መዝሙረ ዳዊት 42
42
የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ ፍረድልኝ፥
ከጽድቅ ከወጡ ሕዝብም በቀሌን ተበቀል።
ከዐመፀኛና ከሸንጋይ ሰው አድነኝ።
2አንተ አምላኬ፥ ኀይሌም ነህና፥ ለምን ትተወኛለህ?
ጠላቶቼ ቢያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመለሳለሁ?
3ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ፤
እነርሱም ይምሩኝ፥
አቤቱ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።
4ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ፥
ጐልማስነቴንም ደስ ወዳሰኛት ወደ አምላኬ እገባለሁ፤
አቤቱ፥ አምላኬ፥ በመሰንቆ አመሰግንሃለሁ።
5ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ?
የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ
በእግዚአብሔር ታመኚ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 42: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ