የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 15

15
የዳ​ዊት ቅኔ።
1አቤቱ፥ በአ​ንተ ታም​ኛ​ለ​ሁና ጠብ​ቀኝ።
2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ሁት፥ “አንተ ጌታዬ ነህ፤
በጎ​ነ​ቴን አት​ሻ​ት​ምና።#ዕብ. “ያለ አንተ በጎ ነገር የለ​ኝም” ይላል።
3ፈቃ​ድህ ሁሉ በም​ድር ባሉት ቅዱ​ሳን#ዕብ. “ክቡ​ራን” የሚል ይጨ​ም​ራል። ላይ ተገ​ለጠ።
4ደዌ​ያ​ቸው በዛ፤ ከዚ​ያም በኋላ ተፋ​ጠኑ፤#ዕብ. “ወደ ሌላ ለሚ​ፋ​ጠኑ መከ​ራ​ቸው ይበ​ዛል” ይላል።
በደም ማኅ​በ​ራ​ቸው አል​ተ​ባ​በ​ርም።
ስማ​ቸ​ው​ንም በአፌ አል​ጠ​ራም።
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የር​ስቴ ዕድል ፋን​ታና ጽዋዬ ነው፥
ርስ​ቴን የም​ት​መ​ልስ አንተ ነህ።
6ይይ​ዙኝ ዘንድ ገመድ ጣሉ​ብኝ፥
ርስቴ ግን ተያ​ዘ​ልኝ።”#መዝ. 15 ቍ. 6 ዕብ. “ገመድ ባማረ ስፍራ ወደ​ቀ​ች​ልኝ ርስ​ቴም ተዋ​በ​ች​ልኝ” ይላል።
7እን​ዳ​ስ​ተ​ውል ያደ​ረ​ገ​ኝን#ዕብ. “የመ​ከ​ረ​ኝን” ይላል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ፤
ደግ​ሞም በሌ​ሊት ኵላ​ሊ​ቶች ይገ​ሥ​ጹ​ኛል።
8ሁል​ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፊቴ አየ​ዋ​ለሁ፤
እን​ዳ​ል​ታ​ወክ በቀኜ ነውና።
9ስለ​ዚህ ልቤን ደስ አለው፥ ምላ​ሴም ሐሤት አደ​ረገ፤
ሥጋዬ ደግሞ በተ​ስ​ፋው ያድ​ራል፤
10ነፍ​ሴን በሲ​ኦል አት​ተ​ዋ​ት​ምና፥
ጻድ​ቅ​ህ​ንም#ዕብ. “ቅዱ​ስ​ህን” ይላል። መበ​ስ​በ​ስን ያይ ዘንድ አት​ተ​ወ​ውም።
11የሕ​ይ​ወ​ትን መን​ገድ አሳ​የ​ኸኝ፤
ከፊ​ትህ ጋር ደስ​ታን አጠ​ገ​ብ​ኸኝ፥
በቀ​ኝ​ህም የዘ​ለ​ዓ​ለም ፍስሓ አለ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ