መዝሙረ ዳዊት 5
5
ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ ቃሌን አድምጥ፥
ጩኸቴንም አስተውል፤
2የልመናዬን ቃል አድምጥ፥
ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥
አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና።
3በማለዳ ቃሌን ስማኝ፥
በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እገለጥልሃለሁም።
4አንተ በደልን የሚወድድ አምላክ አይደለህምና፤
ክፉዎች ከአንተ ጋር አያድሩም።
5ዐመፀኞችም በዐይኖችህ ፊት አይኖሩም፤
ዐመፅ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ።
6ሐሰትን የሚናገሩትን ሁሉ ትጥላቸዋለህ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ታጠፋቸዋለህ” ይላል።
ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው እግዚአብሔር ይጸየፋል።
7እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤
አንተን በመፍራት በቤተ መቅደስህ እሰግዳለሁ።
8አቤቱ፥ በጽድቅህ ምራኝ፤
ስለ ጠላቶቼ መንገዴን በፊትህ አቅና።
9በአፋቸው እውነት የለምና፥
ልባቸውም ከንቱ ነው፥
ጕሮሮኣቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤
በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
10አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በነገረ ሠሪነታቸውም ይውደቁ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በምክራቸውም” ይላል።
እንደ ሐሰታቸውም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እንደ በደላቸው” ይላል። ብዛት አሳድዳቸው፥
አቤቱ፥ እነርሱ አሳዝነውሃልና።
11በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤
ለዘለዓለሙ ደስ ይላቸዋል፥ በእነርሱም ታድራለህ።
ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይመካሉ።
12አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፤
አቤቱ፥ እንደ አላባሽ ጋሻ ከለልኸን።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እንደ ጋሻ በሞገስህ” ይላል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 5: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 5
5
ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ ቃሌን አድምጥ፥
ጩኸቴንም አስተውል፤
2የልመናዬን ቃል አድምጥ፥
ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥
አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና።
3በማለዳ ቃሌን ስማኝ፥
በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እገለጥልሃለሁም።
4አንተ በደልን የሚወድድ አምላክ አይደለህምና፤
ክፉዎች ከአንተ ጋር አያድሩም።
5ዐመፀኞችም በዐይኖችህ ፊት አይኖሩም፤
ዐመፅ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ።
6ሐሰትን የሚናገሩትን ሁሉ ትጥላቸዋለህ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ታጠፋቸዋለህ” ይላል።
ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው እግዚአብሔር ይጸየፋል።
7እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤
አንተን በመፍራት በቤተ መቅደስህ እሰግዳለሁ።
8አቤቱ፥ በጽድቅህ ምራኝ፤
ስለ ጠላቶቼ መንገዴን በፊትህ አቅና።
9በአፋቸው እውነት የለምና፥
ልባቸውም ከንቱ ነው፥
ጕሮሮኣቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤
በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
10አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በነገረ ሠሪነታቸውም ይውደቁ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በምክራቸውም” ይላል።
እንደ ሐሰታቸውም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እንደ በደላቸው” ይላል። ብዛት አሳድዳቸው፥
አቤቱ፥ እነርሱ አሳዝነውሃልና።
11በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤
ለዘለዓለሙ ደስ ይላቸዋል፥ በእነርሱም ታድራለህ።
ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይመካሉ።
12አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፤
አቤቱ፥ እንደ አላባሽ ጋሻ ከለልኸን።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እንደ ጋሻ በሞገስህ” ይላል።