የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 4

4
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በበ​ገ​ና​ዎች የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የጽ​ድ​ቄን አም​ላክ” ይላል። በጠ​ራ​ሁት ጊዜ ጽድ​ቄን ሰማኝ፥
ከጭ​ን​ቀ​ቴም አሰ​ፋ​ልኝ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በጭ​ን​ቀቴ አሰ​ፋ​ህ​ልኝ” ይላል።
ይቅር አለኝ፥ ጸሎ​ቴ​ንም ሰማኝ።#ዕብ. 2ኛ መደብ።
2እና​ንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ
ልባ​ች​ሁን ታከ​ብ​ዳ​ላ​ችሁ?
ከንቱ ነገ​ርን ለምን ትወ​ድ​ዳ​ላ​ችሁ? ሐሰ​ት​ንም ለምን ትሻ​ላ​ችሁ?
3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጻ​ድቁ እንደ ተገ​ለጠ ዕወቁ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ እርሱ በጮ​ኽሁ ጊዜ ይሰ​ማ​ኛል።
4ተቈጡ፥ ነገር ግን አት​በ​ድሉ፤
በመ​ኝ​ታ​ችሁ ሳላ​ችሁ በል​ባ​ችሁ የም​ታ​ስ​ቡት ይታ​ወ​ቃ​ችሁ።
5የጽ​ድ​ቅን መሥ​ዋ​ዕት ሠዉ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታመኑ።
6“በጎ​ውን ማን ያሳ​የ​ናል?” የሚሉ ብዙ​ዎች ናቸው።
አቤቱ፥ የፊ​ትህ ብር​ሃን በላ​ያ​ችን ታወቀ።
7በል​ባ​ችን ደስ​ታን ጨመ​ርህ፤
ከስ​ንዴ ፍሬና ከወ​ይን፥ ከዘ​ይ​ትም ይልቅ በዛ።
8በእ​ርሱ በሰ​ላም እተ​ኛ​ለሁ፥ አን​ቀ​ላ​ፋ​ለ​ሁም፤
አቤቱ፥አንተ ብቻ​ህን በተ​ስፋ አሳ​ድ​ረ​ኸ​ኛ​ልና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ