መዝሙረ ዳዊት 149
149
ሃሌ ሉያ።
1እግዚአብሔርን አዲስ ምስጋናን አመስግኑት፤
ምስጋናውም በጻድቃኑ ጉባኤ ነው።
2እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይለዋል፥#መዝ. 149 ከቍ. 2 እስከ 6 በዕብ. እና በግሪክ ሰባ. ሊ. አንቀጹ በትእዛዝ ነው።
የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤትን ያደርጋሉ።
3ስሙን በደስታ ያመሰግናሉ፥
በከበሮና በበገና ይዘምሩለታል።
4እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ብሎታልና፥
የዋሃንንም በማዳኑ ከፍ ከፍ ያደርጋልና።
5ጻድቃን በክብሩ ይመካሉ፤
በመኝታቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ።
6እግዚአብሔርን በጕሮሮአቸው ያመሰግኑታል፤
ሁለት አፍ ያለውም ሰይፍ በእጁ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በእጃቸው” ይላል። ነው፥
7በአሕዛብ ላይ በቀልን ያደርግ ዘንድ፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ያደርጉ ዘንድ” ይላል።
ሕዝቡንም ይዘልፋቸው ዘንድ፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ይዘልፉ ዘንድ” ይላል።
8ንጉሦቻቸውንም በእግር ብረት፥
አለቆቻቸውንም በሰንሰለት ያስራቸው ዘንድ፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ያስሩ ዘንድ” ይላል።
9የተጻፈውን ፍርድ በእነርሱ ላይ ያደርግ ዘንድ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ያደርጉ ዘንድ” ይላል።
ይህች ክብር ለጻድቃኑ ሁሉ ናት።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 149: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ