መዝሙረ ዳዊት 151
151
ከቍጥር የወጣ መዝሙር ስለ ራሱ።
1ከወንድሞቼ ይልቅ እኔ ትንሽ ነበርሁ፥
በአባቴም ቤት ወጣት ነበርሁ፥
ያባቴንም በጎች እጠብቅ ነበር።
2እጆቼ መሰንቆ ይመቱ ነበር።
ጣቶቼም በገና ይደረድሩ ነበር።
3ለጌታዬ ማን ነገረው?
እርሱ እግዚአብሔር እርሱ ሰማኝ።
4እርሱ መልአኩን ልኮ አዳነኝ፥
የአባቴን በጎች ከምጠብቅበት ወሰደኝ፤
የተቀደሰ ቅባትን ቀባኝ፤
5ወንድሞቼ ግን፥ ያማሩና ያደጉ ነበሩ።
እግዚአብሔር ግን በእነርሱ ደስ አላለውም።
6ልዩ ወገንን#ኢሎፍላዊውን። ልገጥመው ወጣሁ።
በረከሱ ጣዖቶቹም ረገመኝ።
7እኔም ከወንዝ ሦስት#በ 1ኛ ሳሙ. ምዕ. 17 ቍ. 40 “አምስት” ይላል። ድንጋዮችን አነሣሁ፥
ግንባሩንም በወንጭፍ መታሁት።
ያንጊዜም በእግዚአብሔር ኀይል ወደቀ።#ቍ. 7 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
8በላዩ የነበረውንም ሰይፍ ወሰድሁ፥
የጎልያድንም ቸብቸቦ ቈረጥሁ።
ከእስራኤል ልጆችም ስድብን አራቅሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 151: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 151
151
ከቍጥር የወጣ መዝሙር ስለ ራሱ።
1ከወንድሞቼ ይልቅ እኔ ትንሽ ነበርሁ፥
በአባቴም ቤት ወጣት ነበርሁ፥
ያባቴንም በጎች እጠብቅ ነበር።
2እጆቼ መሰንቆ ይመቱ ነበር።
ጣቶቼም በገና ይደረድሩ ነበር።
3ለጌታዬ ማን ነገረው?
እርሱ እግዚአብሔር እርሱ ሰማኝ።
4እርሱ መልአኩን ልኮ አዳነኝ፥
የአባቴን በጎች ከምጠብቅበት ወሰደኝ፤
የተቀደሰ ቅባትን ቀባኝ፤
5ወንድሞቼ ግን፥ ያማሩና ያደጉ ነበሩ።
እግዚአብሔር ግን በእነርሱ ደስ አላለውም።
6ልዩ ወገንን#ኢሎፍላዊውን። ልገጥመው ወጣሁ።
በረከሱ ጣዖቶቹም ረገመኝ።
7እኔም ከወንዝ ሦስት#በ 1ኛ ሳሙ. ምዕ. 17 ቍ. 40 “አምስት” ይላል። ድንጋዮችን አነሣሁ፥
ግንባሩንም በወንጭፍ መታሁት።
ያንጊዜም በእግዚአብሔር ኀይል ወደቀ።#ቍ. 7 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
8በላዩ የነበረውንም ሰይፍ ወሰድሁ፥
የጎልያድንም ቸብቸቦ ቈረጥሁ።
ከእስራኤል ልጆችም ስድብን አራቅሁ።