መዝሙረ ዳዊት 2
2
ትንቢት ስለ ክርስቶስ
1አሕዛብ ለምን ዶለቱ?#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አጕረመረሙ” ይላል።
ወገኖችስ ለምን ከንቱ ይናገራሉ?
2የምድር ነገሥታት ተነሡ፥
አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሲሑ ላይ
እንዲህ ሲሉ በአንድነት ተሰበሰቡ።
3“ማሰሪያቸውን ከእኛ እንበጥስ፥
ቀንበራቸውንም ከእኛ ላይ እንጣል።”
4በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቅባቸዋል።
እግዚአብሔርም ይሣለቅባቸዋል።
5በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥
በመዓቱም ያውካቸዋል።
6እኔ ግን በእነርሱ ላይ#ዕብ. “እኔ ንጉሤን ሾምሁ” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “በእርሱ ንጉሥ ሆኜ ተሾምሁ” ይላል። ንጉሥ ሆኜ ተሾምሁ
በተቀደሰ ተራራው በጽዮን ላይ።
7የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እናገር ዘንድ፥
እግዚአብሔር አለኝ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥
እኔም ዛሬ ወለድሁህ።
8ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ
የምድርንም ዳርቻ፥ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ።
9በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥
እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀጠቅጣቸዋለህ።”
10አሁንም እናንት ነገሥታት፥ ልብ አድርጉ፤
እናንት የምድር ፈራጆችም፥ ተገሠጹ።
11ለእግዚአብሔር በፍርሀት ተገዙ፥
በረዓድም ደስ ይበላችሁ።
12ጥበብን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ተግሣጽን” ሲል ዕብ. “ወልድን ሳሙት” ይላል። አጽኑአት፤ እግዚአብሔር እንዳይቈጣ፥
እናንተም ከጽድቅ መንገድ እንዳትጠፉ፥
ቍጣው ፈጥና በነደደች ጊዜ፥
በእርሱ የታመኑ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 2: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 2
2
ትንቢት ስለ ክርስቶስ
1አሕዛብ ለምን ዶለቱ?#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አጕረመረሙ” ይላል።
ወገኖችስ ለምን ከንቱ ይናገራሉ?
2የምድር ነገሥታት ተነሡ፥
አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሲሑ ላይ
እንዲህ ሲሉ በአንድነት ተሰበሰቡ።
3“ማሰሪያቸውን ከእኛ እንበጥስ፥
ቀንበራቸውንም ከእኛ ላይ እንጣል።”
4በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቅባቸዋል።
እግዚአብሔርም ይሣለቅባቸዋል።
5በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥
በመዓቱም ያውካቸዋል።
6እኔ ግን በእነርሱ ላይ#ዕብ. “እኔ ንጉሤን ሾምሁ” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “በእርሱ ንጉሥ ሆኜ ተሾምሁ” ይላል። ንጉሥ ሆኜ ተሾምሁ
በተቀደሰ ተራራው በጽዮን ላይ።
7የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እናገር ዘንድ፥
እግዚአብሔር አለኝ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥
እኔም ዛሬ ወለድሁህ።
8ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ
የምድርንም ዳርቻ፥ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ።
9በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥
እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀጠቅጣቸዋለህ።”
10አሁንም እናንት ነገሥታት፥ ልብ አድርጉ፤
እናንት የምድር ፈራጆችም፥ ተገሠጹ።
11ለእግዚአብሔር በፍርሀት ተገዙ፥
በረዓድም ደስ ይበላችሁ።
12ጥበብን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ተግሣጽን” ሲል ዕብ. “ወልድን ሳሙት” ይላል። አጽኑአት፤ እግዚአብሔር እንዳይቈጣ፥
እናንተም ከጽድቅ መንገድ እንዳትጠፉ፥
ቍጣው ፈጥና በነደደች ጊዜ፥
በእርሱ የታመኑ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።