መዝሙረ ዳዊት 25
25
የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ እኔ በየዋህነቴ እኖራለሁና ፍረድልኝ፤
እንዳልደክም በእግዚአብሔር አመንሁ።
2አቤቱ፥ ፈትነኝ መርምረኝም፤
ኵላሊቴንና ልቤን ፈትን።
3ምሕረትህ በዐይኔ ፊት ነው፥
በማዳንህም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በእውነትህም” ይላል። ደስ አለኝ፤
4በከንቱ ሸንጎ አልተቀመጥሁም፥
ከዐመፀኞችም ጋር አልገባሁም።
5የክፉዎችን ማኅበር ጠላሁ፥
ከከዳተኞች ጋር አልቀመጥም።
6እጆቼን በንጽሕና አጥባለሁ፤
አቤቱ፥ መሠዊያህን እዞራለሁ፥
7የምስጋናህን ቃል እሰማ ዘንድ፥
ተአምራትህንም ሁሉ እነግር ዘንድ።
8አቤቱ፥ የቤትህን ጌጥ
የክብርህንም ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።
9ከኀጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥
ከደም ሰዎችም ጋር ሕይወቴን አትጣላት።
10በእጃቸው ተንኮል አለባቸው፥
ቀኛቸውም መማለጃን ተሞልታለች።
11እኔ ግን በየዋህነቴ እኖራለሁ፤
አቤቱ፦ አድነኝ ይቅርም በለኝ።
12እግሮቼ በቅንነት ቆመዋልና፤
አቤቱ፥ በማኅበር አመሰግንሃለሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 25: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 25
25
የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ እኔ በየዋህነቴ እኖራለሁና ፍረድልኝ፤
እንዳልደክም በእግዚአብሔር አመንሁ።
2አቤቱ፥ ፈትነኝ መርምረኝም፤
ኵላሊቴንና ልቤን ፈትን።
3ምሕረትህ በዐይኔ ፊት ነው፥
በማዳንህም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በእውነትህም” ይላል። ደስ አለኝ፤
4በከንቱ ሸንጎ አልተቀመጥሁም፥
ከዐመፀኞችም ጋር አልገባሁም።
5የክፉዎችን ማኅበር ጠላሁ፥
ከከዳተኞች ጋር አልቀመጥም።
6እጆቼን በንጽሕና አጥባለሁ፤
አቤቱ፥ መሠዊያህን እዞራለሁ፥
7የምስጋናህን ቃል እሰማ ዘንድ፥
ተአምራትህንም ሁሉ እነግር ዘንድ።
8አቤቱ፥ የቤትህን ጌጥ
የክብርህንም ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።
9ከኀጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥
ከደም ሰዎችም ጋር ሕይወቴን አትጣላት።
10በእጃቸው ተንኮል አለባቸው፥
ቀኛቸውም መማለጃን ተሞልታለች።
11እኔ ግን በየዋህነቴ እኖራለሁ፤
አቤቱ፦ አድነኝ ይቅርም በለኝ።
12እግሮቼ በቅንነት ቆመዋልና፤
አቤቱ፥ በማኅበር አመሰግንሃለሁ።