚ​ያ​ፈ​ራም ዛፍ ዝግ​ባም ሁሉ፤
10አራ​ዊ​ትም፥ እን​ስ​ሳ​ትም ሁሉ፥
ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም፥ የሚ​በ​ርሩ ወፎ​ችም፤
11የም​ድር ነገ​ሥ​ታት፥ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ፥
አለ​ቆች፥ የም​ድ​ርም ፈራ​ጆች ሁሉ፤
12ጐል​ማ​ሶ​ችና ደና​ግል፥
ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ልጆች፤
13የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።
ስሙ ብቻ​ውን ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፥
በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።
14የሕ​ዝ​ቡ​ንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል፤
የጻ​ድ​ቃ​ኑ​ንም ሁሉ ምስ​ጋና
ወደ እርሱ ለቀ​ረበ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ