የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 3

3
የዳ​ዊት መዝ​ሙር፥ ከልጁ ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ፊት በሸሸ ጊዜ።
1አቤቱ፥ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ምንኛ በዙ!
በእኔ ላይ የሚ​ቆ​ሙት ብዙ ናቸው።
2ብዙ ሰዎች ነፍ​ሴን አል​ዋት፦
“አም​ላ​ክሽ አያ​ድ​ን​ሽም።”
3አንተ ግን አቤቱ፥ መጠ​ጊ​ያዬ ነህ፤
ክብ​ሬና ራሴን ከፍ ከፍ የም​ታ​ደ​ር​ገው አንተ ነህ።
4በቃሌ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፤
ከተ​ቀ​ደሰ ተራ​ራ​ውም ሰማኝ።
5እኔ ተኛሁ፤ አን​ቀ​ላ​ፋ​ሁም፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ሥ​ቶ​ኛ​ልና ተነ​ሣሁ።
6ከሚ​ከ​ብ​ቡ​ኝና በእኔ ላይ ከሚ​ነሡ#“በእኔ ላይ ከሚ​ነሡ” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
ከአ​እ​ላፍ አሕ​ዛብ አል​ፈ​ራም።
7ተነሥ፥ አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ አድ​ነኝ፤
አንተ በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉ​ኝን ሁሉ መት​ተ​ሃ​ልና፥
የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ጥርስ ሰብ​ረ​ሃ​ልና።
8ማዳን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥
በረ​ከ​ት​ህም በሕ​ዝ​ብህ ላይ ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ