መዝሙረ ዳዊት 16
16
የዳዊት ጸሎት።
1አቤቱ፥ ጽድቄን ስማኝ፥ ልመናዬንም አድምጠኝ፤
በተንኰለኛም ከንፈር ያልሆነውን ጸሎቴን አድምጠኝ፤
2ፍርዴ ከፊትህ ይወጣል፥
ዐይኖቼም ጽድቅህን አዩ።
3በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው፥
ፈተንኸኝ፥ ዐመፅም አልተገኘብኝም።
4የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር፥#ዕብ. “ፈቃዴ ነው” የሚል ይጨምራል።
ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ።
5ሰኰናዬ እንዳይናወጥ አረማመዴን በመንገድህ አጽና።
6እግዚአብሔር ሰምቶኛልና እኔ ጮኽሁ፤
ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ ቃሌንም ስማ።
7ቀኝህን ከሚቃወሟት፥
የሚያምኑብህን የሚያድናቸውን
ቸርነትህን#ዕብ. “ድንቅ አድርገህ ግለጠው” ይላል። ግለጠው።
8እንደ ዐይን ብሌን ጠብቀኝ፤
በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ፤
9ከሚያጐሳቍሉኝ ኃጥኣን#ዕብ. “ከሚያስጨንቁኝ” ይላል። ፊት፥
ጠላቶቼ ግን ነፍሴን ተመለከትዋት፤#ዕብ. “ነፍሴን ከሚመለከትዋት ጠላቶች” ይላል።
10አንጀታቸውን#ዕብ. “በስብ ሸፈኑ” ይላል። ቋጠሩ፥
አፋቸውም ትዕቢትን ተናገረ።
11አሁንም አባረሩኝ፤ ከበቡኝም፤
ዐይናቸውንም ወደ ምድር ዝቅ ዝቅ አደረጉ።
12እነርሱ ለንጥቂያ እንደሚሸምቅ አንበሳ፥
ተሰውሮም እንደሚኖር እንደ አንበሳ ግልገል ተቀበሉኝ።
13አቤቱ፥ ተነሥ፥ ደርሰህ አሰናክላቸው፤#ዕብ. “ወደ ታች ጣለው” ይላል።
ነፍሴንም ከጦር አድናት።
14ሰይፍህ በእጅህ ጠላቶች ላይ ናት።
አቤቱ፥ በምድር ካነሱ ሰዎች፥
በሕይወታቸው ከፋፍላቸው፥
ከሰወርኸው#ዕብ. “ከሰወርኸው መዝገብህ” ይላል። ሆዳቸው ጠገበች፤
ልጆቻቸው ጠገቡ።
የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ተዉ።
15እኔ ግን በጽድቅህ ፊትህን አያለሁ፤
ክብርህን በማየትም እጠግባለሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 16: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 16
16
የዳዊት ጸሎት።
1አቤቱ፥ ጽድቄን ስማኝ፥ ልመናዬንም አድምጠኝ፤
በተንኰለኛም ከንፈር ያልሆነውን ጸሎቴን አድምጠኝ፤
2ፍርዴ ከፊትህ ይወጣል፥
ዐይኖቼም ጽድቅህን አዩ።
3በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው፥
ፈተንኸኝ፥ ዐመፅም አልተገኘብኝም።
4የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር፥#ዕብ. “ፈቃዴ ነው” የሚል ይጨምራል።
ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ።
5ሰኰናዬ እንዳይናወጥ አረማመዴን በመንገድህ አጽና።
6እግዚአብሔር ሰምቶኛልና እኔ ጮኽሁ፤
ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ ቃሌንም ስማ።
7ቀኝህን ከሚቃወሟት፥
የሚያምኑብህን የሚያድናቸውን
ቸርነትህን#ዕብ. “ድንቅ አድርገህ ግለጠው” ይላል። ግለጠው።
8እንደ ዐይን ብሌን ጠብቀኝ፤
በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ፤
9ከሚያጐሳቍሉኝ ኃጥኣን#ዕብ. “ከሚያስጨንቁኝ” ይላል። ፊት፥
ጠላቶቼ ግን ነፍሴን ተመለከትዋት፤#ዕብ. “ነፍሴን ከሚመለከትዋት ጠላቶች” ይላል።
10አንጀታቸውን#ዕብ. “በስብ ሸፈኑ” ይላል። ቋጠሩ፥
አፋቸውም ትዕቢትን ተናገረ።
11አሁንም አባረሩኝ፤ ከበቡኝም፤
ዐይናቸውንም ወደ ምድር ዝቅ ዝቅ አደረጉ።
12እነርሱ ለንጥቂያ እንደሚሸምቅ አንበሳ፥
ተሰውሮም እንደሚኖር እንደ አንበሳ ግልገል ተቀበሉኝ።
13አቤቱ፥ ተነሥ፥ ደርሰህ አሰናክላቸው፤#ዕብ. “ወደ ታች ጣለው” ይላል።
ነፍሴንም ከጦር አድናት።
14ሰይፍህ በእጅህ ጠላቶች ላይ ናት።
አቤቱ፥ በምድር ካነሱ ሰዎች፥
በሕይወታቸው ከፋፍላቸው፥
ከሰወርኸው#ዕብ. “ከሰወርኸው መዝገብህ” ይላል። ሆዳቸው ጠገበች፤
ልጆቻቸው ጠገቡ።
የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ተዉ።
15እኔ ግን በጽድቅህ ፊትህን አያለሁ፤
ክብርህን በማየትም እጠግባለሁ።