መዝሙረ ዳዊት 24
24
የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ።
2አቤቱ፥ አንተን ታመንሁ፤ ለዘለዓለም አልፈር፤
ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።
3አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩምና።
በከንቱ የሚበድሉ ሁሉ ዘወትር ይፈሩ።
4አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፤
ፍለጋህንም አስተምረኝ።
5በእውነትህ ምራኝ፤ አስተምረኝም፤
አንተ አምላኪዬና መድኀኒቴ ነህና፥
ዘወትርም አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና።
6አቤቱ፥ ቸርነትህን ዐስብ፥
ምሕረትህ ለዘለዓለም ነውና።
7የልጅነቴን ኀጢአትና ስንፍናየን አታስብብኝ።
አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት፥
እንደ ምሕረትህ ዐስበኝ።
8እግዚአብሔር ቸር ጻድቅም ነው፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቅን” ይላል።
ስለዚህ የሚሳሳቱትን በመንገድ ይመራቸዋል።#ዕብ. “ኀጢአተኞች” ይላል።
9ለየዋሃን ፍርድን ያስተምራቸዋል፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በፍርድ ይመራል” ይላል።
ለየዋሃን መንገድን ያመለክታቸዋል።
10የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ይቅርታና እውነት ነው፤
ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚፈልጉ።
11አቤቱ፥ ስለ ስምህ ብለህ፥
ኀጢአቴን ሁሉ ይቅር በለኝ፥ ብዙ ነውና።
12እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው?
እርሱ በሚመርጠው መንገድ ይመራዋል።
13ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥
ዘሩም ምድርን ይወርሳል።
14እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኀይላቸው ነው፥
የእግዚአብሔርም ስም ለሚጠሩት ነው።
ሕጉንም ያስተምራቸዋል።
15ዐይኖቼ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው፤
እርሱ እግሮችን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና፥
16ፊትህን ወደ እኔ አድርግ ማረኝም፥
እኔ ብቸኛና ድሃ ነኝና።
17የልቤ ኀዘን ብዙ ነው፤
ከጭንቀቴ አውጣኝ።
18ድካሜንና መከራዬን እይ፥
ኀጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።
19ጠላቶቼ እንደ በዙ እይ፥
በግፍም ጥልን ጠልተውኛል።
20ነፍሴን ጠብቃት አድናትም፥
አንተን ታምኛለሁና አልፈር።
21አቤቱ፥ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና
የዋሃንና ቅኖች ተከተሉኝ።
22እግዚአብሔር እስራኤልን ከመከራው ሁሉ ያድነዋል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 24: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 24
24
የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ።
2አቤቱ፥ አንተን ታመንሁ፤ ለዘለዓለም አልፈር፤
ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።
3አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩምና።
በከንቱ የሚበድሉ ሁሉ ዘወትር ይፈሩ።
4አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፤
ፍለጋህንም አስተምረኝ።
5በእውነትህ ምራኝ፤ አስተምረኝም፤
አንተ አምላኪዬና መድኀኒቴ ነህና፥
ዘወትርም አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና።
6አቤቱ፥ ቸርነትህን ዐስብ፥
ምሕረትህ ለዘለዓለም ነውና።
7የልጅነቴን ኀጢአትና ስንፍናየን አታስብብኝ።
አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት፥
እንደ ምሕረትህ ዐስበኝ።
8እግዚአብሔር ቸር ጻድቅም ነው፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቅን” ይላል።
ስለዚህ የሚሳሳቱትን በመንገድ ይመራቸዋል።#ዕብ. “ኀጢአተኞች” ይላል።
9ለየዋሃን ፍርድን ያስተምራቸዋል፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በፍርድ ይመራል” ይላል።
ለየዋሃን መንገድን ያመለክታቸዋል።
10የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ይቅርታና እውነት ነው፤
ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚፈልጉ።
11አቤቱ፥ ስለ ስምህ ብለህ፥
ኀጢአቴን ሁሉ ይቅር በለኝ፥ ብዙ ነውና።
12እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው?
እርሱ በሚመርጠው መንገድ ይመራዋል።
13ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥
ዘሩም ምድርን ይወርሳል።
14እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኀይላቸው ነው፥
የእግዚአብሔርም ስም ለሚጠሩት ነው።
ሕጉንም ያስተምራቸዋል።
15ዐይኖቼ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው፤
እርሱ እግሮችን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና፥
16ፊትህን ወደ እኔ አድርግ ማረኝም፥
እኔ ብቸኛና ድሃ ነኝና።
17የልቤ ኀዘን ብዙ ነው፤
ከጭንቀቴ አውጣኝ።
18ድካሜንና መከራዬን እይ፥
ኀጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።
19ጠላቶቼ እንደ በዙ እይ፥
በግፍም ጥልን ጠልተውኛል።
20ነፍሴን ጠብቃት አድናትም፥
አንተን ታምኛለሁና አልፈር።
21አቤቱ፥ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና
የዋሃንና ቅኖች ተከተሉኝ።
22እግዚአብሔር እስራኤልን ከመከራው ሁሉ ያድነዋል።